Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
መንዝህ ይጫ ሳሎ ምድርሽ መንዝህ ጭማ ከማፉድ እስከሮቢት ዳር እስከ ዶቃቂት ከተማ ከሾላ ሜዳ እስከዓዋዲ ከጣርማበር አስከአራድማ ከገዝፈገፍ እስካንጋቻ ከይፋት እስከወላስማ ከአውሳ አብዬስ ግሼን ማዶ በደጋሸ አናት ላይ በርዶ ጐንሽ ቡልጋ ተገድግዶ ፍርኩታ ንዳድ ተወርዶ በከስም በረሃሽ ነዶ ከሸንኮራ እስከምንጃር አንኮበር የመሄዴ አገር ከመረሬ አፋፍ መልሶ እለከጨበሬ ምሑይ ዳር ከወግዳ ከነባሮ አገር ከታላቅ አምባ ነጭ ሣር አንኮበር የአለት ላይ አጥናፍ ስውር ምድር የአድማሳት ጫፍ የኮረብታ ዲብ ያድባር ዛፍ እንደራዕይ በክንፍ አርካብ እንደጽላት በአየር ድባብ አቀበት የደመና አዘል መቀመቅ ዝንጀሮ ገደል የመዲኖች ጭፍግ ጠስል አንኮበር የአምባ ላይ አዝ። አድማስፈጠር ኬላሰበር አንኮበር የአምሃየስ በር። የዓይንሽ ብሌን ያ ብረቱ ያ የመለኮት ሰለቱ ካለማወቄ ያገደኝ ክምድጃ እሳት ያፈለኝ የእጅሽ ድባብ የሙቀቱ የፍቅርሽ ንቃት ፍጥነቱ መዳፍ ዳስሰሳሽ ድቀቱ ተግብር ያለ ሥጋቱ ክውድቀት አፋፍ ያቀፈኝ ክጋሬጣ የጋረደኝ ያ እጅሸ የልጅነት ክንፌ ጣትሸ የድሆሽ መርገፌ አዳዬ መዳፍሽ ዘርፌ የትውልድ እምአእላፌ የዓለም መሻገሪያ ጠንፌ ቀን ማገረሽ አንቺ እጣዬ ጃጀሽ አሉኝ አዴ አዳዬ። ዶርዜ ሠፈር ሰቆቃው ጴጥሮስ ከጴጥሮስ ያቺን ሰዓት ቴአትር አየ ምነው እመ ብርሃን እረሳሻት። አስርጪብኝ የእምነት ቀንጃ ለሥጋቴ አጣማጅ አቻ ሰጭንቀቴመቀነቻ አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሂ እሸሸግበት ጥግ አጣሁ እምፀናበት ልብ አጣሁ ቀበና እንቅልፍ ነው እሚያሰወሰድህ። ከዋክብቱ እንደችቦ በነበልባል ወርቀ ዘቦ ከፅንፍ ፅንፍ አውለብልቦ ደመራው እየተመመ እየፋመ እየጋመ ደመና እንደንዳድ ሲነድ መንጸባርቅ ሰደድ ሲወርድ በራሪ ኮከብ ተኩሶ በአድማሳት እሳት ለኩሶ ይኸ እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዓይኑ የሰለለ ለማይ ጨለማ ነው እንጂ እሳት እኮ እደሰም ኣለ ያልታደለ ይቅር ብቻ አንናገርም እኔና እንቺ አንወያይም ለውይይት አልታደልንም ራሪ እንዲያው ዝም ዝም። አበባ አንሆን ወይም እሳት ተጠምደን በምኞት ቅጣት ሰመመን ባጫረው መዓት ዕድሜአችንን እንዳማጥናት አሳት አንሆን ወይ አበባ በሕቅ እንቅ ስንባባ ባክነች ልጅነታችን እየቃተትን ሰናነባ ሳንፈጠር በሞትንባት ሳናብብ በረገፍንባት ሳንጠና ባረጀንባት አበባ ወይንም እሳት መሆኑን ብቻ አጣንባት። አሰቀመጡህ ብለው አሉኝ በል እሰቲ ይኸ አማርኛ ነው። እኔማ አሳመንኳቸውም በዚህ በቋንቋ ጋጠወጥ ለማጥላላት ለሟሸሟጠጥ የሉሉ አባትየሉሉ እናት ብለን ሰስንቆለማመጥ ፍቅራችንን ለማንጓጠጥ ትዳራችን እንዲናወጥ ልጃችን ቅሰሙ እንዲቆረጥ የተደረገ ዘዴ ነው ቀንተው የሠሩት መበለጥ እንጂ ተቀመጥክስ ቢሉኝሠምንህ ምኗ ላይ ሊቀመጥ። እነሱራፌል ኪሩቤል በእሳት ሠረገላ ወርደው በመለኮት ብርሃን አቅፈው በአክናፋት አኮቴት ቀዝፈው በኅብር አዝለው አንከባክበው ሰባቱን ስማያት መጥቀው ሽቅብ ይዘው አዎ ትዝታኮ ሰካ በሥጋዌ ልቡሰ ሕመም ሳትወሰን ሳትለካ በምድር ሰሜት ሳትነካ በስው መውደድ ሳትረካ ቅዱስ መንፈስ ያላበሳት ብቁ ናት ለካስ ፍጹም ናት የስው እሳት እማይሞቃት። መስል ወራሽ ተካሁ ይበል የዘር ቅርሱን የሚያስፋፋ ድል የሚመታ ሰተቴ በነገር በአሸሙር ልፈፋ በአግቦ እንደቅኔ ዘረፋ በሽሙጥ ባፍ ዘለፋ ይበል እንጂ እኔም ወንድ ወስድኩ ባፍ እሚበልጠኝ አደረስኩ በነገር እሚጥል ፈጠርኩ ያባት ልጅ ያዘው ቅምጥል የደሙ ትክል የወኔው ሸል ፈጠርኩ ይበል ቀበዝባዛ እንደእዙሪት እሚፈትል በምላስ ቀስት አነጣጥሮ ቂም በልቦና እሚተክል ደም በደም እሚያስተጣጥብ ወገን ከወገን እሚያክል እንደሥራሥር ደብተራ ላንቃው መርዝ እሚያቀላቅል ውጋቱ ዘር እሚያጣጥል እንደጦስ እሚደበልል እንደዛር ውላጅ አሽሮ ያጥንት ስባሪ አቅሮ አንደበቱ እንደወስፈንጥር ሾሎ ባስተናግር ቅጠል አፈጊንጥ ያብሾ ጡት ልጅ ጥላ ወጊ ቀትረፍልፈል አለሳልሶ እንደወላፈን አሸልቦ ሲንበለበል በከንፈር ፈግታ ከንፎ ባፉ ጥላወግቶ እሚገል ደምመራዥ ልጅ ያፋፍ ላይ ድጥ መስክ መሳይ ያሽሙር ደስል የወሬ ማንፈሻ ጋሻ ደርሼለት እሱን መሰል በተከስው እሚከተል አባቴስ ወንድ ወለድኩ ይበል ለተማሩ ለማይምሩ አፈሊቃውንት ሀ አዲሳባ ሐረር ሐረር የግንብአጥር ማኅደር ያባአደሬ ያባድር በር። በጥረት ጌራን ከታደግን ከእርካንዋም ከቶ ከታገድን ለብቻ የመኮራመት የዕድሜ ጥሻ ነው የለመድን። ተይ አንል አትሠወሪ ስሚ አንል በሕልም ጥሪ ወይ ፈጽመሽ አንል ቅሪ ፍለ ሳይግል ነው እሚነድ። ሞት ሳይሞቱት ነው እሚለመድ። ምኞት ናዳድጥ ነው ትጥቁ። የዕድሜ ብኩን ጣር ነው ሰንቁ። ጌራ የሕልምዓለም ደለል ትዝታሽ ሞልቶ ሲቆለል ሲቃ ነው እሜኮለኮል። ሌት በቅዥት ተሰትረን ቀኑን በስቀቀን ታንቀን ዕድሜእችን በምኞት ታጥፌ ፍቅር እንደዜ ነው እሚገል ኒኛ ስንቴ እንሙት ጌራ። ዕጣውን ለብቻው ቆርሶ ብቻውን ሰቀቀን ጐርሶ ብቻውን ጭለማ ለብሶ ገበናውን ሣግ ሸፍኖ ክብሩን በሰቆቃ አፍኖ ሌሊት የማታ ማታ ነው ሕቅ እንቁን እሚነጥበው ኤሎቼውን እሚረግፈው ከዓይኑ ብሌን ጣር ተመጦ ከአንጀቱ ሲቃ ተቆርጦ ደም አልሞ ፍም አምጦ ከአፅመወዙ እቶን ተፈልጦ እንደጠፈርብራቅ እምብርት እንደእሳተ ገሞራ ግት ርቅ ነው ወንድ ልጅ እንባው ደም ነው ፍም