Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ቀልና ፍንጥርጣሪው ልድርሰት በሸረፈዲን የእናቱ ልጅ ምእራፍ አንድ ቀኑ ቅዳሜ ነው ጸሀይዋ በሥተምሥራቅ በኩል ለመውጣት እያኮበኮበች ነው።እናቴን ካለ ባልና ልጅ እንድትኖር ያደረጋትን አውሬው መኩሪያውን አግኝቼው ቅጣቱን እራው ልሰጠው እየሄድኩለት ነው። የጅማ ገጠራማው ክፍል ነው ያለነው አለ ሮቤል አንዳች ነገር እንዳየ ሮቤል ብእሩ ላይ ጉጠት ነገር ተመልክቶ ነው ሳይታወቀው የጮኸው ጉጠቷን ሲጫናት የብእሩ ጫፍ ተሽከረከረና ወደ ላይ ሌላ ድራብ ሰራጫፉን ሲጫነው የሆነ ክፍል ቀስ እያለ ተበረገደ ፐፐፐፐ መኩሪያው እንደዚህ ብልጥ አትመሥለኝም ነበርቻይኒሽ ስታይል ነው ኑሮህ ሮቤል የፌዝ ጭብጨባ አጨበጨበ አዝናለሁ መኩሪያው እግዛብሄር ከጎናችን ስለነበር በስተመጨረሻ አሸነፍንህ አለና ወደተከፈተው ሚስጥራዊ ክፍል ገባ ሂዊና ሰላም ቤት ደርሰው ማራማዊትን እያጫወቱ ነው። አለ ሚኪ እእእ አንተ ሰካራም ምን ታየህ አለችው ሂዊ እንኩ እዩት እዚህ ፋይል ውስጥ ያለው ድርጅቱ ውስጥ የአክስዮን ድርሻ ያላቸው ባለስልጣኖች ስም ዝርዝር ነውስማቸው አሻራቸው ፎቷቸው በአጠቃላይ ሙሉ መረጃ ነውሚኪ ስንፈልገው የነበረው ኮማንደርም ሠፍሯልኮማንደር መኮንን የሚባል ነው። ሚኪ ከግድግዳ ጋር ገፍትሮ አጋጨው መኩሪያው በርሊን ሆኖ ሳለ ነው እየተካሄደ ያለውን ነገር አብጠርጥራ ታውቃለች መኩሪያው ሚኪን ለማስፈራራት ወደ ቢሮው ከመሄዱ በፊት መኖሪያ ቤቱ ተደብቆ ገብቶ ነበርሮቤልን የት እንደሚቀጥሩት ከጓደኛው ጋር ሲያወራ ነበርያኔ ነው እንግዲህ ወሮ ምእራፍ መኩሪያውን ቦታው ድረስ ተከትላው አሁን ልትተኩስበት የቻለችው እማ እያየሁት ያለሁት አንቺን ነው። መታጠቢያ ቤት ሄዳ ይሆናል በሚል ግምቱ ሊፍልጋት ወደዛው ጎራ አለሠላሜ እዚህ ነሽ ሚኪ መጸዳጃ ቤቶቹን በየተራ ያንኳኳል ነገር ግን ያላሰበው ነገር ገጠመው በዛ ያሉ ሰዎች እንዳይላወሥ አድርገው ያዙትና ፊቱን በጨርቅ ሸፍነው ይዘውት ሄዱ ሚኪ ማንነታቸውን ለመለየት እንኳን ጊዜ አላገኘም ሁሉም ነገር በፍጥነት ነው የሆነበት።
ሠላሜ ሠላም ወሬውን መቀየር ፈለገችና ቆይ ከየት ነው የተላለፈብህ ሱፍ ያለ መልበስ አላርጂክ ሃሃሃ እለብሳለሁኮ ግን ስራ ላይ ብቻ ነው እውማ ግድ ሆኖብህ ነዋ ሠአቱ እየገፋ የመጠጥ ዶዛቸውም ጨምሮ ብዙ ጠጡሚኪ በመጠኑ ቢሠክርም ሠላም ተንበዛበዘች ሚኪዬ እወድሃለሁየኔ ሸበላቅዳበት ብርጭቆዬ ላይአለችው እየተኮላተፈች ሚኪ ከዚህ በላይ መቆየትም ሆነ መጣጣት እንደሌለባቸው በመወህሀን ይበቃናል ሠላሜ ወደ ክፍላችን እንሂድ አላት በናትህ ሚኪ አንድ ብርጭቆ ብቻ አያይ ከዚህ በላይ ከጠጣን አብረን መውደቃችን ነው ከወንበሩ ተነስቶ አቀፈና አነሳት ከዛም ደግፏት ወደ ክፍላቸው እያመሩ ሳለሚኪዬ አለችው ውዴ አቅፈህ አሥገባኝ ክፍሌ እሺ ታዛዥ ነኝ አለና ተሸከማት ከመጠጡ ጋር የሷ ክብደት ሲጨመርበት እየተንገዳገደ ይዚት ገባአልጋው ላይ አስቀምጧት ደህና እደሪ የኔ ቆንጆበደንብ ተኝልኝ ጠዋት መጥቼ እቀሠቅስሻለሁ ግንባሯን ስሟት ለመሄድ ወደ በሩ ፊቱን አዞረ ሠላም እጁን ያዘችውሚኪዬ አብረሀኝ አተኛም ብቻዬን ሠላሜ እርግጠኛ ነሽ አዎበህይወቴ ካንተ ጋር መሆንን እንደመምረጥ እርግጠኛ ሆፔ አላውቅም እሺ የኔ ውድ ሚኪ ብርድ ልብሱ ውስጥ ዘሎ ገባ እሷም ተከትላው ገባች በመሀከላቸው ዝምታ ሠፈነከትንሽ ደቂቃ በሁዋላ ሚኪአለችው ሠላም አቤት የኔ ውድ እቀፈኝ ትቅፍቅፍ ብለን እንተኛደግሞ ዋ ሌላ እንዳታሥብ ክክክክ እሺ አንቺ ሞዛዛ ብሎ አቀፋት የሚኪ ሙቀት በደቂቃዎች ልዩነት እየናረ መጣየራሱ ገላ አቃጠለውእንደ ሰሀራ በረሃ ነደደ። የሰላም አባት ልጄ አላት እጂን ይዞ እያቀፋት እንዴ ምን ያስፈራሻል አባትሽኮ ነኝ ሠላም እጁን ምንጭቅ አደረገችው ቆይ በድብቅ እየተከታተልከኝ ነበር አዎ እየተከታተልኩሽ ነበርምክንያቱም ለደህንነትሽ ሥለምጨነቅ ነው ቆይ ስለምን ደህነነት ነው የምታወራው እኔኮ ትልቅ ልጅ ነኝ የሚጠቅመኝንና የሚጎዳኝን ለይቼ አውቃለሁእራሴን መጠበቅ እችላለሁ ሠላም በንዴት ጸጉሯን አተረማመሠችው ሚኪ እንደ ጅብራ ተገትሮ ሁኔታውን ይከታተላል እና ለምን ዋሸሽኝፍቅረኛሽን አምጥተሽ ልታሥተዋውቂኝ አይገባም ጊዜው ሲደርስ ላሥተዋውቅህ ነበር አንተ ግን ሁሉንም ነገር አበላሸኸው የሰላም አባት ግንባሩን ፈታ አድርጎ ሚኪያስ ወደቆመበት ሄደና እጁን ለሰላምታ ዘረጋ ሚኪ ሠውነቱ በላብ ተደፍቋልቆዳው እያሳከከው ነው አቶ መኩሪያው እባላለሁየሠላም አባት ነኝ በዚህ መንገድ ስለተዋወቅኩህ አዝናለሁ አለው ሚኪ ውሥጡ ነደደ የእጆቹ ጡንቻዎች ተፈታተኑት እዚሁ ጉሮሮውን አንቆ ሲጥ አርጎ ሊገለው ፈለገግን ሊያደርገው አልቻለም ተው እንጂ ሚኪ እቅድህን በችኮላ እንዳታበላሸው ለዚህ አረመኔ ሞት እረፍት ነውበቁሙ ልታሠቃየው ይገባል የሚል ነጋሪት ተሠማው ሠውነቱን ለቀቀ አደረገና እጁን ጨበጠውሚኪያስ እባላለሁየልጅዎት ጓደኛ ነኝ እሺ ልጅ ሚኪያስ ስለመሸ ሰላምን ልወሥድብህ ነውበል ደህና አምሽአንድ ቀን ቤት መጥተህ እራት እየበላን እናወራለንአቶ መኪሪያው የሚያቦለውን ሲጋራ ወደ መሬት ጣል አድርጎ በጫማው ረገጠው ሠላም ሚኪን ጉንጩን ስማው አባቷ መኪና ውስጥ ገባችከአይኗ እሥኪጠፋም ዘወር እያለች ታየው ነበር ሚኪ መኪናውን አስነስቶ በፍጥነት ወደ ቤቱ አመራ የሠላም አባት መሆኑን ማመን አቅቶት የመኩሪያውን ፎቶ ከቦርሳው ውስጥ በርብሮ ፈልጎ ቅድም ያየው መልክ ጋር አስተያየውአዎ እራሱ ነውቀንደኛ ጠላቱ መኩሪያው የፍቅረኛው አባት ነው። አሁንኮ ደህና ነው ወገቧን በእጄ መታ መታ አደረገቻት ዶክተሩ ወደ ክፍሉ ሲገባ ሠላም ሂዊን ለቀቀቻት ሰላማዊት የምትባይው አንቺ ነሽ አላት ዶክተሩ መነጽሩን እያሥተካከለ አዎ እኔ ነኝ ባልተሳሳትኩ ፍቅረኛው ትመስይኛለሽወይም ባለቤቱ አይ ፍቅረኛው ነኝ ዐ ጥሩእሥቲ እውን ሊያነቃው የሚችል ጥሩ ትዝታችሁን አስቢ ሠላም ትንሽ እንደማሰብ አለችና ኦው ሁሌ የሚያንጎራጉርልኝ ሙዚቃ አለበዚያ ላይ የመጀመሪያ ምሽታችን በዚሁ ሙዚቃ ነበር ሂዊ ሠላምን እያዳመጠች ሳግ አነቃትአይኖቿ እንባ አቆሩ ስለዚህ እንሞክረው አሠሚው አላትና ወጣ ዶክተሩ ሰላም ሞባይሏን አውጥታ ሙዚቃውን ከፈተችውከዛም በቅርብ እርቀት ጆሮው ጋር አደረገችው የዶን ዊሊያም ዊ ጎት ሎቪ የሚለው ሙዚቃ ጸጽታ የሠፈነበት ክፍል ውስጥ ለስለስ ብሎ ይንቆረቆር ጀመር አዎ ሠላምና ሚኪ ጀልባው ላይ ውብ በሆነው ምሽት አብረው አተወዛወዙ ነውበድንገት ግን ጀልባዋ ትነቃነቃለችሚኪ ወጣ ብሎ ሲመለከት ከባድና አስፈሪ ዝናብ እየዘነበ ነውንፋሱ ሀይሎ ጀልባዋን ከወዲያ ወዲህ አንገላታት ወዲያውም ግፊት አድርጎባት የውሃው ጥልቅ ክፍል ከተታት ሠላሜ ጀልባዋ ልትሠምጥ ነው ቶሎ ይሄን አጥልቂ እንድትንሳፈፊ ይረዳሸል ሁለታቸውም ቶሎ መንሳፈፊያውን አድርገው ከጀልባዋ ሊወጡ ሲሉ ከየት መጣ የማይባል ማእበል ጭራውን አቅጥኖ ሊናደፍ እንደተዘጋጀ ኮብራ እባብ አንገቱን አቆላሞ አጠገባቸው ደረሰሚኪ ሠላምን እጄን ይዞ በፍጥነት ወደ ውሃው ተወረወረጥንዶቹን ያላገኘው ማእበልም ጀልባዋን ገለባበጣት ሚኪና ሠላም የለበሁት መንሳፈፊያ የሆነ የባህር ዳርቻ ወሥዶ ጣላቸውሚኪ ምንም ባይሆንም ሠላም ግን ብዙ ውሃ ጠጥታትንፋሺ ጸፅ ብሏልሚኪ ከውሃው ውሥጥ ታግሎ ሽሯማ ወደ ሆነው ዳርቻ አሥተ ኛትና ትንፋሺን ለመመለስ ይታገል ጀመር ሠላሜ ተንሺ እንዲህማ ጉድ አትሠሪኝምበከንፈሩ ከአፍንጫዋ ውሃ ይመጥላታልሁለት እጆቹን አነባብሮ ደረቷን ወደታች ይጫናልከንፈሯን በከንፈሩ በመምጠጥ ትንፋሽ ሊሠጣት ይሞክራል በመጨረሻም ሠላሜ ብሎ በመጮህ ከአንቀላፋበት ተነሳና በቂጡ ቁጭ አለሆስፒታል ውስጥ ያሉት ሠዎች በጩኸቱ ተደናገጡሠላምና ሂዊም ተአምር ሆኖባቸው ባሉበት ጥቅም የሌለው በድን ሆነዋል ሚኪ ከዚህ አስፈሪ ቅዝቱ ሲባንን ግራ ተጋባምድረ በዳው ደሴት የለምውሃውም የለምጥቅጥቅ ያለው ጫካም አልታይ አለው ዙሪያ ገባውን እየቃኘ ሠላሜሠላሜ ይላል እዚህኮ ነኝ ይሄው አለሁ የኔ ጌታእጁን ያዝ አደረገችው ትኩር ብሎ አያት ሠላም ደህና መሆኗን አረጋገጠ የት ነኝ ዶክተሩ ጩኸቱን ሰምቶ ሲገባ ሚኪ ነቅቷል ሚኪ ጥያቄውን ቀጥሏል እዚህ ምን እያደረኩ ነው ምን እየሆነ ነው ዶክተሩ ተረጋጋ ሆስፒታል ነው ያለኸውለጥቂት ቀናት እራስህን ስተህ ነበር አለው ምን ሆቼ ነው እራሴን የሳትኩት። ተረጋጋትንሽ እረፍት አድርግ ወደ ራስህ ስትመለስ ሁሉንም ታስታውሳለህፈጣሪ ይማርህ ብሎት ለነርሷ መስጠት ያለባትን መድሀኒት ነግሯት ወጣ ሠላምም ሂዊም የደስታ ማእበል ጠራርጎ ሊወስዳቸው ምንም አልቀራቸውምየሚያፈቅሩት ሚኪ በመንቃቱ እንስቶቹ ደስታቸውን ለመግለጽ ተቃቀፉ ሂዊ ጠጋ ብላ ሚኪ እንኳን ፈጣሪ አተረፈህ አለችው ፊቷ በደ ስታ እያበራ ሚኪ አሁን ወደ እራሱ እየተመለሰ ነውሁሉንም ነገር መለየት ችሏል አመሠግናለሁ ሂዊአላት ሠላምን ሮጣ እንዳትመልጠው በሚመሥል መልኩ እጂን ጠንከር አድርጎ ይዞ ሂዊ ሰላም በፍቅር አይን እያየችው ስትስመው ቆማ መመልከት አልቻለችም በቃ ሰላም አንቺ ከጎኑ ካለሽ እኔ ልሂድና ቤቱን ላጸዳዳው ሂዊ ቦርሳዋን አንጠልጥላ ከክፍሉ ወጣችወደ ቤት እየሄደች ዛፍ ሥር አረፍ ብላ አነባችሚኪ አንተ እንደ እህትህ እንደምታየኝ አውቃለሁ ስህተቱ የኔ ነውግን ምን ላድርግ ደግነትህና እንክብካቤህ አሸነፈኝእህእህ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ግን አታስብ ራስ ወዳድ አልሆንም ሠላምን ምን ያህል እንደምትወዳት አውቂያለሁ እሷም ትወድሃለችእንዴት እንደምትተያዬም ተመልክቻለሁበእናንተ መሀል ገብቼ ደሥታህን ልነጥቅህ አልሻልምአንተን ለመርሳት እሞክራለሁ ልክ እንደምታስበኝ ጥሩ እህትና አጋር እሆንልሃለሁ አለችና እንባዋን እየጠራረገች ከዛፉ ስር ተነሳችእርምጃዋን ቀጥላም ቤት ደረሰች ከሚኪ የፈሰሰው ደም ወለሉ ላይ እንደረጋ ነውየፈሰሰው ደም ብዛቱ ለአይን ይከብዳልቤቱ ለትንሽ ቀን ስለታፈነለአፍንጫ የሚከብድ ሽታ ይሸታልእምክ እምክ ይላል። ሂዊ በድካም የዛላ ጉልበቷን ለማሳረፍ ሶፋው ላይ ጋደም አለችግን አንድ ነገር ግር ብሏታልሚኪን እንዲህ ያደረገው ማነው ዘራፊዎች ናቸው እንዳትል ቤቱ ውስጥ የጎደለ እቃ አልነበረምመኩሪያው ነው ብላ እንዳታስብ መኩሪያው ሚኪ እየሠለለው መሆኑን በምንም ተአምር ሊያውቅ አይችልም ሂዊ ተወዛገበችይሄንን ጥያቄዬን እንግዲህ ሚኪ እራሱ ነው ሊመልስልኝ የሚችለው አለችና ቤቱን ቆልፋ ወደ ቤቷ አመራችየናፈቀቻትን ልጄን ማራማዊትን እና እናቷን እትዬ በለጡን ለማግኘት እርምጃዋን ፈጠን ፈጠን አደረገችው ቋጽጽቋ የግቢያቸው የቆርቆሮ መዝጊያ ሲከፈት የሰሙት እትዬ በለጡ እንደ ልጃቸው የሚያዩዋት ሂዊ መሆኗን አውቀው ደጃፋቸው ላይ ጠበቋት እትዬ በለጡ ሂዊን እንዳዩዋት ደህና እንዳልሆነች ተረዱ ልጄ ምን ሆነሽ ነውያ ልጅ አንድ ነገር ሆነ እንዴ አሏት ከላይ እሥከ ታች አብጠርጥረው እየተመለከቷት አይ ምንም አልሆነምእንዲያውም ነቅቷል እው ምን ይሳነዋል አሉ እትዬ በለጡ እጃቸውን ዘርግተው ታዲያ ልጄ ምነው ከፋሽ ደሥታው ይሆናላ እትዬ አይ ልጄ አትደብቂኝ ንገሪኝእኔኮ አንቺን በደንብ አውቅሻለሁአንድ ነገርማ አለ እትዬ ሚኪ የሚወዳት ፍቅረኛ አለችው ሂዊ ሆድ ባሳትእትዬ በለጡም ደገፍ ካሉበት ድንጋይ ወገባቸውን አላቀው በፍጹም ፍቅር ልክ እንደ እናቷ አቀፏት ልጄ ይቅር በይኝ እኔ ነኝ ልጁን እንዳትተዊው ብዬ የገፋፋሁሽእኔማ ምኑን አውቄው ጥሩ ማድረጌ ነበር ልጄ አይ እትዬ እርስዎ ምንም አላጠፉምእርስዎን ሳይውቅዎት በፊትም አፍቅሬው ነበር ግን ሂዊዬ ልጅቷን የሚያፈቅራት ይመሥልሻል አዎ ከምልዎት በላይ ነው የሚወዳት ታዲያ ምን ተሻለ ልጄ አይጨነቁ እትዬ እረሳዋለሁይልቅ ማራማዊት የት ናት ናፍቃኛለች እሥካሁን ስትጫወት አርፍዳ አሁን እንቅልፍ ወስዷታል አንዴ አይችያት ልምጣሂዊ ማራማዊትን ለማየት እትዬ በለጡ ቤት ገባች እትዬ በለጡም ትክዝ ብለው ከተመለከቷት በሁዋላ ተከትለዋት ወደ ውስጥ ዘለቁ ቋድድፏድፏጁ ጽጵጵጵጵድፕጵፓኗ ጽድፕድድ ድድድ ጽድድድድጃቋ ድድቋጽ ሚኪ ሆስፒታል ከገባ ፖተኛ ቀኑ ነውበቶሎ ስላገገመ ዶክተሩ ከሆስፒታል እንዲወጣ ባዘዘው መሠረት በሳምንቱ ከአልጋ ላይ ሊነሳ ነው ክፍሉ ውስጥ ሂዊና ሠላም ይገኛሉአንዳንድ እቃዎቻቸውን እየሸከፉ ነው በተጨማሪም ከተጠቂው ከራሱ አንደበት ቃል ሊቀበሉ የመጡ ሁለት ፓሊሶችም ማስታወሻና ብዕራቸውን ቀሥረው ይጠባበቃሉ አቶ ሚኪያስእንኳን ፈጣሪ ማረህ ስለተፈጠረው ነገር ታስረዳንአለ ጠቆርና ቦርጩ ወጣ ያለው ፓሊስ እእእእ እኔንጃ አላውቅም ትዝ የሚለኝ ተመትቼ ከወደቅኩ በሁዋላ ቤቱን ሲያተረማምሱትና ሲበረብሩት እንደነበር ነው አይ ምንም አይነት ጠላት የለኝምእንዳልኬችሁ ዘረፋ ነውከኪሴ ገንዘብ ወስደውብኛል በዛ ላይ ቤት ያስቀመጥኩትንም ገንዘብ ወሥደውት ይሆናል ሚኪ ሆዱ እያወቀ የተፈጠረውን አድበሰበሰው እሺ ዘራፊዎችን አሥተውለሃቸዋል ማለት ፊታቸውን መለየት ትችላለህ ትንሽም ፍንጭ ቢሆን ዱካቸውን ለመለየት ይጠቅመናል አይ ምንም ትዝ አይለኝምደግሞ ፊታቸው በጭንብል ተሸፍኗል እሺ አቶ ሚኪያስ ስለተባበርከን እናመሰግናለንፈጣሪ ጨርሶ ይማርህ ብለውት ሲወጡ መርማሪ አለ ሚኪ ፓሊሶቹ ከአንገታቸው ዘወር አሉ ወንጀለኞቹን በቅርብ ቀን ለፍርድ እንደምታቀርቧቸው አምናለሁ አላቸው እራሳቸውን በመነቅነቅ አወንታቸውን ገልጸውለት የከፈቱትን በር አልፈው ሄዱ። አለችው ሠላም አይን አይኑን እያየችው አንቺን እንዴት ብዬ እተውሻለሁ የኔ አለምከሞት ጋር እንኳን እንድታገል ያስቻለኝ ላንቺ ያለኝ የማያልቅ ፍቅር ነው ግንባሯን ሳማት እሺ የኔ ጌታ መቼም እንዳትተወኝ ሠላም እቅፉ ውስጥ ገባችሚኪ ግን ወይኔ ብሎ ጮኸ ሠላም በመደንገጥ ብርግግ ብላ ከእቅፉ ውስጥ ወጣች ምነው የኔ ጌታምን ሆንክብኝ ሠላም የምታደርገው ጠፋት ስትጫፒኝ በደንብ ያልዳነውን ትካሻዬን ሠበርሽው መሠል አላት ግንባሩን ኩምትርትር እያረገ እሺ በቃ ዶክተር ጋር ስልክ ልደውል ሠላም እየተቻኮለች ስልኳን ፍለጋ ቦርሳዋን መበርበር ያዘች አላስችል ያለው ሚኪ ሃሀሃሃሃሃሃሃ ከት ከት ብሎ ሳቀ። አላት ሊያስደስታት ስለፈለገ እንዴታ ቅዝቴ ለመልካም ነዋበል ሥጣት እኛ ሴቶቹ እናውራ ሚኪ ስልኩን ለሠላም አቀበላት እማማ እንዴት ነዎት ሠላም እባላለሁ አለቻት በተረጋጋና ለስለስ ባለ ድምጽ የልጄን ልብ የሠረቅሽው ምራቱቴ አንቺ ነሽስላንቺ ገና ያየሽ ቀን ነግሮኛልልጄን ተንከባከቢልኝ አደራቁመቱ እንዲሁ ረዘመ እንጂ ስለሴት አስቦ አያውቅምአደራ ጠብቂልኝ ልጄን እሺ እማማ አይጨነቁ እንዲከፋው አላደርግም ሚኪ ስልኩን መልሶ ተቀበላት እማማ እንዴት ናት ወደድሻትካልወደድሻት እተዋታለሁ አለ እየቀለደ እረ ልጄ ወድጃታለሁ እረጋ ያለች ናትደግሞ እንዳትቀላውጥ የሚኪ ስልክ ጢው ጢው ብላ ዘጋችይሄ የተረገመ ስልክ አለና ቻርጅ እንድታረገው ለሠላም አቀበላት ሰላሜ አላት ሚኪ ወዬ የኔ ጌታ አለችው ቤት ሂደሽ እረፍት አድርጊአልታወቀሽም እንጂ ተጎሳቁለሽብኛልኮሶስት ቀን ሙሉ ከጎኔ አልተለየሽም አላደርገውም እንዴት እንዲህ ሁነህ ሥለመጎሳቆሌ አሥባለሁሚኪ እንደ ባዳ እያደረከኝኮ ነው አይ እንደዛ አይደለም ውዴ አባትሽ ከቤት ስትጠፊ ማሠቡ አይቀርምበዚያ ላይ ሶስት ቀን ሙሉ ትምህርት ቤት አልገባሽምውዴ እያልኩሽ ያለሁት ቤት ደርሰሽ ለአባትሽም ታየት በይትምህርት ቤትሽም ያለውን ነገር አሥተካክለሽ ተመልሰሽ ነይልኝ ነው ካልክ እሺ የኔ ጌታ አለችውና ቦርሳዋን አነሳች ጎንበስ ብላም ከንፈሩ ላይ ተጣበቀችበት ውይ የልቤን ታውቂያለሽኮ ይሄ ኢንጆሪ ከንፈርሽ ናፍቆኝ ነበር አላት ሂድ ሞዛዛቻው በቃ እወድሃለሁአለችውና እየወጣች ሳለ ሂዊ ከኪችን ቡና ይዛ ሥትመጣ ተገናኙ እንዴ ሠላም ወዴት ነው ወደ ቤት ባሌ አባረረኝ ቆይ ቡና ጠጥተሽ ትሄጃለሻ አይ ይቅርብኝእሥክመጣ ባሌን ጠብቂልኝ የሚያሥፈልግ ነገር ካለ ደውይልኝቻው ብላት ታክሲ ለመያዝ ሄደች ሂዊ ያፈላችውን ቡና ለሚኪ አቀበለችውና ተመቻችታ ቁጭ አለች እሺ ሚኪ እነማን ናቸው የደበደቡህ ዘራፊዎች መሠሉኝ ለፓሊሶቹ የሠጠኸው ቃል ውሸት እንደሆነ እኔም አንተም በደንብ እናውቃለንበየት አገር ነው ሌባ ሳይዘርፍ የሚሄደው የተወሠነ ገንዘብ ወሥደውብኛልኮ ሚኪ ቤት ስገባ የታሠርክበትን ወንበርና ገመድ አይቼዋለሁእውነቱን የማትነግረኝ ከሆነ ሌላ አጋር መፈለግ ትችላለህ እሺ አረጋጊው እነግርሻለሁልደብቅሽ ፈልጌ ሳይሆን ነገሩ ግራ ሆኖብኝ ነውእንዴት እንደምነግርሽ ጨንቆኝ ነው ግዴሌም ሚኪ ንገረኝ አብረን መፍትሄ እንፈልግለታለን መኩሪያው ነው እንደዛ ያስደረገኝ ምን ገናኮ እንቅስቃሴ ላይ እንኳን አልገባንምእንዴት አወቀህ አይ ማወቅ እንኳን አላወቀኝምመኩሪያው የሰላም አባት ነውከእሷ ጋር ስላየኝ ብቻ ነው እንደዛ ያደረገው ሂዊ ደነገጠችሚኪ የነገራትን ፍጹም ልታምን አልቻለችም ታውቂያለሽ ሂዊ ሠላምን ከምልሽ በላይ አፈቅራታለሁእሷ ማለት መለአክ ናት ለሠው አዛኝደግአሥተዋይና የዋህ ሴት ናትምኗም እሱን አይመሥልም። ሚኪ የሆነ ሰው እቃ በፌስታል አንጠልጥሎ መኖሪያ ቤቱ አከባቢ ተመለከተትኩረቱን ስብስቦና እይታውን አጥርቶ ሲመለከት ሠውዬው የግቢውን በር ለመክፈት ከኪሱ ቁልፍ እያወጣ ነውሂዊ አላት ሚኪ ዝም አለችውሂዊ ወንበሩን ተደግፋ አንቀላፍታለች በእጁ ነቅነቅ አደረጋት ምናለ ትንሽ ብተኛ ባትረብሸኝ በእጄ አፏን ከድና አዛጋች ሂዊ ንቂና ለማየት ሞክሪ የምንፈልገው ሰው የመጣ ይመሥለኛል ሂዊ ተስተካከለችና አይኖቿን አሽታ ፊት ለፊት ለማየት ሞከረች አዎ ሠውዬው ነውእንሂዳ ምን እንጠብቃለን አለችና የመኪናውን በራፍ ከፈተችው አያይ ቆይሲገባ እንጠብቀውና እንደማንኛውም ሠው አንኳኩተን እናሥከፍተዋለንአለና እጂን ያዝ አደረጋት አዎ ሠውዬው የግቢውን በር ከፍቶ ገባ ከ ደቂቃ በሁዋላ እነ ሚኪም ከመኪናቸው ወርደው ወደ ቤቱ ቀረቡሲደርሱ ግን እንዳሠቡት የግቢው በር ከውስጥ ተቀርቅሮ አላገኙትምገርበብ ብሎ ነበርጥርጣሬ ያደረበት ሚኪ ሂዊን በጀርባው ከልሎ ገርበብ ያለውን በር በጥንቃቄ ገፋ አደረገውና አንገቱን አስግጎ በአይኑ በየአቅጣጫው አማተረምንም አደጋ ላይ የሚጥል ነገር የለምቀስ እያለ ገባ ሂዊም ተከተለችው የሲ አይ ኤ ኤጀንት ሁነን አረፍነዋ አለችው ሂዊ እየሳቀች ምንም እንደታወራ በእጁ ምልክት አሳያትና አጥሩን ዘልቀው ወደ ደጃፉ አመሩ ደርሰውም በሩን አንኳኩ መልስ የለምበድጋሚ አንኳኩ ኮሽ እንኳን የሚል ድምጽ አይሠማምትግስቱ የተሟጠጠበት ሚኪ በሩን ገፋ ሲያደርገው ያለምንም ትግል ሠተት ብሎ ተከፈተቀድሞውንም አልተቆለፈም ነበር ሚኪ እየሆነ ያለው ነገር ባያምረውም ወደ ውስጥ መግባትን ወስኖ ቀኝ እግሩን አስቀደመ ቀጥሎም ግራ እግሩን አሥከተለ የፈራው አልቀረለትም ማካሮቭ ሽጉጥ ፊት ለፊቱ ተደግኖበታል እንዳትንቀሳቀስእጅህን ወደ ላይ አድርግአለበለዚያ ግንባርህን ነው የምበጠርቀው አለው ከፊቱ የተገተረው ሠውዬ ስህተት እንዳትሰራእኛ ልንጎዳህ አልመጣንምሽጉጡን ዝቅ አድርገው አለው ሚኪ አፍህን ዘግተህ ባለህበት ቁምአጋርህንም አሥገባትአለው ጠንከር ባለ አነጋገር ሂዊ እግሮቿ እየተብረከረኩ እጂን ወደ ላይ እንደሰቀለች ወደ ውስጥ ገባች አሁን እነማን እንደሆናችሁ ትናገራላችሁ ደህንነት ወይም ሚስጥራዊ መርማሪ ናችሁ አይደል እረ አይደለንም አለች ሂዊ እና ማን ልኳችሁ ነው። ሂዊ አጠይቂኝ ከዚህ በላይ እኔም አላውቅምመልእክት አሥቀምጣልኝ አዳምጩው ነው ስንት ሰአት ላይ ነው ያስቀመጠችልህ ገ አከባቢ እሺ ወዴት ነው እየሄድን ያለነው እነ ሰላም ቤት ነዋ ሚኪ ተረጋጋአሁንኮ ሰአት ሊሆን ነው ምን ለማለት ፈልገሽ ነው ለሁሉም ነገር አርፍደናል እያልኩህ ነው እንዲህ አትበይኝ ሠላሜ ምንም አትሆንምታያለሽ ደህና ሁና እናገኛታለን ጮኸባት ሚኪ እሷ ምንም ትሆናለች እያልኩህ አይደለም የኔና የአንተ እዛ መገኘት ህይወታችንን ሊያሳጣን ይችላልእቅዳችንም ሊበላሽ ይችላልምክንያቱም መኩሪያው አንተ የልጁ ፍቅረኛ እንደሆንክና እኔ ደግሞ የበፊት ቅምጡ እንደነበርኩ ያውቃል ስለዚህ ሁለታችንን አንድ ላይ ቢያየን ምን የሚፈጠር ይመስልሃል አለችው ለዛ ባለው አነጋገር ሚኪ መኪናውን አቆመውና መሪውን ደገፍ ብሎእሺ አሁን ምንድነው ያሰብሽውበምን መልኩ ስለ ሰላሜ ልወቅአላት ወደ ቀልቡ ተመልሶ ያሰብኩት ምን መሰለህ ሮቤልን አብሮን እንዲሄድ እናድርግና እሱ የተፈጠረውን ያጣራልን ማንነቱ ስለማይታወቅ አደጋ አይኖርብንም አለችው ሚኪ ምንም ሳይመልስላት ወደ ኮሌፌ ነዳውሰአቱ ስለመሸ መንገዱ ጭር ብሏልበመጨረሻው ፍጥነት መኪናውን አከነፈው አየር ላይ የሚንሳፈፉ እሥኪመሥል ድረስ እንደደረሱ መኪናውን አቁሞ የሮቤልን የግቢውን መዝጊያ ይደበድቡ ጀመር ጋደም ብሎ መጽሀፍ እያነበበ የነበረው ሮቤል ሲጢጥ የሚል የሚኪና ድምጽ ሲሰማ ጆሮውን ወደ ውጪ ቀሰረውጭራሽ በሩ ሲቆረቆረ ሽጉጡን ከኮመዲኖው መ ሳቢያ አወጣና በጥንቃቄ ወደ በሩ አመራድብደባው አየለ ሊያጠቃው የመጣ ተሹሎክሉኮ እንጂ በግልጽ እንዲህ በር በሀይል እንደማይመታ ስላወቀ ድምጹን ዝቅ አድርጎ ማነው አለ ሮቤል ሚኪ ነኝ ክፈትልኝ ሮቤል ኡፍፍፍፍ ብሎ በረዥሙ ተነፈሰ በሩን ከፍቶም አስገባቸውእናንተ እብዶች ናችሁ እንዴ ምንድነው እንደሰይጣን አሥሬ ውልብ የምትሉብኝ ሮቢ እርዳታህ ያስፈልገናል አለችው ሂዊ ሮቤል የሚኪን ፊት ሲያይ በደህና እንዳልመጡ ገባውምነው በሰላም አላቸው የተከሰተውን መጥፎ ነገር ነግረውት በሚኪ መኪና ወደ ቦሌ ሄዱ ከመኩሪያው መኖሪያ ቤት መቶ ሜትር ርቀት ላይ ሰዋራ ቦታ ፈልገው መኪናዋን አቆሟትና ሮቤል የተፈጠረውን ለማወቅ ከሚኪናው ወርዶ በእግሩ ተራመደ ሮቤል ከሄደ ግማሽ ሰአት ቢቆጠርም እስካሁን አልተመለሰም ሚኪ ከዚህ በላይ መቆየት አልቻለም ቁጭ ብሎ የመጠበቅ ትግስቱ ሲሟጠጥበት ከመኪናው ወረደሂዊም ተከትላው ወርዳ ልታስቆመው ሞከረች እባክህ ሚኪ በእኔ ይሁንብህ አትሂድመኩሪያው ወይ ይገልሃል ወይም ፓሊሶች ይይዙሃል ሂዊ ተይኝአታስቁሚኝ ወደ መኪናው ተመልሰሽ ግቢ አላት በጣቱ እየጠቆመ እመነኝ ሁሉም ጥሩ ይሆናልግን በተረጋጋ መንገድ እናድረገው ሚኪ ሊሰማት አልቻለም መንገዱን ቀጠለሂዊ ስሜቷ እንቢ ሲላት እየሮጠች ሄዳ ክንዱን ያዝ አደረገችውወደ እራሷ አዞረችውና ሚኪ ሳያስበው ከንፈሩን በከንፈሯ ገመጠችው። ሚኪ ከላዩ ላይ መንጭቆ ገፈተራት ሂዊ ምን ማድረግሽ ነውእኔና አንቺኮ በሥጋ ዝምድና ባይኖረንም ወንድምና እህት ነውእንዴት እንደዚህ ታደርጊያለሽ ጮኸባትበጥፊ ሁሉ ሊመታት ከጀለ ሂዊ በሀፍረት ተሸማቀቀች ሚኪ እምነትህን ስላጎደልኩ ይቅርታ አድርግልኝአእምሮዬ ስለተጨናነቀ ነው ይሄን ያደረኩት እንጂ ምንም አሥቤ አልነበረምትሞታለህ ብዬ ስለፈራሁ ስሜቴ ተፈታተኘኝእንባዋ ኩልል እያለ ወረደ በይ በቃሽ ሂዊ አታልቅሺአሁን በሁለታችን መካከል የተፈጠረውን እንዳልተፈጠረ አርገን እንረሳዋለን ትካሻዎን ያዝ አድርጎ አባበላት ሰዎች ምንድነው የምትላቀሠት አለ ሮቤል ከሄደበት ተመልሶ እየተቀላቀላቸው እእእ ምን አዲስ ነገር አለ ሰላሜ እንዴት ናት አለው ሚኪ ግቢው በፓሊሶች ተሞልቷልየህክምና ቡድኑ ጥቃት የደረሠባቸውን የጥበቃ ሰራተኞች እያከመ ይገኛልመርማሪዎቹም ቦታ ከልለው ስራቸውን እየሠሩ ነው ሮቢ እባክህ መስማት የምፈልገውን ንገረኝ አለው ሚኪ ሆዱ እየሻከረበት ምን መሰለህ ሚኪ ሰላም በቤቱ ውስጥ የለችም ምን አለ ሚኪ አይኑ እየተጉረጠረጠ ሚኪ ተረጋጋ እንደሚመስለኝ ከሆነ ሰላም አልሞተችም ተጠልፋ ነው ለምን ይሄን ልታስብ ቻልክ ቢገሏት ኖሮ አሥክሬኗ ይገኝ ነበርሌላው ደግሞ መኩሪያው ከብዙ ሠዎች ጋር ይነካካል ብዙ ጠላት አለው ስለዚህ እሷን ይዘው ሊጠቀሙበት ነው እሺ አሁን ማድረግ የምንችለው ነገር ምንድነው። መኩሪያው ይሄ ድርጊቱ የሠላምን ህይወት አደጋ ላይ ቢከተውም ትእቢትና አልነካም ባይነት ወጥሮ ይዞት ከትእዛዛቸው ውጪ ሆነአዎ አሁን ላይ ሠላምን ማትረፍ ብቻ አይደለም ፍላጎቱ ይሄን ያህል እሱን የተሳፈጡትን ሰዎች እሥከመጨረሻው አደባይቶ ልክ ማስገባትና ክብሩን ማስጠበቅ መኩሪያው ከጠዋቱ ሰአት አከባቢ መኪናውን አስነስቶ ወደ ተባለበት መጋዘን ጉዞ ጀመረበቤቱ አከባቢ አድፍጠው የነበሩት እነ ሚኪም በቅርብ እርቀት ይከተሉት ጀመር ይገርማል መኩሪያው በህይወቱ አንድ ጊዜ ጥሩ ስራ ሊሰራ ነውህይወቱን ለልጁ አሣልፎ ለመስጠት ብቻውን እየሄደ ነው አለች ሂዊ ምንም ጨካኝ ቢሆንኮ ልጁ ናትሁሉም አባት ለልጁ ጥሩ ነው አለ ሮቤል ሚኪ ግን በሀሳባቸው አልተሥማማም እንዲያውም የመኩሪያው እንዲህ በነጻነት ብቻውን መሄድ ጥርጣሬ አሳድሮበታል አይ እኔ እንኳን አልተዋጠልኝምእንደ መኩሪያው አይነት እራስ ወዳድ ሠው ይሄው መጣሁላችሁ ግደሉኝ ብሎ የሚሄድ አይመስለኝም ብቻ ምን እንደሆነ ባላውቅም የሆነ ተንኮል አስቧል አለ ሚኪ ሽጉጡን እያገላበጠ መኩሪያው የተነገረው መታጠፊያ ጋር ሲደርስ መኪናውን አቆመውና ስልክ ደወለ ሄሎ አለቃ ኮማንደር ሁሉም ነገር ሠላም ነው። የያዛችሁት ቦታ ምንም አያስጠረጥርም ሰዋራ ነው እውን ለእኔ ተወውአከባቢውን ከቃኘሁ በሁዋላ ነው ጥሩ ቦታ ፈልጌ የመሸግኩት ማንም ሊያየን አይችልም እሺ ሁኔታው እንዴት ነው ብዙ የታጠቁ ሰዎች አሏቸውሠዎቹ የተደራጁ ናቸው ግን ቢሆንም እንችለዋለን አምንብሃለሁ ኮማንደር መኩሪያው ስልኩን ዘጋና የኮረኮንች መንገድ ጉዞውን ጀመረ እነ ሚኪ የመኩሪያው መንገድ ላይ መቆም ግር እያላቸው መከተላቸውን ቀጠሉ ቦታው ላይ ለመድረስ ትንሽ እንደቀራቸው ሚኪ ቅጠል ውስጥ የተደበቁትን የመኩሪያው ሰዎች አያቸው ሮቤል እዚህ ጋር አቁመው መኪናውን አለው ሚኪ ፈጥኖ ምን ተፈጠረ ። እሺ አሁን ምን እናድርግአለች ሂዊ መኪናውን ሠዋራ ቦታ ደብቀን በእግራችን እየተሹለከለክን በደረታችን እየተሳብን መጋዝኑ ጋር መድረስ ነዋግን ሂዊ እንዳታስቸግሪ አንቺ መኪና ውስጥ ትጠብቂናለሽ አላት ሮቤል እንዴ ለምን አለች ኩስትርትር እያለች ምን መሰለሽ ሂዊ ቆራጥ ሴት እንደሆንሽ አውቃለሁ ነገር ግን እዛ የሚያስፈልገው ሽጉጥ የያዘ ሠው ብቻ ነውእዚህ ደግሞ ሁኔታውን እየቃኘ የሚያሳውቀን ሰው ያስፈልገናል ስለዚህ እኛን በዚህ እርጂን አላት ሮቤል ሽጉጡን በጀርባው እየሻጠ እንደማያስከትሏት ያወቀችው ሂዊ ተስፋ ቆርጣ ዝም አለች ሂዊዬ ምንም ቢፈጠር ከመኪናው እንዳትዎርጂ አያድርገውና መጥፎ ነገር ቢከሰት መኪናውን አስነስተሽ ከዚህ ተሰወሪ አላት ሚኪ ሚኪና ሮቤል ጥንቃቄ በተሞላበት አካሄድ እየተሽሎከለኩ የየትኛውም አካል እይታ ውስጥ ሳይገቡ ከመጋዝኑ ከጀርባው ክፍል ደረሱነገር ግን ያገኙት መጋዝን አልነበረምትልቅና የሚያምር ቤት ነው የቱ ነው መጋዝኑ አለ ሚኪ እያቸው እነዚህን መኪኖች አለው ሮቤል ለምን ከጀርባ እንደቆሙ ያስተዋለውን ሊነግረው ፈልጎ እእእእእ ምን ሰዎቹ እዚሁ ቤት ውስጥ ናቸውመጋዝን ብለው የነገሩት መኖሪያ ቤት ላለማለት ነውእነዚህ መኪኖች ከጀርባ የተዘጋጁት መኩሪያው ችግር ከፈጠረ በጀርባ ለማምለጥ ነው በማለት ሚኪ ያላሰበውን ነገረው ብዙም ሳይቆይ ከምድር ቤት ድምጽ ሰሙድምጹን ለማጣራት ጆሯቸውን ቀስረው አይናቸውን ቢያቅበዘብዙም ጭላንጭል ድምጹ ከየት እንደሚመጣ መለየት ከበዳቸው በመጨረሻም ሚኪ የቆሙበት ጋር በራፍ ተመለከተራመድ ብሎ ተጠጋና በመዝጊያው ክፍተቶች አሾልኮ ለማየት ሞከረአዎ እንደ እድል ሆኖ አጋቹና መኩሪያው ያሉት እነ ሚኪ የቆሙበት ቦታ ላይ ነውሮቤል ና እይማ እዚህ ናቸው በጀርባ ማምለጫቸው ይሄ መሆን አለበት አለው ሮቤልና ሚኪ በጀርባ ደህንነታቸው ቢጠበቅም ለጊዜው ከፊት በኩል አምርተው ሠላምን ሊያድኗት አይችሉም ምክንያቱ በብዙ ሰዎች እየተጠበቀ ነው። በቂጡ ተዘርፍጦ በቀኝ እጁ ከጭንቅላቷ ከፍ አደረጋትና ጭኑ ላይ አሥቀመጣት ሚኪ ተረጋጋ ድንጋጤው እራሷን አሥቷት እንጂ አልተተኮሰባትም አለው ሮቤል መኩሪያው የታሰረበትን ገመድ ሙሉ በሙሉ አሥወገደለት መኩሪያው ወደ መሬት ተጎንብሶ ልጄ እኔ ዝም ልበልልሽ እያለ እንድትነቃ እጂንና ትካሻዋን ወዘወዘውነቀነቃት ሮቤል የቤቱን ግቢ ሲቃኝ ትንሽ ፈቀቅ ብሎ የውሃ ታንከር እይታው ውስጥ ገባበጆግ ውሃ ይዞ ተመለሰናተረጋጉ ሰዎችትንሽ አየር ስጧትከላይዋ ላይ ገለል በሉላት አላቸው ትንሽ ለቀቅ ሲያደርጉለት አሁን ትነቃለች አለና በጆግ ይዞ የመጣውን ውሃ ፊቷ ላይ እረጨባት በአናቷም አፈሰሰባት ሠላም ተንፈራግጣ ተነሳችመላ ሰውነቷ ይንቀጠቀጥ ነበር አባቷን ከጎኗ በህይወት ስታየው እውነት አልመሰላትም ፊቱን በእጂ ዳበስ አደረገችው አዎ የእውነት አጠገቧ ያለው የሙት መንፈስ ሳይሆን በህይወት ያለው አባቷ መሆኑን አረጋገጠችበሌላኛው አቅጣጫ ደግሞ ሚኪን አየችው ቅዝት ውስጥ ያለች መሰላት ሰላሜ ደህና ነሽ አላት ሚኪ እንዴ ምንድነው ነገሩ ሚኪ እዚህ ምን ያደርጋል። ጠየቀችው አባቷን ግራ ተጋብታ ልጄ እነሱ ናቸው ህይወታችንን ያተረፏትእነሱ ናቸው እቺን አየር እንድንተነፍስ እድል የሰጡን አላት ፈገግ ብሎ ሰላም ተጠግታ ሚኪን ተጠመጠመችበትሚኪዬ ለሁለተኛ ጊዜ አተረፍከኝሁለቴ ደረስክልኝአንተ እንደማተወኝ አውቅ ነበርበዚያ በጭንቅ ጊዜዬ እንኳን አንተን ማሰብ አላቆምኩም ነበርአፈቅርሃለሁ የኔ ጌታ አለችው እየተንሰቀሰቀች መቼም አልተውሽምከአንቺ ውጭ ምን ህይወት አለኝናአፈቅርሻለሁ የኔ ልእልትሞት እንኳን ከአንቺ ሊለየኝ አይችልም ሚኪ እያለቀሰ እጆቿንጉንጮቿን ግንባሯንና አንገቷን እያፈራረቀ ይሥማት ጀመር እሷም እንደዛው ቆፍጣናው መኩሪያ በመካከላቸው ያለውን ጥልቅ ፍቅር አይቶ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ሰውኛ ልቡ እራርቶና አዝኖ አለቀሰባለማወቅ ሚኪ ላይ ጨክኖ ሳያመዛዝን ባደረሰበትም ጉዳት እፍረት ተሰማው ሰላምና ሚኪ ተላቅሰው እንደጨረሱ ሰላም ብድግ አለችና ሮቤልን አመሰገነችው ሰላም ሞትና ህይወት ጭንቀትና ደስታ በአንዴ ተደራርበውባት እሥካሁን የሚኪ ክንድ መቁሰሉንና እየደማ መሆኑን አላየችውም መኩሪያው ከለበሰው ሸሚዝ ላይ እራፊ ጨርቅ ቀደደና ና ልጄ ሀኪም ጋር እሥክንሄድ ልሰርልህ አለው ሚኪም እሺ ብሎ እጁን ዘረጋለት ሁሉም ሰላም እንደሆነ መኩሪያው ለኮማንደር መኮነን በሮቤል ስልክ ደወለለት ሄሎአቤት አለ ኮማንደሩ ሄሎ ኮማንደር እኔ ነኝ መኩሪያው አለቃ የት ናችሁተርፈሃል አዎ ሁሉም ሰላም ነውአንተስ ጋር አልቋል አዎ ጨርሰናል የተወሰኑትን በቁጥጥር ሥር አውያለሁግን እንዴት ሆኖ ልታመልጡ ቻላችሁ። ጉድጽድድፏድቋ ሮቤልና ሚኪ የተሳካ ምሽት በማሳለፋቸው ተደስተዋል ዛሬ መኩሪያው በገዛ ምላሱ ውድቀቱን ጠራ አለ ሮቤል በጣም እንጂያልከው እውን ሆኗል ሮቢ ሚኪ ሮቤልን በአድናቆት ተመለከተው እሺ ሚኪ ይሄንንማ አሁኑኑ ማክበር አለብን ዛሬ አዳር ሲጠጣ ሲጨፈር ነው የሚታደረውጥንካሬያችን ይለይናል አለው ሮቤል እየሳቀ ሮቤል ለሂዊ ስልክ ደውሎ በአስቸኳይ ወደ ቦሌ እንድትመጣ ነገራት አንተ የእውነትህን ነው እንዴ አለው የምሩን ያልመሰለው ሚኪ አዎ በመጠጥ ይቀለዳል እንዴዛሬ እንደ ጉድ ይቀመቀማልበል አሁን አለ የተባለ ጭፈራ ቤት ነው የምወስድህተከተለኝ ሮቤልና ሚኪ ገብተው በመጠኑ እየጠጡ ሂዊን ይጠብቋት ጀመርመሽታ ቤቱ ገና ጊዜ ስለነበር ደመቅመቅ አላለም ቢሆንም ግን ቀለም እየቀያየረ የሚንቦገቦገው ዲምላይትና የጆሮ ታምቡር የሚበጥሰው የሙዚቃ ጩኸት ድባቡን አሳምረውታል። ሚኪ ለምን እንዲህ እንደምትሆን ደጋግሞ ቢጠይቃትም ሰላም ልትነግረው አልቻለችም እለተ አርብ ሚኪ ሰላምን ከትምህርት ቤት ወደ ቤቷ እያደረሳት ነውቤቷ ሳይደርሱ ድንገት መኪናውን አቆመው የእሷ እንዲህ መሆን ምን ያህል እየጎዳው እንደሆነ አስረዳት የማትነግረው ከሆነ የመጨረሻቸው እንደሆነ ቁርጥ አድርጎም ነገራትይሄኔ የሰላም ጉንጮች በእንባ ታጠቡ እነግርሃለሁ ነገር ግን በቅድሚያ ማየት ያለብህ ነገር አለ አለችውና ወደ ቤቷ ወሰደችው እናቷ ክፍል አስገብታው ስለ እናቷ የሆነውን አስረዳችው በመጨረሻም ሚኪ አዝኖና ተክዞ ከግቢው እየወጣ እንዳለ አየህ ሚኪ አሁንስ ማልቀስ አይገባኝም ምርቃቴ ጥቂት ቀን ነው የቀረው ግን እንደምታየው እናቴ አትኖርም አባቴም የኔ አይደለም ታዲያ እንዴት አይከፋኝም አለችው እያለቀሠች ሚኪ ወደ ሁዋላ ተመልሶ አጥብቆ አቀፋት አይዞሽ ሠላሜ እኔ አለሁልሽ የእነሱን ቦታ ባልተካም አግዝሻለሁ አላት ሚኪ ከዛ በሁዋላ ነው እንግዲህ ሁለቱን ለማስማማት ጥረት ማድርግ የጀመረውየሰላምን ደስታ ለመመለስ ሲል የግድ ማድረግ ነበረበት ሁለቱን የእረፍት ቀናት እንደምንም ቆጥሮ ሰኞ ቀን ደረሰለት በጠዋት ተነስቶ ቢሮ ገባትንሽ ረፈድ ሲልም ወደ መኩሪያው ቢሮ አመራ ሠላም አደርክ ልጄ ሪፓርቱን ይዘህ መጣህ አለው መኩሪያው አይ ጋሼ ስለ ስራ ላወራህ አይደለም የመጣሁት ስለ ልጅህ ሰላም እንድናወራ ፈልጌ ነበር ቁጭ በልተቀመጥ ልጄ መኩሪያው ተስገበገበ ልጅዎት እራሷን አጥታለችእርስዎ ባያዩዋትም ሁሌ ታለቅሳለች ለማወቅ እንደቻልኩት ደግሞ ቤተሰብ ማጣቷ ነው እንዲህ የሚያደርጋት እኔምኮ ሳላስባት ውዬና አድሬ አላውቅም ግን እሷ ይቅር እንድትለኝ ብሞክርም አልሆንልህ አለኝለአይን ጠልታኛለች አለ መኩሪያው አይ አትጠላዎትምእኔ ጋር ያሰብኩት መፍትሄ አለኝ አለ ሚኪ መቀመጫውን እየተደገፈ ምንም ቢሆን አደርጋለሁንገረኝ እሥቲ ልጄ አንተ መላ አታጣም መኩሪያው የሚኪን ሀሳብ ለመስማት አሰፈሰፈ ጋሼ ሰላም ምን እንደምትፈልግ ጠንቅቄ አውቃለሁልትመረቅ የቀሯት ቀናቶች ዐ አይሞሉም ስለዚህ የምርቃቷ ቀን ትልቅ የመጽሀፍ መደብር አበርክቱላት በአዲስ ሞዴል መኪና ሰርፕራይዝ ብታደርጓት ለሷ ምኗም አይደል እሷን ለማስገረም ከፈለጉ አሁን ያልኩዎትን ያድርጉበዛ ላይ እርስዎ ከእንደዚህ አይነት ነገር እንድትርቅ ብዙ ጊዜ ተናግረዋታልም አግደዋታልም ስለዚህ ሀሳብዎን ቀይረው ይሄን ለሷ ማድረግዎ ለጥበበ ያለዎት አመለካከትዎ እንደተቀየረና ምን ያህል እንደሚወዷት ትረዳለች ይቅርም ትለዎታለች ሚኪ መፍትሄ ያለውን ሃሳብ አቀረበ ልጄ ጥሩ ሀሳብ ነው እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ ያደርጉት ጋሼ እርግጠ ኛ ነኝ ይሠራል ሚኪ ደስታና እፎይታ እየተሰማው ከቢሮ ለቆ ወጣ የምርቃቷ ቀን መኩሪያው በቦታው ተገኝቶ ባልጠበቀችውና ባልገመተችው ሁኔታ አስደመማት የሚኪ ሀሳብ መሆኑን ያላወቀችው ሠላም በደስታ ባህር ዋኘችአባቷንም ይቅር አለችው ወደ ቀድሞው ባህሪዋም ድፓድድድ ድፏድድፕድ ድድድ ድ ድ ድ ፏድድድድጽድቋ ዛሬ የድርጅቱ ሰራተኞች አመታዊ ክብረ በአል ነው። ሮቤል ሶደሬ ሆቴል ሪዞርት ቀድሟቸው ደርሷል አንተ ጉድ የሆንክ ልጅ መች ነው የምቀድምህ አለው ሚኪ ጭነት ስለያዝክ ነው እንጂ ትቀድመኝ ነበር አለው ሮቤል እየሳቀ አንተ እኔ ነኝ ጭነት አለችው ሠላም የቀልዷን አይኗን እያጉረጠረጠች ካካካካ ወዶ ነው እንዲህ ያማረብሽስትሽሞነሞኒ አይደል ሚኪም ቁጭ ብሎ ፋሽን ሲመርጥልሽ ነበር አንተ ተንኮለኛሚስቴንማ አትናገርብኝ እሷ ለወጉ ብላ እንጂ ባትበጃጅም ውብ አድርጎ ነው የፈጠራት ሚኪ ጉንሟን ሳማት ባልና ሚስት ተባበራችሁብኝኮይሄ የ አይደለም አለ ሮቤል በድጋሚ እየሳቀ አጋዥ መፈለግ ነዋሮቤልዬ ሂዊን ጠበቅ አርጋት አለው ሚኪ ሰላምና ሚኪ ሮቤል እንዲጠብቃቸው ነግረውት ክፍል ለመያዝና የያዙትንም ቦርሳ ለማስቀመጥ ባለበት ጥለውት ሚኪ እቃዎቹን ቦታ ካስያዘ በሁዋላ በመስኮቱ አሻግሮ አይኑን ጀንበር ወደንተሰራፋበት የሶደሬ ሀይቅ ላከ ሶደሬ መንፈስን ያድሳል። እያንዳንዱ ሆቴል ላይ የአባቴ ስም በትልቁ እንዲጻፍ አደርጋለሁ ያኔ ነው የአባቴ ነፍስ ሰላም የምታገኘው አላቸው እየሠራን ያለነው አንዱም ለሠ ነው ግን እንዴት አለችው ሂዊ እሁን ለኔ ተይው ሂዊ ሠርፕራይዝ ነው የማደርጋችሁ ሂዊ ሌላም ጥያቄ ልትሠነዝር ሥትል ኮምፒውተሩ ላይ መኩሪያው ወደ ቤት ሲገባ ሚኪ ተመለከተ ሠዎች እዩ መኩሪያው እየገባ ነው በማለት አነቃቸው ስድስት አይኖች ኮምፒውሩ ላይ ድጋሜ አፈጠጡ ልጅቷን አዘጋጃችሁዋት አለ መኩሪያው አዎ ጌታዬ ግን ልጅቷ ለምን እንደመጣች የገባት አልመሰለኝምእውነት ለቤት ሠራተኝነት ልንቀጥራት መስሏታል መሰል እሥካሁን ቤት እያጸዳች ነው እንተ ምንም የማይገባቸው አሥቸጋሪዎች ናቸውእንዳታመጣብኝ አላልኩህም አለው መኩሪያው ቆጣ ብሎ አዎ ብለዋል ጌታዬ ግን እቺ የምትወደዋት አይነት ነች አመት ቢሆናት ነውገና ያልተነካካች ናት አለው ሠውዬው እየተቅለሰለሰ ይሄኔ መኩሪያው ፊቱ ፈገግ አለ ቀድመህ እንደዛ አትለኝም ነበርእሸት ናት ማለት ነውአንተኮ አንበሳ ነህ የምፈልገውን ታውቃለህ መኩሪያው ሰውዬውን አሞጋገሠው ለመሆኑ ከየት ነው ያመጣችሁዋት መኩሪያው ጠየቀ ከዚሁ ከአዲስ አበባ ነው ጌታዬ አውቶብስ ተራ አከባቢ የወዳዳቁ አትክልቶችን ለመሸጥ በጠዋት ዘርግታ ነው ያገኘናት ጥሩ ሥራ ነውበል እሺ ሂድና እረፍት ለማድረግ ሞክር አመሠግናለሁ ጌታዬ ሠውዬ ብቻቸውን ጥሏቸው ወጣ መኩሪያው ስጋ እንዳየ ውሻ እየጎመጀ ልጅቷ ወዳለችበት ኪችን ክፍል አመራ። እናንተ ካልረዳችሁኝም ብቻዬን እሄዳለሁ አለ ሚኪ ሽጉጡን አቀባብሎ በሽንጡ እየሻጠ ሮቤልና ሂዊ እንዳይሄድ ለሁለት ጥፍንግ አድርገው ያዙት ልቀቁኝ ልሂድበትገናኮ አንድ ፍሬ ልጅ ናት ሚኪ እረጋ በል ቦታው እሩቅ ነውአሁን ብንሄድም ይረፍድብናልእሥክንደርሥ መኩሪያው ሥራውን ይጨርሳልስለዚህ ለመሞት ካልሆነ መሄድ የለብንም አለው ሮቤል ሚኪ ለዚህች ልጅ አልደረሥንላትም ለሚቀጥሉትሥ ልትደርሥላቸው አትፈልግም መኩሪያውን እሥር ቤት እንዲበሰብስ የሚያደርግልንን መረጃ ይሄው ኮምፒውተሩ እየቀዳው ነውመኩሪያው አልቆለታልእቺ ልጅ ግፍ የተፈጸመባት የመጨረሻዋ ትሆናለችከሄድን ግን ሁሉንም ነገር ታበላሸዋለህ እዛ ግቢ ብንገባ ምን የሚፈጠር ይመሥለሀል ሁላችንንም ያስገድለናልቅጂውም ዋጋ ያጣል አለችው ሂዊ የሮቤልን ሀሳብ በመደገፍ ግንኮ አለ ሚኪ ምንም ግን የለም ተቀመጥ አሉና ወንበር ላይ አሥቀመጡት ሚኪም ትንሽ ተረጋጋለመሄድ ያሰበውንም ተወው እሺ ሀሳቤን ቀይሬያለሁእናንተ እንዳላችሁ ሽጉጡን ለሮቤል አሥረከበው ግን ከዚህ በሁዋላ በኮምፒውተሩ ስክሪን ላይ የሚታየውን የመኩሪያውን እንስሳነትና የልጅቷን ስቃይ የሚከታተልበት አቅም ስላልነበረው ውጪ ልሁን ብሏቸው በሩን ከፍቶ ወጣ ሮቤል ሂዊን እንድትከተለው በምልክት ነገራት ሮቤል የድምጽ መቅጃውም ሆነ ካሜራዎቹ በትክክል ስራቸውን እየሠሩ መሆኑን ካረጋገጠ በሁዋላ ከመቀመጫው ተነስቶ ሚኪና ሂዊን አያቸው ሁለቱም በረዳው ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠው ፊት ለፊታቸውን እያዩ ፍዝዝ ብለዋልምንም አይነት ንግግር በመካከላቸው የለም ከአይናቸው ግን ንጹህ እንባ እየፈለቀ በጉንጫቸው ላይ ይፈሳልአባይ ኢትዮጵያን አቋርጦ ግብጽና ሱዳንን እንደሚያካልልው የእነሠም እንባ ከገደብ አልፎ ደረታቸውን አበስብሶታል ሮቤል በሩን መለስ አደረገና ተቀላቀላቸው በቀልና ፍንጥርጣሪው ሆክፍል ዶድርሰት በሸረፈዲን የእናቱ ልጅ እንደነጋለት ሚኪ ቢሮ ገብቶ ከጥቂት ቀን በፊት ያዘጋጃቸውን ሰነዶች ማስተካከል ያዘ። አለ መኩሪያው መነጸሩን ከፍ ዝቅ እያደረገ አዲስ ምርቶችን ከሚያቀርብልን ድርጅት ጋር የተዋዋልነው ውል ነውእርስዎ ለአንድ ወር ስለሚቆዩ ስራው መጓተት የለበትም ብዬ ነው ሳይሄዱ በፊት ቀድሜ ላስፈርመዎት የመጣሁት አንበሳኮ ነህ የኔ ልጅምነው እንዳንተ አይነቱ ታታሪ ድርጅቴ ውስጥ ሶስት አራት ቢሆንልኝስጠኝ ወረቀቱን ልጄ አለው መኩሪያው በመደሰት ሚኪ ወረቀቱን አቀበለውና መኩሪያው ሳያነብ እንዲፈርም ለአምላኩ ጸሎት ማድረስ ጀመረ መኩሪያው ወረቀቶቹን እየገለጠ ያለምንም ጥርጣሬ ይፈርማልሚኪ ሳቁ ሊያመልጠው ምንም አልቀረውም መኩሪያው ሁሉም ወረቀቶች ላይ ፈርሞ አቀበለው መልካም ጉዞ አለው ሚኪ ለመውጣት በሩን እየከፈተ አመሰግናለሁ ቆይ ልጄ አንዴ አለው መኩሪያው ሚኪ ፊቱን መለሰ ልጄ የውክልና ወረቀት ስላስገባሁ እሥክመጣ ወክለኸኝ ድርጅቱን ትቆ ጣጠርልኛለህማንኛውንም ነገር ለማከናወን እኔ አላስፈልግህም በራስህ ማድረግ ትችላለህ አለው መኩሪያው አያስቡ ጋሼ እርሥዎ እንዳዘዙ ሚኪ ቢሮውን ለቆ ወደ እራሱ ቢሮ ገባና ከውሥጥ ቆለፈው ተሽከርካሪው ወንበር ላይ ተቀምጦ ዝም ብሎ ይስቅ ጀመር ካካካካ ብቻውንም ያወራል። ሚኪ እነ ሮቤል ጋር በማምራት ልጅቷ እንዴት ናት አላቸው የማንሾካሾክ ያህል ደህና ትሆናለች ብዬ አሥባለሁ አለው ሮቤል ምን ማለት ነው ይሄ ለህይወቷ ያሰጋታል እንዴ ሚኪ በድጋሜ ጠየቀ አናውቅም ዶክተሩ መጥቶ ምንም አላላንም ሂዊ መለሰችለት ምንድነው የያዝከው ወረቀት አለው ሮቤል ሂዊ ሮቢአደረኩት አላቸው ሚኪ ገለጥ አድርጎ እያሳያቸው በቃ ቤት ስንደርስ በዝርዝር እናወራበታለን። ህይወቴን እሰጥሻለሁ ያልከኝ እያስመሠልክ ነበርየእናቴ ምትክ ነሽ ያልከኝስ ሁሉም ነገር ድራማ ነበር ቅንጣት ያክል አታፈቅረኝማ የቀረብከኝና ያ ሁሉ አጋጣሚ አቅደህበት ነው አይደል ሠላሜ አባትሽ ጋር ባለኝ ጉዳይ አንቺን አልተጠቀምኩብሽም እመኝኝ ሁሉም ነገር እውነት ነው ከልቤ አፈቅርሻለሁ ሠላሜ አላት አሁንም ታስመስላለህ እንዴ ሚኪ ተው ይብቃህ ከዚህ በላይ አትጉዳኝእኔኮ ካንተ ውጭ አለም የለኝም ነበርአንተ ጋር ስሆን ብቻ ነበር የዚህች ምድር ጣፋጭ ነገሮች የሚታዩኝ ነገር ግን ህልም ውስጥ ነበርኩ ማለት ነው ድንገት ስነቃ ፍቅረኛዬና የምመካበት ሠው የአባቴ ጠላት ሆኖ አገኘሁት አለችው እንባዋ አለቅጥ እየፈሰሰ ሠላም አባትሽ ምን ያህል አውሬ እንደሆነ ስታውቂ ያልሽው በሙሉ ይጸጽትሻል አላት በጣቱ እየጠቆመ እረ ምኑ እፍርታም ነህካንተ በላይ አውሬ የትም አይገኝምአባቴን አውቀዋለሁ በጣም ጥሩ ሠው አንተን ግን ጭርሱኑ አላውቅህም የለየልህ ውሸታም ነህ አለችው እየተንዘፈዘፈች ሠላሜ መኩሪያው ጥሩ ሠው ነው ስትይ ሠማሁ ልበል ሚኪ ንዴቱ ከቁጥጥሩ ውጪ ሆነበትየማታውቀው ሚኪ ሆነባት ሠላም ተሳስተሻል አዎ የአባትሽ ጠላት ነኝመኩሪያውን እሥከመጨረሻው በቁሙ ብቀብረው እንኳን ውስጤ ያለው ንዴት አይወጣልኝም ምክንያቱም አባትሽ ልጅነቴን ነጥቆኛልደሥታዬን ወስዶብኛልእድገቴን አቀጭጮብኛልቤተሠቤን አፈራርሶታልከ አመቴ ጀምሮ አባትሽ በህልሜ እየመጣ ሲያስደነግጠኝና ሲያሸብረኝ ነው እዚህ የደረስኩትተይኝ አትቀስቅሽብኝ ተይኝ አላት ከቤቱ በላህ እየጮኸሚኪ ሲናገር መላ ሰውነቱ አብሮት ይጨፍር ነበር ሠላም እንባዋን እያዘነበች ቦርሳዋን አንጠልጥላ ለመውጣት ወደ በሩ ሄደች በሩን ከፈተችና ቆመች ሚኪ አለችው ምንም መልስ ሳይሰጣት ጀርባውን እንዳዞረና እጆቹን ሽንጡ ላይ እንዳደረገ ወዲያ ወዲህ ይንጎራደዳል ሚኪ አባቴን ለመበቀል እኔን ቀርበህ እንዲህ ልቤን ከምታቆስለው እንደ መካሻ ብታግተኝና ሽጉጥ ብትደግንብኝ ይሻለኝ ነበርእዚህ ጋር አብቅቷል የህልም ሩጫችን አለችውና በእንባ የጨቀየውን ፊቷን እየጠራረገች በሩጫ ወደ መኪናዋ ተፈተለከች ጃጃቿቋፏጽ ሚኪና ሰላም ከተለያዩ አንድ ሳምንት ሞላቸውሁለቱም ክፉኛ ተጎድተዋልልባቸው ቆስሏልሚኪ ብዙ ጊዜ ስልክ ቢደውልም ሆነ መልክት ቢልክላትም ከሠላም የሚመጣ ምንም አይነት መልስ የለምሁለቱም የእለት ተእለት ክንውናቸውን እርግፍ አድርገው ትተውታል ተቀምጠው ማልቀስ ያሳላፉትን የፍቅር ጊዜያት በሙዚቃ እየቀላቀሉ መከለስና ቃል የተገባቧቸውን ነገሮች እያሰቡ መተከዝ የዘወትር ሥራቸው ሆኗል ሚኪ የሠላምን ያህል ባይሆንም ተጎሳቁሏል እነ ሂዊን እራሱ ዘግቷቸው ብቻውን መሆንን መርጧልሠላም ደግሞ ነገሮች በፍጥነት ተደበላልቀውባት ተሽመድምዳለች እቺን አለም አምር ራ ጠልታታለችየሚያፈቅሩትና የሚያምኑት ሠው ድንገት ሽፋኑ ተጋልጦ ሌላ አይነት ሠው ሁኖ ሲገኝ ያማልበዛ ላይ ሰላም የውስጧን አውጥታ የምትተነፍስለት ይሄ ነው የምትለው ሰው የላትምሁሌ እንደምታደርገው ከማስታወሻዋ ጋር ታወራለችሁሉንም ነገር ልቅም አድርጋ ለወረቀቷ ትነግረዋለችአንዳንዴ እየጻፈች የምትገልጸው ነገር ሲከብዳትና ያለፈው ጥሩ ትውስታዋ ፊቷ ላይ ድቅን ሲልባት ስቃዩዋን ያብሰዋል እንባዋ ከየትኛው ግድብ አልፎ እንደመጣ ግልጽ ባይሆንም ወረቀቷ ላይ ዝርግፍ ይልና የጻፈችውን ያበላሽባታልበእራሷ ትናደድና ወረቀቱን ቀዳ ጥላ ማስታወሻዋን ትዘጋና ጋደም ትላለች ዳሩ እንቅልፍ በአይኗ ዝር ባይልምአእምሮዋ ከሚሯሯጠው ሀሳቧ እረፍት ባያደርግም ወገቧን ታሳርፈዋለች። አለቻት ሠላም በትህትና ንግግሯን በማከታተል አይ ይቅርብኝ ወደ ጉዳይ ብገባ ይሻላል አለች ሂዊ በረዥሙ ተንፍሳ አየር ለመውሰድ እየሞከረች እሺ ቀጥይ እየሠማሁሽ ነው ሰላም ሚኪ ከልቡ ያፈቅርሻል በአንቺ አይደራደርም በምንም ሊቀይርሽ አይችልም አለቻት ሂዊ ለመጀመር ያክል ስለ እናትሽ ማወቅ ያለብሽ ነገር አለ ያልሽኝ መሥሎኝ ሠላም ከመቀመጫዋ ብድግ አለች ተቀመጭ ሠላም ሁሉንም ነገር እነግርሻለሁየምነግርሽ ነገር ላይዋጥልሽ ይችላል ግን እውነት ብቻ ነው አለቻት ሂዊ ወሬዋን እንዳታሥቆማት ጠንከር ብላ እሺ ምንድነውተረት ተረቱን አቁመሽ ለምን ፍሬ ሀሳቡን አትነግሪኝም ሚኪ ትክክለኛ ስሙ ሮቤል ነውየመጣው ከጅማ ነውአንቺ ጋር ያገናኛችሁ አጋጣሚ እንጂ አሥቦበት አልነበረምአባትሽ መንገድ ዘግቶ እሥኪያሥቆማችሁ ድረስ ምንም ስላንቺ አባት የሚያውቀው ነገር አልነበረም። ግን እንዴት ህጻናቶችን ሲደፍርና ሲያበላሽ ማወቅ ተሣነኝሂዊዬ ይሄን አረመኔ ነው እንዴ እንደ መላእክ ስቆጥረው የነበረውይሄን ሠው ነው እንዴ እድሜዬን በሙሉ አባ እያልኩ ስጠራው የነበረው ሠላም እራሷን መቆጣጠር አቃታት አይዞሽ ሠላሜ ይሄ ላንቺ በጣም እንደሚከብድሽ አውቃለሁ ግን መረጋጋት አለብሽመጠንከር አለብሽ አለቻት ሂዊ ወደ እራሷ አስጠግታ እያቀፈቻት ሂዊ ያማልእዚህ ጋር በጣም ያማል አለች ሠላም እጂን ደረቷ ላይ አድርጋ የልቧን መታመም በምልክት እያሳየች ተነሽ አሁን እንሂድ አለቻት ሂዊ ፍላሹን ከኮምፒውተሩ ላይ እየነቀለች የትም መሄድ አልፈልግም ሠላም ብቻዋን መሆን እንደምትፈልግ ገለጸችላት አይ ብቻሽን መሆኑ ይበልጥ ይረብሽሻልእህትሽን ላሳይሽ ነው ከሷ ጋር ስትጫወቺ ትረሺዋለሽ አለቻት ሂዊ በግድ እጂን እየጎተተች እያስነሳቻት ቋጽድድድፏድ ሮቤል የጫማ ድምጽ ሲሰማ ከቢሮው ወጥቶ አንገቱን በማስገግ ለማየት ሞከረሂዊና ሰላም ወደ ውጭ እየወጡ ነው ወደ ውስጥ ተመለሰና ፍለጋውን በነጻነት ማካሄድ ጀመረ አንተ ቆሻሻ የሆንክ ሰውዬ አገኝሀለሁየት ነው የደበቅከው ብቻውን እያወራ ቢሮውን አተረማመሠውግን ምንም ሊያገኝ አልቻለም እእእህህህህ ይሄ የማይረባ አለና በንዴት የብእር ማስቀመጫውን በእጁ ገፍቶ ከጠረጴዛው ላይ ወረወረው ብዛት ያላቸው ብእሮችም ከማስቀመጫው ወደ መሬት ተደፉ ሮቤል የተበተኑት ብእሮች ላይ አይኑን ሲልክ ከመካከላቸው ለየት ያለ ብእር ተመለከተአነሳውና በእጁ ያዘው እንዴ አለ ሮቤል አንዳች ነገር እንዳየ ሮቤል ብእሩ ላይ ጉጠት ነገር ተመልክቶ ነው ሳይታወቀው የጮኸው ጉጠቷን ሲጫናት የብእሩ ጫፍ ተሽከረከረና ወደ ላይ ሌላ ድራብ ሰራጫፉን ሲጫነው የሆነ ክፍል ቀስ እያለ ተበረገደ ፐፐፐፐ መኩሪያው እንደዚህ ብልጥ አትመሥለኝም ነበርቻይኒሽ ስታይል ነው ኑሮህ ሮቤል የፌዝ ጭብጨባ አጨበጨበ አዝናለሁ መኩሪያው እግዛብሄር ከጎናችን ስለነበር በስተመጨረሻ አሸነፍንህ አለና ወደተከፈተው ሚስጥራዊ ክፍል ገባ ሂዊና ሰላም ቤት ደርሰው ማራማዊትን እያጫወቱ ነው። መተቃቀፉን ተቃቀፉ ግን የምን መላቀስ ነውዛሬ መልሰን አንድ ሆነናልእዩ ሁላችንም አብረን ነን ስለዚህ ልንደሠት ነው የሚገባው አላቸው ሮቤል ሂዊና ሚኪም ተላቀቁ የኔ ጌታ ተጎሳቅለህብኛልኮጸጉርህም ተንጨባሯልአንተን ሳጸዳ መዋሌ ነው ሰላም ሳቅ አለችና ደግፋው ሸዋር ቤት አስገባችው የለበሰውን ልብስ አወላልቃ መለ መላውን አሥቀረችውና በአናቱ ውሃውን ለቀቀችበትቺ እያለ የሚወርደው ውሃ እሥኪለምደው ሚኪን አንቀጠቀጠው እጅና እግሩን አጣጥፎ እንደ ህጻን ልጅ ኩርምት ብሎ ተቀመጠ ሠላም ሳቋ መጣባት የኔ ሠካራም ቀዘቀዘህ አለችው ቁልቁል እያየችው አዎ ሠላሜ አላት ጥርሱን እያፋጨ ትለምደዋለህ ቅዝቃዜው ሥካርህን ያባራዋል አለችውና ሳሙና አነሳችከጸጉሩ ጀምራ እሥከ እግር ጥፍሩ ድረስ በአረፋው አዳረሰችው እጂ ላይ ባለው ሣሙና ሠውነቱን ደጋግማ ከፈተገችው በሁዋላ ንጹህ መሆኑን ስታረጋግጥ መልሳ ቀለል ባለ ውሃ አለቀለቀችው ጸጉሩን አስተካክላ አበጠረችና ሠውነቱን አደራርቃ በፎጣ ጠቀለለችው ደግፋው ሻወሩን ለቃ ስትወጣ ሮቤል ሶፋው ላይ ተቀምጦ ቲቪ እያየ ነውካለምንም ተቀናቃኝ ሪሞቱን በእጁ ይዞ ያሻውን እየቀያየረ ያያልሂዊ ደግሞ የተመሰቃቀለውን ቤት ለማስተካከል ደፋ ቀና ትላለች ሠላም ሚኪን መኝታ ክፍሉ ወስዳው አስተኛችውየኔ ፍቅር አይንህን ጨፍነህ ለማረፍ ሞክርእኔ ሂዊን በሥራ ላግዛት አለችውና ልትወጣ ስትል እጂን ያዛት ሰላሜ አትሂጅብኝአብረሽኝ ሁሺ አላት እዛው ብርድ ልብሱን እንደለበሠ የትም አልሄድብህምኮ ስካሩ ሙሉ በሙሉ እንዲለቅህ ቢያንሥ ለግማሽ ሠአት መተኛት ስላለብህ ነው ሠላም ግንባሩን ሳመችውና ወደ ሳሎን ተመለሰች ቤት ማጸዳዳቱ ላይ ለመሳተፍ ብትሞክርም ሂዊ አልቀመስ አለቻትእኔ እበቃለሁ በማለት እንዳትሠራ ከለከለቻት ሠላምም ኪችን በመግባት ለአራት ሰው የሚበቃ ምግብ አዘጋጀች። ሚኪ ከግድግዳ ጋር ገፍትሮ አጋጨው መኩሪያው በርሊን ሆኖ ሳለ ነው እየተካሄደ ያለውን ነገር ጆሮ ጠቢው ደውሎ የነገረውባለስልጣኖቹ እንደታሰሩና የሆቴሎቹ ስሞች አባተ በሚል መጠሪያ እንደተቀየሩ ሲሰማ ነው የድሮው ትዝታው ብልጭ ያለበትየሚኪን ማንነት ከተገነዘበ በሁዋላ ወዲያው ከጀርመን ተመለሰና ከህግ አካላት እራሱን እየሸሸገ ወደ ጅማ አመራከዛም እናቱን ጠልፎ በሚኪ ደካማ ጎን መጣበት አንተ ልጅ ተረጋጋ እንጂእኔን ብትገለኝ ወይም ለፓሊስ ብታሥረክበኝ የእናትህን እሥትንፋስ ለማቋረጥ ሠከንዶችን የማይጠብቅ ታማኝ ሠው አለኝ አለው መኩሪያው እየሳቀና ከወደቀበት እየተነሳ ሚኪ እራሱን አረጋጋ መኩሪያው ፊት ላይ ለማረፍ የተወጣጠሩት ጡንቻዎቹም ረገብ አሉቆሞ ግንባሩን ማሸት ጀመረ ሥንት የለፋሁለትን ሀብት በቀላሉ ሠጥቼህ እዛው የምቀር መስሎህ ነበርካካካ መኩሪያው በድጋሜ ሳቀበት አንተ ቆሻሻ ሽማግሌ ንብረቱ የአባቴ ነው አለው ሚኪ ነበር ግን አሁን የኔ ነውይልቅ እናትህን ለማትረፍ የምልህን አድርግሙሉ ሀብቱን ትመልስልኛለህ ቦታውን ቴክስት አደርግልሃለሁከአንድ ሰአት በሁዋላ ብቻህን መጥተህ እናትህን አድናት እሷ ብቻ ናት የቀረችህ ቤተሰብ ብሎት ፊቱን መልሶ ሸፋፈነና ጎምለል ጎምለል እያለ ቢሮውን ለቆለት ወጣ ሰላምና ሂዊ ማራማዊትን በመኪና እያንሸራሸሯት ነው አሪፍ የሚባል ጊዜ እያሳለፉም ነውህጻን ማራማዊት አይታ የማታውቀውን አለም አንድ ባንድ በግርምትና በመደነቅ ታያለችበጣም እንደተደሠተች በየደቂቃው የምትሥቀው ሳቋ የሂዊ ስልክ በድንገት ጮኸበቶሎ አነሳችው ሄሎ ሚኪ ሂዊ መኩሪያው እናቴን አግቷታልምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅምአሁን እንድመጣ በነገረኝ መሠረት ወደ ቦታው እየሄድኩ ነው። ምን ቦታው የት ነው ሂዊ አመዷ ቡን አለ ወደ አዳማ የሚሄደውን መሥመር ይዘህ ሥትመጣ በጅምር ላይ የሚገኝ ፋብሪካ አለእዛ እንድገኝ ነው የነገረኝቻው በቃ መፍጠን አለብኝ ሚኪ ስልኩን ጆሯዋ ላይ ዘጋባት ምንድነው ሂዊምን ተፈጥሮ ነው ሠላም ጠየቀቻት አባትሽ የሚኪን እናት ይዚታልእናም ሚኪ ወደ ቦታው እየሄደ ነው ሠላም በድንጋጤ መኪናውን ሲጢጥ አድርጋ አቆመችው ምን ጉድ ነው ሂዊመኩሪያውኮ መመለሻው ቀን አልደረሠም አለች ሠላም አዎ እኔም ምንም አልገባኝም ሂዊ ተናገረች የት ነው ቦታው። ለሰውዬው ስጠው የያዝከውን አለ መኩሪያው ምንም ማድረግ ያልቻለው ሚኪ ፋይሉን ለሠውዬው አሥረከበ የፈለከውን አግኝተሀልእሺ አሁን ልቀቃት መኩሪያው ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ልክ መሆኑን ካጤነ በሁዋላ ሚኪ ላይ ሽጉጡን አነጣጠረበት እባክህ ተው መኩሪያው ልጄን አትግደለውያለኝ እው ብቻ ነው ወሮ የሺወርቅ እያለቀሠች ለመነችው አይሆንም ይሄ ቤተሠብ እሥካለ ድረሥ ሠላሜን አላገኝምእንደጀመርኩት እጨርሰዋለሁልጅ እዮብ ገና ድሮ ነበር አንተን መግደል የነበረብኝ አለና የሽጉጡን መጠበቂያ እንደከፈተው መኩሪያው ተው እንዳታደርገው ሠላም እየለፈለፈችና እየጮኸች ሚኪን በሠውነቷ ከልላ ጥልቅ አለች ሠላሜ እዚህ ምን ትሠሪያለሽዘወር በይ አሁን ይሄ ባለጌ አምቼ ቤቴ ባስገባውና አንድ ማድ ባቀርበው እጄን ነከሰኝሙሉ ሀብቴን በራው ሥም አዞረው አላት መኩሪያው ሽጉጡን ሳያወርድ መኩሪያው የሠራሃውን ሁሉ ሀጢያት አውቂያለሁአንተ በሰው አምሳል የተሠራህ ዲያቢሎስ ነህትንሽ እንኳን እንጥፍጣፊ እዝነት የሌለህ አውሬ ነህአሁን አንተ ለሠራኸው ሁሉ ክፋት የምትከፍልበት ጊዜ ነው እንጂ ሌላ ወንጀል የምትሠራበት አይደለም።