ነው እሚያነባው። ችሎ ውጦ ተጨብጦ ሰቀቀኑን በሆዱ አጥሮ በአንጀቱ ገበና ቀብሮ ውሎ ጭጭ እፍን ብሎ እንደደመና ተቋጥሮ ጣሩን ውጦ ተጣጥሮ በሲቃ ግት ተሰትሮ ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ ከቤተሰው ተደብቆ አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ ተሸሽጐ ተከናንቦ ተሸማቆ ተሸምቆ የብቻ ብቸኝነቱ የጭሰማ ልብሱ እስኪደርስ በዓይን አዋጅ ሃሞቱ እንዳይረክስ ቅስሙ በገበያ አንዳይፈስ ተገልሎ በእኩለሌት ወንድ ብቻውን ነው እሚያለትሰ። ዛ ጋርባ ጉራቻ አዘቦን ዳግም አየኋት ዓይን ማየት ነውና እሚያቅ የብርሃን ዕድሜ አዚሙ እስኪያልቅ ከአሥራ አራት ዓመት በኋላ ተመልሼ አዳመጥኳት እና ዛሬስ እንኳን አልኳት ያኔ ድምጺ ከሩቅ ነበር እንደሟች ሳል ሲል የሚለው የልሳን ሲቃ ጥላ ነው የክፉ ቀን የቅዙት ጣር ብዥ እልሙ ነው እሚታየው ያደባባይዋም ሳይ ጭጋግ የጥንብ አንሳ አክናፍ ብቻ ነው። እስቲ ገብርዬን መሰል ዘር ፍሬው ከቶ አይለመልምም። ያለፈ ጥረታችንን ሳስታምመው ትዝ ሲለኝ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው እሚቆጨኝ።
ማኅፀንሸ ጽዋው መረዘኝ ዘጠኝ ወር ያጠባኝ ገንቦ ጡትሽ የደም ወተት ዘንቦ ሆድሽ የቁስል ምጥ ታልቦ ባዳ ቅሪት ተመትሮብሽ የእንብርቴ እልባት ተስብሮ ደሜ በፋፋበት እትብት ገፊ ዲቃላ ተቋጥሮ በቃ እማማ እማማዬ መቀነቴ ገበናዬ በቃሁሽ አድባሬ መቅኔ ከእንግዲህስ ላንቺ መጥኔ እዬ ላንቺ አዬ ለኔ ጫቅላዬን ባዘለ እቅፍሽ ገፊ ጉግ ማንጉግ መፅነለሸ ጐምቱ ሾተላይ ማብቀልሽ አይሆንም እንጂ ከሆነሸ ካለልሽ ካዘለቀልሸ እግዚአብሔር ያሳድግልሽ አዎን ቃል ለምድር ለሰማይ ደኅና ዋይ በቃ ደኅና ዋይ ዓይኔ ዓይንሽንም አያይ ክፉም በጐም አናሰማ እንዲያው ደኅና ዋይ እማማ እናት ዓለም የስሜ አርማ የሕይወቴ ወዝ የዓይኔ ማማ እማትነፍጊ እማታቅማሚ እማታሳጪ እማታሟ እኔን በራበኝ በጠማኝ አብረሽኝ እምትጠሚ ጥቃቴን እምትጠቂ ቁስሌን እምትታመሚ ፍሥሃዬን ፈገግታዬን ሳቄን ብቻ እምታልሚ አንቺ እማማ አንቺ የነፍሴ ልብ ዓልማ የዓይኔ ማማ ምነው ጡትሽ ተጣረረኝ። ለኳስ አርበኛ አዴ አዳዬ አዴ አዳዬ እመምኔቴ የትውልድ መስታየቴ የዘመን ቅርሴ መክሊቴ የዕድሜ አንቀልባዬ ሞግዚቴ ቀን ማገረሽ አንቺ እጣዬ ጃጀሽ አሉኝ አዴ አዳዬ በሥጋትሽ ተንጠልጥዬ በአንገትሽ ማተብ ታዝዬ በዓይንሸ ጢሎሽ ተንጠልጥዬ በጮጮሽ ተሞካሽቼ በጉርሻሽ ውሽን ተብዬ በእንጐቻሽ ተከባክቤ በእንኮኮሽ ተደሳድዬ ካፍ ከወጣ አፋፍ ነው ሲባል ለካለሰ ነገር ይገለማል አዴ አዳዬ የአባዬ እናት ለምን ይሆን ያሉሽ አያትያ ባፍ ዝምድናሽን ሲያቀርቢት ስምሽን ሦስት እጥፍ ያራቁት። አዴ አዳዬ እመምኔቴ የትውልድ መሰታየቴ የዘመን ቅርሴ መከሲቴ የዕድሜ አንቀልባዬ ሞግዚቴ ቀን ማገረሽ አንቺ እጣዬ ጃጀሽ አሉኝ አዴ አዳዬ። ጊዜ የጊዜ ነው እንጂ አንቺ እኔ ነሽ እኔ አንቺ ነኝ ብልሽ ላንደበት ወግ በቀር እኔም አንቺም አንጠቀም ሕመሜን ሳትታመሚ ሕመምሽን ላልታመም የዘመን አጥር ክፍሎናል አውቀነዋል አንደለል ታድያን ጊዜ የጊዜ እንጂ ድሮም የዘለቄታ አደል እና የነገ ጥሪዬን ዛሬ በጥሪሽ አየሁት አዴ አዳዬ እመምኔቴ ጭንቄን በጭንቅሽ ለየሁት እንጂ ካንቺ አልክፈልም እኔ ቁሰልሽን አልቄስልም ጣርሽን አልጣጣርም በጉልበትሽ እንደጠናሁ አንቺ በጉልበቴ አትጠሂም በወዝሽ አንደለመለምኩ በወዜ አትለመልሚም ቁቤ ያንቺን መንጠቅ እንጂ ዕዳ መክፈሉን አያውቅም በጉርሻሽ መጥናቱንም በቀር መጠንጠኑን ከቶ አያይም አዴ አዳዬ ብቻሽን ነሽ ጣር እሚካፈልም የለሽ። ለኤድዋርዶ ሞንድላን ፀ ዳሬ ሰላ እሳት ወይ ኣበባ እና እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዓይኑን የታወረ እግረ ሕሊናው የከረረ ባሕረራሃላቡን ያልታደለ የውበት ዓይኑ የሰለለ ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ አበባ እኮ አደለም አለ። ከዋክብቱ እንደችቦ በነበልባል ወርቀ ዘቦ ከፅንፍ ፅንፍ አውስብልቦ ደመራው እየተመመ እየፋመ እየጋመ ደመና እንደ ንዳድ ሲነድ መንጸባርቅ ሰደድ ሲወርድ በራሪ ኮክብ ተኩሶ በአድማሳት እሳት ለኩሶ ይኸ እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዓይኑ የሰለለ ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ እሳት እኮ አደለም አለ ያልታደለ ይቅር ብቻ አንናገርም እኔና አንቺ አንወያይም ለውይይት አልታደልንም እንዲያው ዝም እንጂ ዝም ዝም። አበባ አንሆን ወይም እሳት ተጠምደን በምኞት ቅጣት ሰመመን ባጫረው መዓት ዕድሜአችንን እንዳማጥናት እሳት አንሆን ወይ አበባ በሕቅእንቅ ስንባባ ባከነች ልጅነታችን እየቃተትን ሰናነባ። ታድያን እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዓይኑን የታወረ እግረ ሕሊናው የከረረ ባሕረፃሳቡን ያልታደለ የውበት ዓይኑ የሰለለ ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ አበባ እኮ አደለም አለ። ያልታደለ ሌት ከዋክብቱ እንደፀደይ አጥለቅልቆን በቀይ አደይ ሰማዩ ሥጋጃ አጥልቆ ተሽለምልሞ እንጸባርቆ ፈክቶ እሸብርቆ ደምቆ በአዝመራ በአጥቢያ ዐፀድ ሰፍኖ የዓደይ አዝርእት ተከሽኖ በዕንቁጣጣሽ ሰብል ታጥኖ ኢዮሃ አበባዬ ሆኖ ጨረቃዋ ከቆባዋ ከሸልምልሚት እምቡጧ ጧ ብላ ከስንኮፈንዋ ተንዣርግጐ የእንኮይ ቡጧ ድንግል ጽጌረዳ ፈልቃ ፍልቅልቂት ድምቡል ቦቃ ተንሠራፍታ የአበባ ጮርቃ ታድያን ብሌኑ የጠጠረ ባሕረሃሳቡ የከረረ የውበት ዓይኑን የታወረ ልበሕሊናው የስሰለ አይ አበባ አይደለም አሰለ እይ እሳት አይደለም አለ ያልታደለ ሰማይ ጨለማ ነው እንጂ እሳት አደል ብሎ ካደ እቶን በዓይኑ እየነደደ። ከዋክብቱ እንደችቦ በነበልባል ወርቀ ዘቦ ከፅንፍ ፅንፍ አውለብልቦ ደመራው እየተመመ እየፋመ እየጋመ ደመና እንደንዳድ ሲነድ መንጸባርቅ ሰደድ ሲወርድ በራሪ ኮከብ ተኩሶ በአድማሳት እሳት ለኩሶ ይኸ እንደኔና እንዳንቺው የውበት ዓይኑ የሰለለ ለማይ ጨለማ ነው እንጂ እሳት እኮ እደሰም ኣለ ያልታደለ ይቅር ብቻ አንናገርም እኔና እንቺ አንወያይም ለውይይት አልታደልንም ራሪ እንዲያው ዝም እንዲያው ዝም ዝም። መስከረም መስቀል አደባባይ ጌራ ጌራ ነበልባል ዘለሳ እንደመንጸባርቅ ጥሳ ሽልም ሽፋልሽ ሲያጠሳ ጌራ የፈተና መከር የቁንጅና ራዕይ በር እድብተሽ እንዳረህ ደለል በልብ እሳት ለመዋለል ሰቀቀን እስኪዘነበል ጣር ለጣር ለመቀላቀል ድንገት ደርስሸ ለመንጣለል ጌራ የልጅነት ፍቅር ድብቅ የዕድሜ ልክ ምሥጢር አይሆንም እንጂ ቢሆንሽ ነፍሳችን ይኳረፍ እባክሽ። ጌራ ያረቀቀሽ የአምላከ ሥራ ጌራ የቁም ሕልም እንጀራ ጌራ የዲበቡዙሉ ጡብ የሕዋው ፈተና ክቡብ የመስኮት ቅጣት ዕቁብ ጌራ የሰቀቀን ጽዋ ዓይጥ በበሳ ነው ዳዋ እሚበራይ አሚሰዋ ብላን ብቻ ብላን ትቅር። ፍቺልን ጌራ ፍቺልን ስው አይከርምም ሕልም ጐርሶ በቅዣት ጠረንሽን ዳሰሶ በሽውታተስፋ ደርሶ ቀን በቁሙ ካልጸለየ ጌራ ያንቺን ኪራራይሶ። ማግረሺን በሕልም ጐጆ ጌራ ብርሃን ጌራ ቆንጆ ለተለፋችን ዕዳ ሆንነው። ጌራ ብኩን ጌራ ብካይ ጌራ ከንቱ ጣር አሰልሳይ ጌራ የሕልም ዓለም ሰቃይ ጌራ ሰቀቀን መከራ በቅዥት ከምንጣራ አይሆንም እንጂ ቢሆንሽ ነፍሳችን ይኳረፍ እባክሽ። ጌራሸልም ጌራስውር ገጸረቂቅ ልበነብር እመብርሃን መሰል ጌራ እንደ እመብርሃን እማትምር ሽሸግ የዕድሜ ልክ ምሥጢር ጌራ የልጅነት ፍቅር አይሆንም እንጂ ቢሆንሽ ነፍሳችን ይኳረፍ እባክሽ። ድንቅም አደልገ ለብቸኞች ዛ አዲሳባ አብረን ዝም እንበል ከሰው መንጋ እንገንጠል ለአንድ እፍታ እንኳ እንገለል በእፎይታ ጥላ እንጠለል ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል። ከሰው ኳኳታ እንነጠል ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል በእፎይታ ጥላ እንጠለል ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል።