Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ይህ ዓይን ያወጣ ድፍረት ነው ይህ ሲኖዶስ ኃላፊነቱን ቢወጣ ኑሮ የቤተክርስቲያኗን ችግር እፈታለሁ የሚል ሌላ አካል ባልተነሳም ነበር ቤተክርስቲያንም እንዲህ ግራ ከሚገባ ደረጃ ላይ ባልደረሰች ነበር እፄም ይህ ሲኖዶስ ችግሩን ቢያስተካክልና ቢቆጣጠር የበቀል አርምጃ በመውሰድ መፍታት በሚለው ጸረ ወንጌል በሆነው ከነገሥታቱ ተወርሶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሥር ሰዶ በቀረው ፊውዳላዊ አስተሳሰብ በመመራት ጥያቄዎቹን ከመስማት ይልቅ በእኔ ላይ እርምጃ በመውሰድ ጩኸቴን ለማፈን በመመከሩ እንዲህ በይፋ ለመጻፍ ተገድጃለሁ አሁንም ጽሑፌ በዚህ ብቻ ስለማያበቃ ሌሎች ጽሑፎችን ከማውጣቴ በፊት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለሲኖደሱ አቀርባለሁ ጥቄዎቼን ሰምቶ ተገቢውን መልስ የሚሰጠኝ ከሆነ እንደዚህ ያሉ ጽሑፍ መጻፍ የቤተ ክርስቲያኗን ችግር ይፈታል ብየ አላምንም ጥያቄዎች ጥያቄ ክፍል ሁለት ጳጳስ መሾም ያለበት መነኩሴ ብቻ ነው አንጂ ባለትዳር መሾም አይገባውም መባሉስ አስቀድሜ እንደዘረዘርሁት በመጽሐፍ ቅዱስና በፍትሐ ነገሥት ስለ ጳጳስ ሹመት ከተደነገገው አንፃር ልክ ነው ዘተባለስ መጽሐፍ ቅዱስና ፍትሐ ነገሥት ተሳስተዋል ማለት ነው። ጳጳስ ባይሆኑም እንኳን የቤተክርስቲያን ምሑራን በቤተክርስቲያኗ ሁለንተናዊ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት የሲኖዶስ አባል የማይሆኑበት ምክንያት ምንድን ነው።
ምንኩስና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው አይደለም የሚለው በመነኮሳትና በባለትዳሮች የቤተክርስቲያን ሊቃውንት መካከል የሚነሳ ክርክር ነው ስለ ምንኩስና በመጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠ መመሪያም ሆነ ስያሜ ወይም ሥርዓት የለም ምክንያቱም የምንኩስና ታሪክም እንደሚያስስረዳው ምንኩስና የተጀመረው በኋላ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጀመረ ስለሆነ ነው ይላሉ ባለትዳሮች መነኮሳቱ ደግሞ ሲመልሱ ስያሚውና ስርዓቱ በግልጽ ተጽፎ ባይገኝም ምንኩስና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ብለው ይከራከራሉ ለዚህም ማስረጃ በታሪኩ ላይ እንደተገለፀው የምንኩስና ጀማሪ የሆነው አባ እንጦንስ ይዞት የተነሳውን በማቴዎስ ወንጌል ላይ ጌታችን አንድ ሰው ቀርቦ የዘለዓለም ሕይወት እንድወርስስ ምን መልካም ነገር ላድርግ ብሎ በጠየቀው ጊዜ ወደ ሕይወት ልትገባ ብትወድ ትዕዛዛትን ጠብቅ ብሎ ከሕግጋት የተወሰኑትን ጠቅሶ ቢነግረው እነዚህንስ ከልጅነቴ ጀምሬ ጠብቂአለሁ ብሎ በመመለሱ ጌታችን «ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ መጥተህም ተከተለኝ ያለውን ቃል በዋናነት ይጠቅሳሉ ለዚህ መልስ የሚሰጡት ባለትዳሮች ደግሞ ይህ ቃል ከምንኩስና ሥርዓት ጋር አይስማማም የመጀመሪያው ምንኩስና መስራች አባ እንጦንስ ሁሉን ትቶ የመነነ ቢሆንም ከእርሱ በኋላ ያለውን ምንኩስና ታሪክ እንደሚያሳየውና በምንኩስና ሥርዓት መጻሕፍት ላይ እንደሚታየው ከምንኩስና መገለጫዎች ዋና ዋናዎቹ ፃዛብት ንብረትን ለሚኖሩበት ገዳም ማስረከብ ወንድ ከሆነ ሚስቱን ሴት ከሆነች ደግሞ ባሏን መተው ወይም ያላገቡ ከሆኑ በድንግልና መኖርና ከገዳም ሳይወጡ መኖር ናቸው ከነዚህም መካከል ንብረትን ገዳም ይዞ መግባት ከሚለውና ሚሜስስትን ወይም ባልን ትቶ ገዳም መግባት ከሚለው ጋር ይህ ከላይ የተነገረው ጌታችን ለዚያ ሰው ከነገረው ቃል ጋር ይጋጫል ጌታችን ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድሆች ሰጥተህ ተከተለኝ ነው ያለው አንድ ሰው ንብረቱን ሁሉ ይዞ ገዳም ከገባ ይህ ሰው ለማህበራዊ ኑሮ ነው እንጂ ያለህን ሸጠህ ተከተለኝ ያለውን የጌታን ቃል ፈፀመ ሲያስብለው አይችልም ሌላው ደግሞ የትዳር ጓደኛን ትቶ መሄድ ነው ጌታችን ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድሆች ሰጥተህ ተከተለኝ አለው አንጂ ሚስትህን ትተህ አላለውም ስለሚስት የተነሳ ነገርም የለም ጌታን መከተል ማለት ደግሞ የግድ ትዳርን መፍታት አይጠይቅም ለዚህም ማስረጃ የሚሆነን ያ ሰው ባለፀጋ ነበርና ንብረቱን ሸጦ ለድሆች ሰጥቶ ጌታን መከተል አቅቶት ሲመለስ አይቶ ጴጥሮስ ጌታችንን አነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን» ብሎ ጠይቆታል ጴጥሮስ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ማለቱ ታዲያ ሚስትን መፍታትን አያካትትም ምክንያቱም ጴጥሮስ ሚስስቱን ትቶ አይደለም የተከተለው እርሱ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ሐዋርያት ሜስቶቻቸውን ይዘው ነው የተከተሉት ኛቆሮሮፀ ስለዚህ ይህ ለምንኩስና የተጠቀሰው የጌታ ቃል ለምንኩስና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያ ሊሆን አይችልም ይላሉ መነኮሳቱ ደግሞ ምንም ጴጥሮስ ና ሌሎችም ሐዋርያት ሚስቶቻቸውን ትተው የተከተሉት ባይሆንም ከዚያው ጋር አያይዞ ጌታችን ጴጥሮስን ስለስሜም ብለው ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እህቶችን ወይም አባትን ወይም አናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ አጥፍ ይቀበሳል የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሳል ብሎ ስለተናገረ ሚስትንም ያለው ቃል ሚስትን ትቶ መከተል እንደሚገባ ያስረዳል ይላሉ ለዚህም ባለትዳሮች መልስ ሲሰጡ አንድ ሰው በጌታችን አምኖ ጌታን ለመከተል ሲያስብ ሌሎች ቤተሰቦቹም ሆኑ ሚስቱ የሚቃወሙት ከክሆነና ከአርሻው የሚያገኘውም ጥቅም እንቅፋት የሚሆንበት ከሆነ ጌታ ስም ሌሎች ቤተሰቦቹንም ሚስቱንም የአርሻውንም ጥቅም ትቶ መከተል ዋጋ አንዳለው ሲያስረዳ ነው አንጂ ሚስትን መፍታት ሊያስተምር አይደለም ሚስትን መፍታት ኃጢአት እንደሆነ ደግሞ እራሱ ጌታችን «ሰው እናትና እባቱን ነ ይተዋል ከሚስስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ» የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን ን አንድ ስጋ ናቸው እንግዲህ ወደፊት ሁለት አይደሉም አግዚአብሔር ያጣመረውን አንግዲህ ሰው አይለየውም ብሎ ተናግሮአል በማለት ይከራከራሉማቴ ዘፍ በሌላም በኩል ጌታችን ተከታዮቹ በፈቃዳቸው ሁሉን ትተው ቢከተሉትም ምድረ በዳ ገዳም ይዚቸው አልገባም እዚያው በዓለም እያሉ ከአለም ለያቸው እንጂ «አኔም ከዓለም እንዳይደለሁ ከዓለም አይደሉምና ዓለም ጠላቸው ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም አንድታወጣቸው አልልም» ብሎ ዮሐ ስለዚህ እዚሁ በዓለም እያሉ በክርስቶስ ኣምኖ ከዓለም መለየትን እንጂ ትዳርን ፈትቶ ንብረትን ተካፍሎ ገዳም ገብቶ መቀመጥን ክርስቶስ አላስተማረም ይላሉ ምንኩስና የክርስትና ትምህርት ሳይሆን ከቡድሂዝም ዛይማኖት ትምህርት የተወሰደ ነው የሚሉም አሉ ከዚህ በላይ የሁለቱን ወገን ክርክር ማቅረቤ አንባቢ የራሱን አስተያየት እንዲሰጥ ለመጋበዝ ነው ከላይ የተኑሱትን ክርክሮች አንብቦ ከታሪኩ ጋር እንዲያነጻጽር ታሪኩ እንደሚከተለው ቀርቧል የምንኩስና ታሪክ ምንኩስና በግብጽ በረኃ በሲና በፍልስጥኤም የተጀመረ የመጀመሪያዎቹ የመነኮሳት ሰፈራዎች ገዳማት የተመሠረቱት በኛው መቶ ክፍለ ዘመን መግቢያ ላይ አባ እንጦንስ በተባለ መነኩሴ አማካኝነት ግብጽ ውስጥ ነው ከዚህ ግብፅ ውስጥ ታቢኒዚ በተባለ ቦታ በ ዓም አባ ባኩሚዝ ጳኩሚስ ሌላ ገዳም መሠረተ የመጀመሪያዎቹ መነኮሳት ተራ ምዕመናን ነበሩ ለገዳሙ የቅዳሴ አገልግሎት የሚያገለግሉ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ለቅስና ይሾማሉ ይህ በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የነበረ ልማድ ሲሆን በምፅራብ በኩል ግን መነኩሴ የሚሆኑት አብዛኛውን ጊዜ ካህናት ነበሩ ለምሳሌ ኢየሱሳውያን የተባሉት መነኮሳት ቀሳውስት ናቸው በምሥራቅና በምዕራብ መነኩሳት መካከል ያለው ዋናው ልዩነት ደግሞ የኦርቶዶክስ መነኮሳት በጾም በጸሎት በስግደትና በንስሓ የሚኖሩ ሲሆን የምፅራብ መነኮሳት ከመንፈሳዊ ሰማያዊው ዝንባሌ ሌላ በዚህም ዓለም ተግባር ለምሳሌ በሥነ ጥበብ በተግባረ እድ ድሆችን ሊረዱ በሚያስችሉ ድርጅቶች ላይ የበለጠ ትኩረት ይሰጡ ነበር የመጀመሪያው ገዳም መሥራች የአባ እንጦንስ የሕይወት ታሪክ በታላቁ የእስክንድርያ ፓትርያርክ በቅዱስ አትናቴዎስ ተጽፏል በታሪኩ መሠረት አባ እንጦንስ በርካታ ልጆች ካሏቸው ወላጆቹ ነው የተወለደው አንድ ቀን ወደ ቤተክርስቲያን ሲፄድ በማቴዎስ ላይ «ኢየሱስም ፍጹም ልትሆን ብትወድ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ መጥተህም ተከተለኝ አለው» ተብሎ የተፃፈው ሲነበብ ደረሰ ይህም የወንጌል ቃል ራሱን እንደጠራው ስለአመነ በፍጥነት ከቤተ ክርስቲያን ወደ ቤቱ ተመልሶ የ ጥማድ ያህል ከወላጀቹ የወረሰውን ርስት ለድሆች ለጎረቤቶቹ አካፍሎ መቃብደ ሙታን ወደ ነበረ አንድ ዋሻ ውስጥ ዘጋ ይህንም ያደረገበት ምክንያት ከዚሁ ቦታ አጋንንት በብዛት ያሉበት መሆኑን ስለአመነ በክርስቶስ ኃይልም ድል እንደሚያደርጋቸው ስለተገነዘበ ነው ቀጥሎ ባሉት ዓመታት ለኢትዮጵያ ይሾመሙ የነበሩ ጳጳሳት የሚመረጡት ከቀይ ባህር ኪሎ ሜትር ያህል ርቆ ይገኝ ከነበረው ከዚሁ ከአባ እንጦንስ ገዳም ነበር በዚሁ በአባ እንጦንስ ዘመን ለውትድርና ተገዶ የነበረው አባ ጳኩሚስ የውትድርናን መራራነት ከተመሰከተና በአባ አንጦንስ ገዳም ያለውን የምንኩስናን ጣዕም ከተረዳ በኋላ በዚያው በሲና በረኃ የራሱን ገዳም መሥርቷል በዚህም በማኅበረ መነኮሳቱ ውስጥ የተግባረ እድ ሙያ ይከናወን ነበር የገዳሙ አበ ምፄት አስተዳዳሪ ለሥራው የሚያስፈልጉትን መሣሪያዎች የማቅረብና የተመረቱት ነገሮችም ተሽጠው ለገዳሙ አገልግሎት እንዲውሉ ያደርግ ነበር ኃጢአት የመነኮሳቱን ኑሮ እንዳያናጋው እያንዳንዱ መነኩሴ በየቀኑ የሠራውን ኃጢአት እንዲናገር ተደንግጎ ነበር ቤተክርስቲያንም ይህንን ኃጢአትን የመናዘዝ ልማድ የወሰደችው ከዚሁ ሳይሆን እንዳልቀረ ይገመታል ይህም የምንኩስና ሥርዓት በፍጥነት እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ተስፋፋ ይኸውም በፍልስጥኤም ውስጥ በጋዛ ነበር ሂላርዮስ የተባለው ሰው ገና የአሥራ አምስት ዓመት ወጣት ሆኖ እያለ በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን የተፈጸመውን የክርስቲያኖችን መከራና ስደት አይቶ ከአረማዊነት ወደ ክርስትና ተመልሶ እርሱም ግብጽ አገር ወደሚገኘው ወደ አባ እንጦንስ ገዳም ሄዶ የምንኩስናን ሥርዓት ካጠና በላ በ ዓም ከጥቂት የግብጽ መነኮሳት ጋር ወደ ፍልስጥኤም ሀገር ተመልሶ በጋዛ ገዳሙን መሥርቷል የሄላርዮስ ታሪክ ሪኒምስ በተባለው የምፅራብ አብያተ ክርስቲያናት ቤተክርስቲያን አባት በ ዓም ተመዝግቧል በኢየሩሳሌም በሙት ባህር መካከል የሚገኘው የይሁዳ በርኃ በኛውና በኛው መቶ ክፍለ ዘመን በብዙ ገዳማት የተከበበ ሰፈረ መነኩሳት ሆኖ አንደነበር በታሪክ ታውቋል በቪሁ ጊዜ በ ዓም ተማሪ የነበረ ሀሪቶን የተባለ ሰው ኢየሩሳሌምን ለመሳለም በይሁዳ በረፃ ሲያልፍ ወንበዴዎች ደብድበው ከማረኩት በቷላ ወደ አንዱ ዋሻ ይዘውት ገቡ ከዋሻውም ውስጥ ወይን አግኝተው ከጠጡ በጊላ ወይኑ የተመረዘ ኑሮአል ሁሉም ሞቱ ሀሪቶንም ይህን ከተመለከተ በኋላ ቀሪውን ሕይወቱን በምንኩስና ለማሳለፍ ቆረጠ በዚሁ ገዳም ዘግቶ ተቀመጠ ሀሪቶን የተወለደው ታናሽ እስያ ውስጥ ነው ታላቁ ባስልዮስ ትምህርቱን አቴንስ ውስጥ ካጠናቀቀ በቷላ በ ዓም ከወላጆቹ የወረሰውን ርስትና ጉልት እንዲሁም ቤት ለመነኮሳት መኖሪያ አድርጎ በግብጽ በኢየሩሳሌም በሶርያ እተዘዋወረ ሥርዓተ ገዳማትን በብዙ አጥንቷል ከዚያም ከተመለሰ በኋላ አንቀጾች ያሉት ሥርዓተ ገዳም ጽፎ ለገዳሙ መተዳደሪያ እንዲሆን ኣድርጓል ይህም የባስልዮስ ሕግ በመባል አስካሁን ይታወቃል በፍትሐ ነገሥት የሚገኘው የመነኮሳት ሥርዓትም ይህን መሠረት ያደረገ ነው ፍነ አንቀጽ ኦኮኢሚትን እየተባለ የሚጠራውና በሜስፓታሚያ በሁለቱ ወንዞች ጤግሮስና ኤፍራጥስ መካከል የሚገኘው ሀገር አካባቢ የተነሣው እንቅስቃሴ ደግሞ መነኮሳት ጭራሽ ከእንቅልፍ እንዲወገዱ የሚቀሰቅስ ነበር ይኸውም ጌታ ሳታቋርጡ ተግታችሁ ጸልዩ ያለውን መነሻ በማድረግ ነው ሉቃ በ ዓም የቁስጥንጥንያ ቆንሲል የነበረው ስቱዲዮስ የተባለው ቁስጥንጥንያ ውስጥ ገዳም ለመመሥረት ፈልጎ እነዚህን አኮኢሚሜትን የተባሉትን መነኮሳት አስመጣ በርሱ አማካኝነት የተመሠረተውና በስሙ ስቱዲዮስ ገዳም እየተባለ የሚጣረው ገዳም በዚሁ አካባቢ ለሜገኙ ገዳማት ሁሉ ምሳሌ እንዲሆን በ ዓም ተወሰነ ይህም የሆነው ታላቁ ቲዎጾር የገዳሙን አበምኔትነት ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ነው በኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ የዚሁ ገዳም ሥርዓት ወደ ኢትዮጵያና እንዲሁም ወደምዕራብ ሀገሮች ተሰራጭቷል የሩስያው ቤኒዲግት ሱቢያኮ ከተባለው ቦታ በገበሬዎች አማካኝነት እንዲሰደድ ሲደረግ ምንቴ ካሲኖስ በተባለው ቦታ ቤትና የቦታ ስጦታ ስለተደረገለት በ ዓም መነኮሳትን በማሰባሰብ ገዳም መስርቷል ሞንቲባሲያስ በሚባለው የምዕራብ አውሮፓ የሚገኙ ቤኒዲግቱስ ገዳማት ሁሉ መስራችና የበላይም መሪ አስተዳዳሪ ነው ቤኒደግቱስ ያዘጋጀው ሥርዓተ መነኮሳት አብዛኛውን ጊዜ የተወሰደው ታላቁ ባስልዮስ ከጻፈው ሥርዓተ መነኮሳት ነው በዚህ ጊዜ በኢትዮጵያ የምንኩስና ሥርዓት ማበብ ጀምሮ ነበር ይህም የሆነው አቡነ አረጋዊ የተሣቱ ዘጠኙ ቅዱሳን መሪ በመሆን ወደ አክሱም ከመጣ በላ ነው የመጣውም በቢዛንስ መንግሥት ይሰደዱ ከነበሩት የሶርያ ክፍል ሳይሆን እንዳልቀረ ይገመታል የኢትዮጵያ ሥርዓተ ገዳም የሚያዘነብለው ሶርያ ወደሚገኙ ገዳማት ሲሆን መጽሐ መነኮሳትም የተጻፈው ታላላቆቹ ሶርያ ገዳም አባቶች ያዕቆብ ዘሥሩግና ፊሎክስያስ ዘማአቡክ ከጸፉት ሥርዓተ መነኮሳት እየተተረጎመ ነው ምንኩስናን ወደ ምዕራብ የወሰደው ከ የነበረው ሊቅ አትናቴዎስ ወደሮም በተሰደደበት ጊዜ ነው ይኸውም አስቀድሞ ወደ በረኃ ፄዶ ሥርዓተ ምንኩስናን ከአባ እንጦንስ ተምሮ ስለነበር ነው ምዕራፍ ሶስት ምንኩስና በስርዓት መጻሕፍት የምንኩስና አፈጻጸም ሥርዓት አሲረ ምንኩስና ቅዱስ የሚባል የምንኩስና ሥርዓት መጽሐፍ አለ በዚያ መሠረት የምንኩስና ሥርዓት ሲፈጸም ምንኩስና የሚቀበለው ሰው መጀመሪያ በፈቃዱ ከዓለም መለየቱን ከዚያም የምንኩስና ኑሮው ምን ዓይነት አንደሚሆን በቃል ያስረዱታል በጽሑፍም ያነቡለታል ይህንም ድምጹን ከፍ አድርጎ መስማማቱን ሲገልጽ ከፊታቸው ያጋድሙትና ጸጉሩን ይላጩታል ቀጥሎም ለምንኩስና በሚሆነው ልብሱና በሰውየው ላይ እንደሞተ ሰው ጸሎተ ፍትሐት ይጸልዩለታል ከዚያም በመጀመሪያ የገዳሙ አበምኔት መምህር በመቀጠል በፍትሐቱ የተገኙት ሁሉ ይባርኩትና ልብሱን ያለብሱታል ከዚያ በኋላ የመጨረሻው ጸሎት ተጸልዮለት የምንኩስና ሕይወት ኑሮውን ይጀምራል እንደቀድሞው ሕግ ከሆነ ከጥቂት ዓመታት በኋላ አስኬማ የሚባል ልዩ ልብስ ይሰጠውና ወደ ከፍተኛው ደረጃ ይሸጋገራል አስኬማ ከነት የተለፋ ቆዳ የሚሰራ የመስቀል ሞልክት ያለበት ነው አሁን አሁን ግን ማንኛውንም የምንኩስና ልብስ አስኬማ ይሉታል የአኗኗር ስርዓት በፍትሐ ነገሥት ከላይ ባየነው የምንኩስና ታሪክ እንደተመለከተው ምንኩስና በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጀመረ የመናንያን የአኗኗር ስርዓት በመሆኑ በመጽሐፍ ቭ ቅዱስ የተሰጠ ስያሜና ስርዓት ባይኖረውም በጊዜው የነበሩ አበው መነኮሳት አንዴት መኖር እንዳለባቸው ሥርዓት ሠርተዋል እንደዛሬው የምንኩስና ሥርዓት መረን አለቀቁትም የዛሬው ምንኩስና መረን መለቀቁን የምናየውም የቀድሞዎቹ አበው በሰሩት በራሱ በምንኩስና ስርዓት ነው እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ አይደለም ምክንያቱም ስለ ምንኩስና በመጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠ ስያሜም ሆነ ስርዓት ሰለሌለ ነው አበው አንደ መነሻ ከጠቀሷቸው አንድ አንድ ቃላት በስተቀር ይህን የቀድሞውን ምንኩስና የአኗኗር ሥርዓት በሚከተሉት ነጥቦች ከፋፍለን እንየው ቦታና የቦታው ሥርዓት የመነኮሳት መኖሪያ ቦታ ገዳም ይባላል ገዳም ማለት የግዕዝ ስሙ ሲሆን ትርጉሙ ምድረበዳ ነው ሰው የማይኖርበት ማለት ነው ግዕዙ መጽሐፍ ቅዱስ ገዳም የሚለውን አማርኛው ምድረ በዳ ይለዋል ማቴ ምድረ በዳ ማለትም ሰዎች የማይደርሱበት ማለት ነው ባስልዮስ በጻፈውና የእርሱን ጽሁፍ መሠረት አድርጎ በፍትሐ ነገሥት በተጻፈው የመነኮሳት የአኗኗር ስርዓት መሠረት መነኮሳት ከገዳም እንዳይወጡ የገዳሙ ዘበኛ እንዲጠብቅና ከውጭም ያለገዳሙ አስተዳዳሪ ፈቃድ መግባት እንደሌለባቸው ወጥተው ወደ ገጠር ወይም ወደ ከተማ ከገቡ ግን ምንኩስናቸውን ትተው ሕዝቡን መስለው መናር አንዳለባቸው ይናገራል ፍ ነገ አንቀጽ አመክሮ አመክሮ ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ፈተና ማለት ነው ይኸውም አንድ ምዕመን ለምንኩስና ወደገዳሙ ሲገባ ከመመንኮሱ በፊት ለምንኩስና ብቁ መሆኑን አለመሆኑን ሥርዓተ ምንኩስናውን በመለማመድ ራሱን የሚፈትንበት የምንኩስና ቅድመ ዝግጅት ነው ይህ ቅድመ ዝግጅት ወደ ገዳም ሲገባ ጀምሮ ከሚደረግለት አቀባበል ይጀምራል ስለ አቀባበሉ በፍትሒ ነገሥት እንደሚከተለው ሰፍሯል ምንኩስና በግድ ያይደለች የፈቃድ ናት አንዱ እንኳን መንኩሶ በውስጡ ይኖር ዘንድ ወደ ገዳም በደረሰ ጊዜ ከየት አንደመጣ ሥራውም ምን አንደሆነ ወደ ገዳማቸው በምን ምክንያት እንደተጠጋ ልጅ ሚስት እንዳሱት ስለዘመኑም ችግር ከልጆቹና ከሚስቱ ሊያመልጥ ፈልጎ እንደሆነ የገዳሙ መምህር በጽኑ ይመርምረው ሚስት ያለችው ቢሆን መመንኮሱንም የማትወድ ብትሆን አይቀበሉት ከሚስቱ የተነሣ ህመምና ክፉ ነገር ቢሆንበት ግን ሊድን ወዶ ከእርሷ ቢለይ ይቀበሉት ምንኩስናን የወደደ ሁሉ ልጆች የሌሉት ከሆነ ከመመንኮስ በፊት እንደወደደ በገንዘቡ ይዘዝ ከመነኮሰ በኋላ ግን ገንዘቡ ሁሉ ለገዳሙ ይሆናል በምርመራውም አግብቶ የነበረ ከሆነና ሚስቱን የተወበትም ምክንያት አሳማኝ ከሆነ ወይም ሙታበት ከሆነ ያላገባ ከሆነ ደግሞ በድንግልና ፀንቼ አኖራለሁ ካለ በገዳሙ እንዲኖር ይፈቀድለታል የሥጋ ዘመዶቹንና የዚህ ዓለምን ነገርም ሁሉ መርሳት እንዳለበት ይመከራል አመክሮውን ይጀምራል ከመመንኮሱ በፊት እንደ ገዳሙ ሥርዓትና እንደርሱ ሁኔታ ከሦስት እስከ ሰባት ዓመት ገዳሙን እያገለገለ በአመክሮ ይቀይና ይመነኩሳል ከዚህ በቷላ ከገዳሙ መውጣት አይፈቀድለትም አመጋገብ ስለመነኮሳት አመጋገብ ፍትሐ ነገሥት እንዲህ ይላል ለገዳሙ አርሻ የሚያርሱ መነኮሳት የሆነ እንደሆነ በቀን ሁለት ጊዜ በስድስት ሰዓትና በአሥራ ሁለት ሰዓት ይመገቡ የማያርሱ የሆኑ እንደሆነ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ በዘጠኝ ሰዓት ወይም በአሥራ ሁለት ሰዓት ይመገቡ ሥጋ ለዘለዓለም አይብሉ ወይን ሐዋርው ጳውሎስ ለጤሞቴዎስ አንዳዘዘው ለመድኃኒት ያህል ይቅመሱ ይላል ጤሞ ፍ ነገ አንቀጽ አለባበስ የመነኮሳት ልብስ እንደ ዮሐንስ መጥምቁ ማቅ ይልበሱ ወገባቸውን ከቆዳ በተሠራ መታጠቂያ ይታጠቁ ይላል ዮሐንስ ከግመል ፀጉር የተሠራ ማቅ ይለብስ ወገቡንም በጠፍር ይታጠቅ ነበርና ማቴ ከያጊጡ ሽቱ አይቀቡ ይላል አንቀጽ ጸሎትና ሥራ ለጸሎት ለመስገድ የተዘጋጁ ይሁኑ ወታደር ለጠብ ማታና ቀን ለውጊያ ሰዓት እንደሚዘጋጅ በማለዳ ወደሥራ ይገስግሱ በቀትር ጊዜ ይረፉ ከጸለዩ በኋላ ይመገቡ ፀሐዩ አእስከሚቀዘቅዝም ይረፉ ፀሐዩ ከቀዘቀዘ በኋላ እስከ ምሽቱ ድረስ ይሥሩ ከዚያ በኋላ ፀልየው ይመገቡ ይላል አንቀጽ ሹመት አለመፈለግ መናኝ የክህነት የአበ ምኔሄትነት ሹመት መውደድ አይገባውም የሹመት ፍቅር ሰይጣናዊት በሽታ ናትና በዚህ በሽታ የተያዘ ሰው ካህናትና ሹማምንት ሊሆኑ በሚገባቸው ላይ ቀናተኛ ይሆናል ሰው መክሮ ያነሳሰባቸዋል በነርሱ ሹመት ይተካ ዘንድ ሞታቸውን ይወዳል ሹመቱ ባልሆነለት ጊዜ በርሱና በነርሱ መካከል ችግር ይፈጥራል ከዚህ መጥፎ ተግባር ይራቅ ለሹመት በሚበቃ አድል እግዚአብሔር ከወደደ አርሱ ብቻ የሚሾመውን ያውቃል ይላል አንቀጽ ከተቃራኒ ፆታ መለየት አስቀድመን ከመጽሐፍ ቅዱስ አንዓርም አንዳየነው መነኩሴን መነኩሴ ከሚያሰኙት ዋና ዋና ነገሮች አንዱ ከተቃራኒ ፆታ መለየት ነው በሥርዓተ መጻሕፍትም አመክሮ በተሰኘው ክፍል አንዳየነው ወደ ምንኩስና ሲገባ ሚስት ያለችው ከሆነ ሚስቱ ፈቅዳለት ወይም አሳማኝ በሆነ ምክንያት ከርሷ ጋር መኖር የማይችል ከሆነ ፈቶ ነው ወደ ገዳም መግባት ያለበት ከዚያም በኋላ ወንዶች ከሴቶች ሴቶች ከወንዶች ጋር ከማይተያዩበት ቦታ ነው መኖር ያለባቸው ፍትሐ ነገሥት ከሴቶች ጋር አይጎራበቱ ከመነኮሳት ወገን ከሴቶች ጋር አየኖረ ይህ ነገር ድል አይነሣንም አይበል ይለያዩ ካልተለዩ ግን ሁለቱም ይወገዙ ይላል ሴቶችንም ን ወንድ ካለበት ቦታ አይቀመጡ ይላቸዋል አንቀጽ እስከዚህ ያየነው በፍትሐ ነገሥት የተሠራውን ሥርዓተ ምንኩስና ነው በሃይማኖተ አበው ሃይማኖተ አበው ደግሞ ስለመነኮሳት በተጻፈው ክፍል የሚከተለውን ይናገራል። መነኮሳት ሆነው ቢነግዱ ግን በመከራ የሚገኘውን ክብር ለማግነት የተቀበሉትን የተቀደሰ ማዕረጋቸውን አዋረዱ አንተ መነኩሴ ወይም አንተ ካህን ደዌ ሕማም የሌለብህ ከሆንህ አንቅልፍህ ሁል ጊዜ በመጠን ይሁን ከሁሉ አስቀድሞ ወደተግባረ ነፍስና ወደ ተግባረ እድ ተመለስ እርሻን ቁፋሮን ያዝ ሰነፍ አትሁን በእጅህ ከሰራኸው ሥራ ከራስህ አትርፈህ ለድሆች ለደካሞች ለመጻተኞች የምትሰጠውን ሰአንተም የምትሻውን ታገኝ ዘንድ አንተ መነኩሴ ከአኃው ጋር በአንዲት ገዳም በአንድነት ሳለህ ከርስትህ ከሰበሰብከው በእጅህ ከአገኘኸው ይህን የመሰለ ቢኖርህ በጌታ ትዕዛዝ አንተ አብርፃቸው ካለህ ከአንደኛው ከርሱ ምንም አትሰውር ያለህን ሁሉ ሽጠህ ዋጋውን ለማኅበሩ አበርክት ከአኃው ጋር በአንድነት ብትኖር ሰአንተ ብቻ የሆነ እርሻ ወርቅ ብር ቢኖርህ ወንድሞችህ ያላገኑት ከዚህ ዓለም ገንዘብ ማንኛውም ቢኖርህ አንተ መናኒ አይደለህም ይህን ዓለም ፈቃዱንም በእውነት አልናቅህም አንተ ዘበትህ አጋንንትም ዘበቱብህ እንጂ ከዚህ በላይ ያየናቸው በፍትሐ ነገሥትም ሆነ በሃይማኖተ አበው የተመዘገቡት ምንጫቸው የባስልዮስ የሥርዓተ ምንኩስና መጽሐፍ ነው ምዕራፍ አራት ምናኩስና ዛሬ በኢትዮጵያ ባለፈው ምፅራፍ ምንኩስና ታሪካዊ አመጣጡን እንዲሁም የአኗኗር ሥርዓቱን ያብራራሁት ዛሬ በሀገራችን የሌቦችና ወንበዴዎች መጠለያ ከሆነው የምንኩስና ሥርዓት ጋር እያነፃፀሩ ምዕመናን እውነታውን ተረድተው አንደኛ በጌታችን ደም ላይ የተመሠረተችው ወንንላዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን በምንኩስና ስም ጌታችን እንዳለውየሌቦችና የነፍ ገዳዮች ዋሻ መሆኗን ማቴ የሐ ሁለተኛ ዛሬ የሌቦችና የወንበዴዎች ጭንብል ሆኖ ሥርዓቱ ቢበላሽም የምንኩስናን ሥርዓት ቀደም ብለን እንዳየነው ምንም የፈቃድ የኑሮ ሥርዓት ቢሆንም ሰዎች ከኃጢአት ርቀው የሚኖሩበት ሥርዓት መሆኑን ተረድተው ራሳቸውን ከሌቦችና ከወንበዴዎች እንዲጠብቁ ለማስገንዘብ ነው ሌቦች ነፍሰ ገዳዮች ወንበዴዎች ብየ ደፍሬ ስናገር ብዙ ሰዎችን ያስቀይም ይሆናል እኔ ግን አይደለሁም ጌታ እንጂ ሥራቸው ጌታ እንደተናገራቸው ወንበዴዎች ካልሆነ ተሳስቻለሁ ሥራቸው እንደነዚያ ከሆነ ግን ጌታ የተናገረውን መናገር ምን ያሳፍራል ሐዋርያው ጳውሎስ በወንገል አላፍርም ብሉአልና አሁንም ለወንጌል ከተጠራን በወንጌል ማፈር የለብንም ቤተ ክርስቲያን የወንበዴዎች ዋሻ ስትሆን ዝም ብለን ስናይ የራሳችን ድርሻ መወጣት ይኖርብናል አለዚያ ግን የወንበዴዎች ተባባሪ መሆናችን ነው የውንብድና የነፍስ ገዳይነት ሥራቸውን ወደፊት እናየዋለን በቅድሚያ ያሁኑ ሥርዓት ከቀድሞው ሥርዓት ጋር ያለውን ልዩነት አንይ የመነኮሳት ዓይነቶች ቀድሞ ምንኩስናውም ሆነ በመነኮሳቱ የአኗኗር ስርዓት አንድ አይነት ነበር ዛሬ በሀገራችን የሚታዩትን መነኮሳት ግን ስራቸውንና አኗኗራቸውን መሰረት በማድረግ በአራት ከፍሎ ማየት ይቻላል እነርሱም አባ ዓለም ለምኔ አባ ዓለም በቃኝ አባ ዓለም በዘዴ አባ ቆብ አልባ ናቸው አባ ዓለም ለምኔ በድሮው የምንኩስና ሥርዓት መሠረት ሚስት ሳያገቡ ቤት ሳይሠሩ በብሕትውና ተወስነው በገዳም የሚኖሩት ናቸው አባ ዓለም በቃኝ በዚህ ዓለም ሚስት አግብተው ቤት ሠርተው ኑረው በኋላ ሚስት ስትሞትባቸው ወይም ስትከዳቸው ወይም በበሽታም ምክንያት ይህን ዓለም በቃኝ ብለው መንነው ገዳም የሚገቡና ወይም በአሉበት አካባቢ መንኩሰው ቤተ ክርስቲያን የሚያገለግሉ ናቸው እነዚህ ዓለምን አይተው በቃኝ ብለው የተዋት ስለሆኑ በዓለም ሁነው ቤተክርስቲያንን ቢያገለግሉም ብዙም ሲያጭበረብሩና ምዕመናንን ሲያታልሉ ዓይታዩም ቤተ ክርስቲያን በማስተዳደር በኩልም አስቀድመው ቤተሰብን በማስተዳደር ችግሩን ስለሚያውቁት የምዕመናን ፃሳብ የመረዳትና የማዘን ዝንባሌአቸው የተሻለ ነው ቤቱን ማስተዳደር ያልቻለ የእግዚአብሔርን ቤት ማስተዳደር አንዴት ይችላል አንዳለው ሐዋርው ጳውሎስ ቤተሰብ ያስተዳድሩ የነበሩ መሆናው የተሻሉ ሊያደርጋቸው ችሏል ጢሞ ከጥቂቶቹ በቃን ካላሉት በስተቀር አባ ቆብ አልባ እነዚህ የምንኩስና ልብስ ሳይለብሱ ቆብ ሳይደፉ በድንግልና ተወስነው ትምህርት በማስተማር ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ መምህራን ናቸው አነዚህ ለሀገራችንም ሆነ ለቤተክርስቲያናችን ባለውለታዎች ናቸው ዘመናዊ ትምህርት ወደ ሀገራችን ከመግባቱ በፊት ቤተ ክርስቲያናችን ብሎም ሀገራችን በፊደል በሥነጽሑፍ በቋንቋ ራሷን ጠብቃ እንድትቆይ አድርገዋል የቀድሞዎች የዛሬዎቹ መሰሎቻቸውም በማስተማር ተጠምደው የራሳቸውን አስተዋጽኦ አያበረከቱ ነው የቤተክርስቲያኗ ገንዘብ በአነ አባ ዓለም በዘዴ ቁጥጥር ሥር ስለሆነና እንደድሮው ለምኖ ለመብላትም ሕዝቡ ስለ ደኸየ የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ እንዲሉ እነርሱም እንደነ አባ ዓለም ለምኔ ለመሆን ተማሪዎቻቸውን እየበተኑ ወደ ከተማ በመፍለስ ላይ ናቸው እንጂ አነ አባ ዓለም በዘዴ እስከ ሦስት ሺህ ብር ይከፈላቸዋል እነርሱ ግን የመቶ ብር ደመወዝ የሚሰጣቸው አጥተው የቤተክርስቲያኗን ትምህርት ማስተማር ትተው በመኮብለል ላይ ናቸው አንዳንዶቹ ደግሞ ወደርሻና ንግድ ባመሰማራት ላይ ናቸው እነ አባ ዓለም በዘዴ ፊደልን እንኳን አስተካክለው ሳይቆጥሩ ነው ባቋራጭ ቆባቸውን በመጫን ወፍራም ደመወዝ የሚከፈላቸው ወይም የምዕመናንን ገንዘብ ያለከልካይ የሚካፈሉ እነርሱ ግን አሥርና ፃያ ዓመት ተምረው መቶ ብር እንኳን የሚሰጣቸው አጥተው ነው የሚራቡት ታዲያ እነዚህ መምህራን ምን ያድርጉ የችግሩን አሳሳቢነት የቤተክርስቲያንን ልጆች ሊያሳስብ ይገባል እያልሁ ወደ ተነሣሁበት ነጥብ ልመለስ አባ ዓለም በዘዴ እነዚህ ጌታ ፍሬ እንዳጣባት የለመለመች በለስ በአለባበሳቸው ጀርፈፍ ብለው የጽድቅ ፍሬ የማይገኝባቸው ናቸው እስኪ ይህን ሃሳብ በጥንቱ ትርጓሜ ስልት ልግለጸው ለሊቃውንቱ በቀድሞው በለስ አስራኤል ናት ተብሉ ተተርጉሟል አሁን በሀገራችን ደግሞ መነኩሴ ተብሎ ቢተረጎም የሚስማማ ይመስለኛል የቃሉ የመጨረሻ አንድምታ ሆኖ እንዲህ ቢቀጥልስ አንድም በአንጻረ በለስ ረገሞ ለመነኮስ ያሰኛል በለስ መነኩሴ ቅጠል ጀርፋፋው አለባበሳቸው ጌታ ፄዶ ፍሬ እንዳጣባት የዛሬ መነኮሳትም የጽድቅ ፍሬ አይገኝባቸውምና ፍሬ አይገኝብሽ እንዳላት ግብሩ ፍሬ ዘይደሉ ለንስሐ እንዲል ንስሐ ገብተው የጽድቅ ፍሬ አያፈሩምና ማቴ አንድም ፍሬ ልጅ ነው ብሎ መነኮሳት ልጅ አይወልዱምና ፍሬ አይገኝብሽ አላት እነ አባ ዓለም ለምኔ እንጂ እነ አባ ዓለም በዘዴማ እስመ ብዙኃት አንስቲአ ሆሙ ወአልቦ ልቁ ለደቂቆሙ ሜስቶቻቸው ብዙ ኣ ልጆቻቸው ቁጥር የላቸው እንዲሉ ይፈለፍሉ የለምን ቢሉ እናቱ ካላጋለጠች ነ ልጁ አባቱን ካልመሰለ አይታወቅምና ካልታወቀ ብሎ ደግሞም ቢወልዱም አያሳድጉምና ልጅ የላቸውም አለ አንድም ምፅመናንን በመልካም ሥነ ምግባር በመንፈሳዊ አኗኗር አይወልዱምና ፍሬ አይገኝብሽ ብሎ ተናግሮባቸዋል ለጥቋቁር ርግቦች የተነገረ ትንቢት እነዚህ ዛሬ በምንኩስና ስም በከተማ ለተሰማሩ ሰዎች ከብዙ ዘመናት በፊት እንደዚህ ሆነው እንደሚመጡ ትንቢት መሰል ንግርት ተነግሮላቸዋል ያውም ከነአለባበሳቸው ትንቢቱን አባ ጳውሊ የተባለ ባህታዊ ራፅይ አይቶ ለአባ እንጦንስ እንደነገረው ነው ፊልክስዮስ በተባለው መጽሐፍ መቅድም ላይ ሰፍሮ የሚገኘው ምንም እንኳ ትንቢት የተባለው ነገር በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የተነገረ ነው ለማለትባንደፍርም ሰዎቹ ራሳቸው በራሳቸው ባሕርይ ላይ ይሆናል ብለው የተናገሩት ግን እውን ሆኖ ታይቷል ። ትምህርት ስለማይገባቸው ከቅኔ የትምህረት አሰጣጥ በስተቀር ሌላው ብዙም የሰውን አስተሳሰብ የሚያዳብር ባይሆንም የቤተክርስቲያናችን የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ሽምደዳ ስለሆነ ብዙዎቹ ይህ የሽምደዳ ትምህርት አልሆንላቸው ሲልና ጓደኞቻቸው ተምረው ካህን አስተማሪ ሆነው ሲበልጧቸው ቤተክርስቲያን በማገልገላቸውም የተሻለ ጥቅም ወይም ደመወዝ ሲያገኙ ሲያዩ ካህን ለመሆን እንኳን በአኛ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ትምህርት አይጠየቅም መሪ ጌታ ሆኖ ግን ቤተክርስቲያን በማገልገልና በማስተማር ብሎም የአብነት መምህር ለመሆን ከፍተኛ ድካምና ትጋት ስለሚጠይቅ እነዚህ ሰዎች ደግሞ ሰነፎችና ትምህርት አልገባቸው ሲል እነቪያ ጓደኞቻቸው ከደረሱበት ደረጃ ለመድረስ ብሎም ከነርሱ በላይ ባለሥልጣን ለመሆን አቋራጭ ዘዴ መነኩስን ማለትን ይመርጣሉ ይህም በቆሎ ትምህርት ቤት አብረውን በነበሩ በብዙ ሰዎች እያየነው ያለ ጉዳይ ነው ብዙ ሰዎችን እንደምናያቸው ትምህርት አልገባቸው ብለው አለዚያም ጎበዝ ተማሪ ትምህርቱን ተግቶ ሲማር መንደር ለመንደር ሲያውደለድሉ የነበሩ ሁሉ በኋላ ያንን ምንም ያልያዘ ጭንቅላታቸውን በቆብ ሽፍነው መነኮስን ብለው እነዚያ ትምህርታቸውን ተምረው በሙያቸው በተሰማሩት ላይ በበላይ ሆነው ሲያቃጥሉአቸው ይናራሉ እነርሱንም ብቻ አይደለም የቤተክርስቲያን አለቃ በሆነበት ቦታ ሁሉ ቤተክርስቲያንን በአውቀታቸው መምራት አልሆንላቸው ሲል ሕዝብን ከሕዝብ ካህንን ከካህን ካህንን ከሕዝብ በማበጣበጥ ቤተክርስቲያን ሲያውኩ ይኖራሉ በአሁኑ ሰዓት በየአንዳንዱ ዔተ ክርስቲያን ውስጥ ከሚገኙት አገልጋዮች በትምህርት ዝቅተኛ መነኮሳት ነን ባዮች ወይም እነ አባ ዓለም በዘዴ ናቸውየደብር አለቆችን ጨምሮ ከመቶ ዘጠና አምስት ያህሉ መነኮሳት ነን ባዮች ከሁሉም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በአውቀት ያነሱ ናቸው ይህንንም አብዛኛው ካህናት ቤተክርስቲያን የሚያዘወትር ምዕመን የሚያውቀው ነው አንዳንድ በትምህርታቸው ሻል ያሉ ቢኖሩ እንኳን መጀመሪያ በጥሩ ዓላማ ተነስተው መንኩሰው በላ አቅጣጫቸውን የሳቱ ናቸው ወይም እነርሱ ብዙ ተምረው ያልተማሩት በአቋራጭ ሥልጣን ይዘው ሲያይዋቸው ተምረው ማስተማራቸውን ትተው ወደምንኩስና የገቡ ናቸው ዞሮ ዞሮ ሁሉም ለቤተ ክርስቲያን በተሻለ አመራር ሲመሩ ወይም ሲያገለግሉ አይታዩም በትምህርት ማነስ ብቻም ሳይሆን በዓላማ መሳትም ምክንያት እስካሁን ከሀገራችን የተሾሙትን ጳጳሳት ጨምሮ በምንኩስና ማዕረገ ከነበሩም ሆነ ካሉት የማስተማሪያ ጽሑፍ እከሌ የሚባል የለም ማለት ይቻላል በተለይ በጵጵስና ደረጃ በጽሑፍ በማስተማር ደረጃ ቤተክርስቲያኗ አልታደለችም ለማለት ያስደናራል ለትውልድ የሚተላለፍ በጊዜውም ለሰው በሚባ ቋንቋ በሰል ያለ ጹሑፍ የጻፈ ጳጳስ አለ ለማለት ብዙም አያሰደፍርም ይህም የሆነበት ምክንያት አንደኛው ምክንያት ከላይ እንዳልሁት አብዛኞቹ ወደምንኩስና የሚመጡትና እስከጵጵስና ደረጃ ድረስ ሥልጣን የሚይዙት በትምህርት ስላልሆነ ነው ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ቀደም ብየ አንደጠቀስኩት አብዛኛው ቤተክርስቲያናችን ትምህርት በሀገራችን ከመቼ ጀምሮ እንደሆነ ባይታወቅም ከጥቂት ዘመናት በፊት ጀምሮ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴው የሚጠቅመውንም የማይጠቅመውንም የቀድሞ ሰዎች የጻፉትን የተናገሩትን መሸምደድ ብቻ አንጂ ትምህርቱ የተማሪውን አዕምሮ የሚያሰፋና የሚያመራምር ስላልሆነ ተመራምሮ ለማወቅም እንደ ክህደት ስለሚቆጠር በነዚህ በሁለት ዓይነት ምክንያቶችና በሌሎችም ምክንያቶች ምንኩስና አቅጣጫውን ከመሳቱ ጋር ተዳምሮ ከመነኮሳት በተለይም ከጳጳሳት ፍሬ ያለው የማስተማሪያ መጽሐፍ መጻፍ አልተቻለም በሌሎች ሀገሮች ቀድሞም የነበሩ ጳጳሳት ፃይማኖተ አበው የተባለውን መጽሐፍ ጨምሮ ሌሎችንም ድርሰቶች ጽፈው ለትውልድ አስተላልፈውልናል የዛሬዎቹም እየጻፉ ነው ምነው የአኛ ቤተ ክርስቲያን የወላድ መካን ሆነች አሁን ያለው የምንኩስናና የጵጵስና አካሄድ ወደ ተሻለ መስፈርት ካልመጣና ባለበት አካሄድ የሚቀጥል ከሆነ የወላድ መካንነቷ መፍትፄ የሚኖረው አይመስለኝም ለመከበር የሀገራችን ምዕመናን ቀደም ሲል ብዙም የመጽሐፍ ቅዱስ ግንዛቤ ስላልነበራቸው በጋብቻ ከመኖር ይልቅ በምንኩስና መኖር የበለጠ የጽድቅ አኗኗር እንደሆነ አድርገው ስለሚያምኑ በጋብቻ ከሚኖሩት ካህናት ይልቅ ለመነኮሱትና ለባህታዊ የበለጠ ክብር ይሰጣሉ ስለዚህ ነው ጸጉራቸውን በማሳደግ አሁን አሁን ደግሞ ሰው ሰራሽ ጸጉር በመጎንጎን በየከተማው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው ጩኸት በሚጮኹ ባህታውያን ነን ባዮች ሥር ተሰብስቦ ፍሬ አልባ ስብከታቸውን ሲያዳምጥ የሚውለው ከዚህ ከምዕመናን የመጽሐፍ ቅዱስ ግንዛቤ ማነስ የተነሣ ከባለ ትዳር ይልቅ ለመነኩሴው የሚሰጠውን ክብር ለማግኘትና ጻድቅ ቅዱስ ለመባልና በዚያውም የሥጋ ፍላጎታቸውን ለማሳካት ወደ ምንኩስና የሚገቡ ብዙዎች ናቸው በምንኩስና መኖር በጋብቻ ከመኖር የበለጠ አድርገው ያስቡ እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ስናየው ግን ከጋብቻ የበለጠ አይደለም ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንረዳው የአግዚአብሔር ጸጋና ጽድቅ የሚገኘው በማግባትና ባለማግባት ሳይሆን በአግዚአብሔር ምርጫና በተመራጩ መልካም ሥራና ታዛዥነት ነው እግዚአብሔር ሰዎችን ሲመርጥ አንተ አግብተፃል አንተ አላገባህም ብሎ የመረጠበት ጊዜ የሰም አብርሃምን ከሀገሩ ሲጠራው በጋብቻ ላይ እያለ ነበር ሲመጣም ሚስትህን ትተህ ውጣ አላለውም ዘጸ ሙሴን አስራኤልን እንዲመራ ሲመርጠው በትዳር ላይ እያለ ነበር ሲልከውም ሜስትህን ትተህ ፃድ አላለውም እንዲያውም በኋላ ሚስቱ ኢትዮጵያዊት በመሆንዋ ወንድሙ አሮንና እኅቱ ማርያም ቢያሙት አግዚአብሔር ተቆጥቶ ቀጥቷቸዋል እርሱ በቤቴ ሁሉ የታመነ ነው እኔ አፍ ለአፍ በግልጥ እናገረዋለሁ በምሳሌ አይደለም የአግዚአብሔርንም መልክ ያያል በባሪያየ በሙሴ ላይ ትናገሩ ዘንድ ስለምን አልፈራችሁም በማለት የርሱን ክቡርነት ነግሮአቸዋል ዘጉ በሐዲስ ኪዳንም ሚስት አግብቶ የነበረውን ቅዱስ ጴጥሮስን የሐዋርያት አለቃ አድርጎታል በእምነቱም አንተ ብፁህ ነህ ብሎ አመስግኖታል የቤተ ክርስቲያን ሀላፊነትና የማሰርና የመፍታትም ሥልጣን ሰጥቶታል ባለትዳሮችን እንደዚህ አንደመረጠና እንዳከበረ ሁሉ ሳያገቡ የሚኖሩትንም መርጧል አክብሮአል በገዳም በብህትውና ይኖር ወደነበረው ዮሐንስ ፄዶ ተጠምቋል ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ « ዮሐንስ የሚበልጥ የለም ብሎ ክብሩን ተናግሮአል ማቴ ሐዋርያው ጳውሎስንም ለወንጌል አገልግሎት የተመረጠ እቃ አድርጎታል ሐዋ እንግዲህ የነዚህና የሌሎችንም ምርጫና ጽድቅ ስንመለከት የእግዚአብሔር ምርጫና ጸጋው የተከናወነው በማግባትና ባለማግባት ላይ አይደለም ሰዎችም የርሱን ትፅዛዝና ምርጫውን ተቀብለው በመፈጸማቸው እንጂ ጻድቅና ቅዱስ የሆኑት በማግባታቸው ባለማግባታቸው አይደለም ስለዚህ ያላገባ መነኩሴ መነኩሴ በመሆኑ ብቻ ካገባው የበለጠና ቅዱስ ነው ብሎ ማሰብ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው ይህ የተሳሳተ አስተሳሰብ በምፅመናን ብቻ ሳይሆን በመነኩርቤ ነን ባዮች ዘንድም ያለ አስተሳሰብ ነው ለዚህም ነው ሕዝባችን መጽሐፍ ቅዱስ ካለማወቁ የተነሣ ይህን የተሳሳተ ግንዛቤ በመያዙ መነኩሴን እንደ ልዩ ጻድቅና ቅዱስ አድርጎ ስለሚቆጥር አነርሱም ቆብ በመጫን ብቻ ጻድቅ ለመባል መነኩሴ ነን የሚሉት እናም ይህን ከንቱ ሙገሳና ጻድቅ መባልን ሸተው ገብተው ወደስርቆትና ማጭበርበር የገቡት ብዙዎች ናቸው ለገንዘብ ጌታችን በወንጌል ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ መዝገብምሀብትም በሰማያት ታገኛለህ መጥተህም ተከተለኝ ብሎ እንደተናገረው ማቴ በሃይማኖተት አበውም መነኩሴ ከመነኮሰ በኋላ የግሉ የሆነ ገንዘብ ወርቅ ብር ሀብት ንብረት ሲኖረው እንደማይገባ ተደንግጓል አንድ ሰው ለመመንኮስ ወደገዳም ሲገባም ልጆች የሌሉት ከሆነና ንብረት ያለው ከሆነ ንብረቱን ሁሉ ለገዳሙ ማስረከብ አንዳለበት ይህን ካላደረገ ግን ዓለምን የናቀ ማናኒ መነኩሴ ሳይሆን አጋንንት የሚዘብቱበት አታላይ አንደሆነ ተጽፋል ዛሬ ግን ከዚህ በተቃራኒ መልኩ ብዙዎች መነኮስን የሚሉት በሌላ መንገድ ሊሳካላቸው ያልቻለውን የገንዘብ ማካበት በምንኩስና ስም ለማካበት ነው በሌላ መልኩ ገንዘብ ለማግኘት ለፍቶ መማር ደክሞ መሥራት ይጠይቃል ዛሬ በአኛ ቤተክርስቲያን ግን ገንዘብ ለማግኘት ምንኩስና ድካም የማይጠይቅ አቋራጭ መንገድ ነው እነዚህ ለገንዘብ የተሰማሩ መነኮሳት ነን ባዮች ገንዘብ እያጋበሱ ያሉት በሁለት ዓይነት መንገድ ነው አንደኛው ምዕመናን ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን አሥራትና መባ ጳጳስና የደብር አለቃ ሆነው በመጂዷጂም በስምምነት በደመወዝ በውሎ አበል በወንበር ወዘተ ስም የሚከፋፈሉት ነው በደመወዝ ብቻ እንኳን ብንመለከት የአንድ ጳጳስ ደመወዝ በአማካኝ ሰስድስት ባለትዳር የቤተክርስቲያን አገልጋዮች የሚከፈለውን ደመወዝ ያህላል ይህም ለቀለባቸው ከሚወጣው ሌላ ነው የአንድ የቤተክርስቲያን አለቃ ደመወዝ ደግሞ በአማካኝ ለአራት ባለትዳሮች ደመወዝ ይሆናል በአብዛኛዎቹ በርከት ያለ ገቢ ባለባቸው አብያተ ክርስቲያናትን የሚሹሙት መነኮሳት ናቸው እንደዚህ በመስማማት በደመወዝና በሌላ በሌላ መልኩ ከሚያገኙት ገንዘብ በተጨማሪም ሙዳየ ምጽዋት አያስገለበጡ በሚዘርፉት ገንዘብ ብዙዎቹ ጳጳሳትና የደብር አለቆች አዲስ አበባ ውስጥ ዘመናዊ የሆነ ቪላ ቤታቸውን ገንብተዋል ሌላኛው የገንዘብ ማግኛ ዘዴ ደግሞ እነዚህ ጳጳስና የደብር አለቃ እየተባባሉ የሚሺችዷዉሙትና ሌሎችም ይህ እድል ያልገጠማቸውን ጨምሮ እየፈጸሙት ያለ ዘረፋ የቤተክርስቲያን ማሠሪያ ለድዛ የሚመጸወት አምጣ ጸሎት እጸልይልሀለሁ ከደዌህ አፈውስፃለሁ እያሉ ጻድቅና ቅዱስ በመምሰል ለመነኩሴ ከናተኛ አክብሮትና አመኔታ ካለው የዋህ ሕዝባችን የሚዘርፉትን ዘረፋ ነው ይህም በብዙ የዜና ማሰራጫዎች የሚሰማ ጉድ ነው ይህ የገንዘብ ማግኛ የማጭበርበር ዘዴ አሁን አሁን በጥቂቱም ቢሆን ሕዝባችን እየተማረ ሲሄድ እየነቃባቸው በመፄዱ እየቀነስ ሄደ እንጂ ቀደም ሲል አንድ መነኩሴ ቆብ ጭኖ ከተማ ገባ ማለት ሙዳየ ምፅዋት በራሱ ተሸክሞ የመዞር ያህል ነበር ገንዘብ የሚያፍሰው ስለዚህ ነው ሰርቶ ገንዘብ ማግኘት ያልቻለው ሁሉ በአቋራጭ ለመክበር ቆብ እየጫነ ወደ ከተማ የሚገባው ለዝሙት አስቀድመን እንዳየነው መነኮሳት ከተቃራኒ ፆታ ጋር መጐራበትና መተያየት መቀራረብ እንደሌለባቸው በዝሙት ድል አልነሳም ብለው የተቀራረቡ እንደሆነ እንኳን መራራቅ አንዳለባቸው ያንን ባያደርጉ ግን ተወግዘው መለየት እንዳለባቸው በፍትሐ ነገሥት ተደንግጓል ፍነ አንቀጽ ማና በፍትሐ ነግሥት የተደነገገው በወንጌል የተነገረውን መነሻ በማድረግ ነው ጌታችን ስለስሜም ሜስትን የተወ መቶ እጥፍ ይቀበሳል ብሷል ማቴ ስለስሜ ሜስትን የተወ መቶ አጥፍ ይቀበላል ማለት ሚስት በማግባት ልጅ በመውለድ ከሚገኘው ደስታ መቶ እጥፍ የሜበልጥ ደስታ በኋላ በመንግሥተ ሰማያት ያገኛል ማለት ነው እንጂ መቶ ሚስቶች ይሰጡታል ማለት አይደለም በመንግሥተ ሰማያት ሰዎች እንደመላእክት የሚኖሩ እንጂ የሚያገቡ የሚጋቡ እንዳልሆኑ ደግሞ ራሱ ጌታ ተናግሮአል ማቴ ይህ ጌታችን ስለስሜም ሚስትን የተወ መቶ እጥፍ ያገኛል ብሎ የተናገረው ቃል በኋላ በመንግሥተ ሰማያት ስለሚገኝ ክብር ይሁን አንጂ የዛሬ መነኮሳት ነን ባዮች ግን በአንድ ሚስት ታሥሮ ከመኖር ይልቅ በምንኩስና ስም ከትዳር በመሸሽ ከተማ ለከተማ በመዞር መቶ ሴቶችን ማቀየያር በምንኩስና ስም አንድ ሚስት ትቶ መቶ ሴቶችን ማግኘት ብለው የተረጐሙት ይመስላል በስጋ ፍላት ሲተረጉሙት ማለት ነው ረ ይህን የዝሙት ተግባራቸውን የሚፈጽሙት ደግሞ ሲመቻቸው በየቤተክርስቲያናቱ ጥግ በሚኖሩበት መኖሪያ ቤታቸው እውነተኛ መነኩሴ መስለዋቸው ከሚመጡት ወይም እንደነሱ የአመንዝራነት ስሜት ተጠናውቷቸው ፍትፍት እየተሸከሙ ከሚመጡ ባለትዳሮችና ጋለሞታዎች ጋር አንዲሁም ወላጆቻቸውን ቤተክርስቲያን ስነምግባር ይማሩልናል ብለው የሚልኳቸውን ልጃገረዶች በማባበልና አስገድዶ በመድፈር ነው በዚህም በአስገድዶ መድፈር እጅ ከፍንጅ ተይዘው የክስ መዝገባቸው ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ ብዙዎች ናቸው በገዳም ሳይቀር ሴቶችን በማባበል ኤድስ አስይዘው በመገናኛ ብዙኃን የሰማናቸው አሉ ይህ በቤተክርስቲያን አካባቢ የሚደረገው ያልተመቻቸው ደግሞ በየ ቡና ቤቱ በመዞር ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር ነው የሚያመነዝሩት በዚህ ዙሪያ በኋላ የጥቂቶችን ታሪክ እናያለን ታመው ፈውስ ፈልገው ወደ ቤተክርስቲያን ከሚመጡ ሴቶች ጋር የሚያመነዝሩትም ብዙዎች ናቸው ጸቦል አንረጫለሰን በመስቀል እንዳስሳለን እያሉ በዚያው አንቀው እየያዙ ተደርሶባቸው የተዋረዱ ስንቶች ናቸው አነዚህ ላይ ቆየት ያለና አንድ ዲያቆን የገጠማት የቅኔ ስንኝ ላንሳ አንዲት ወጣት ታማ ለጸበል ወደ ቤተክርስቲያን ትመጣና ደጀ ሰላሙ አካባቢ ታርፋለች ከዚያ ወጣ ገባ ስትል የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የሆኑት መነኩሴና አንድ ዲያቆን ሁለቱም ቀልባቸው ያርፍባታል ከዚያም መነኩሴው ለመጠየቅ እያሉ በምክንያት ወደርሷ እየተመላለሱ ለርሱ እንቅፋት ይሆኑበታል ከዚያም በቅኔ « ከደጀ ሰላሙ ታመሽ ተኝተሽ እንያት አያሉ አባ ባሱብሽ » ብሎ ተናገረ ይባላል ከዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባ ነገር ይህን ሁሉ በግልጥ ልናገር ተገደድሁት በምንኩስና ስም አተፈጸመ ያለውን ደባ ሕዝባችን አውቆ ራሱን ከነዚህ ዓይነት አመንዝራዎችና ሴቦች እንዲጠነቀቅና ይህ ዓይነት ሥርዓትም የአውነተኛው ምንኩስና ሥርዓት አለመሆኑን አሁን አየተፈጸመ ያለው የምንኩስና ሥርዓት አላማውን የሳተ መሆኑን እንዲያውቅ ለማድረግ ነው ወላጆችም ልጆቻቸውን ከአነዚህ ዓመንዝራዎች ሥራ ልጆቻቸውን እንዲጠብቁ በተለይ በዚህ የአስከፊ በሽታ ዘመን መጠንቀቅ አንዳለባቸው ለማስገንዘብ ነው በስንፍና ምክንያት ስንፍና ለሕጉ ወጥ ምንኩስና ያደረገው አስተዋጽኦ በሁለት ዓይነት መንገድ ነው አንደኛው ከገዳም ውስጥ የነበሩት ወደ ከተማ አንዲኮበልሉሱ አድርጓል ሁለተኛ ደግሞ ወደገዳም ያልገቡና ሠርቶ መብላት ሞት መስሎ የታያቸው ሁሉ ምንኩስናን የሥራ መሸሻ ምሽግ እንዲያደርጉ አድርጓቸዋል ከገዳም የሚወጡት በመጀመሪያ ወደ ገዳም ሲሄዱ በገዳም ሥራ ያለ መሆኑን ሳይረዱ ይፄዱና ከገቡ በኋላ ሠርቶ በመብላት ሳይደሰቱ ምንኩስና አስከሚቀበሉ እንደነገሩ ይቆዩና በኋላ ከመነኮሱ በኋላ ይኮበልላሱ በገዳም ያለሥራ መኖር አይቻልም ለጸሎት የተመደበው በየሰዓቱ ጸሎት ያደርሳል ምግብ የሚያበስለው ምግብ ያበስላል ከብት የሚጠብቀው ይጠብቃል ሁሉም በየተመደበበት ይሠራል ይህን የማይወዱ ሰነፎች ግን በከተማ ዝም ብሎ አባ አባ እየተሳሉ ወፍራም ደመወዝ ተከፍሏቸው ከየዋኃን ምፅመናን ትፍት በሳህን እየቀረበላቸው የሚበሉ መሆናቸውን ሲያውቁት ገዳሙን ጥለው ይኮበልላሉ መቼም ለጽድቅ በምንኩስና ከገዳም ወደ ከተማ አንደማይወጡ ግልጽ ነው በፍትሐ ነገሥት መነኮሳት ከገዳም ከወጡ ምንኩስናቸውን ትተው እንደሕዝብ ሆነው ይኑሩ ተብሎ ተደንግጓል ከዚህ ዓንፃዛር ሲታይ አሁን በከተማ እያታለሉ ያሉት መነኩሴ ነን ባዮች ሕገ ወጥ መነኮሳት አይደሉም ይባላል ወይስ ፍትሐ ነገሥት ተሳስቷል። በሌላ መንገድ ለመውጣት ቢያንስ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ማጠናቀቅ ይጠይቃል እነዚህ ሰዎች ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗን ችምህርት እንኳን በደረሰበት አያድረሰኝ እያሉ ሲያውደለድሉ የኖሩ ናቸው እንኳን አሥራ ሁለተኛ ክፍል ሊያጠናቅቁ ስለዚህ ትምህርት የማይጠይቀው መንገድ ምንኩስና ስለሆነ ምንኩስናው መርካቶም ይፈጸም አራት ኪሎ ያልተደከመበት ድግሪ ስለሆነ በቀሳሱ መነኩሴ ነኝ ብሎ መቅረብ ነው ከዚያም የውጪ ሀገር አድል ይሰጠኝ ማሰት ነው ከዚህ ላይ ትዝ የሚለኝ አንድ ነገር አለ አንድ ጓደኛችን ነበር በትምህርትም በሥራም በጣም ሰነፍ ነው ብቻ ከዚያም ከዚያም ብሎ በሚያገኘው ገንዘብ ሲፈልግ የሚገኘው ጠጅ ቤት ነው በኋላ ለአንድ ሳምንት ጠፍቶ ሰንብቶ መነኮስኩ ብሎ ቀሚስ ለብሶ ቆብ ጭኖ መጣ ከዚያ ለምን መነኮስክ ብለን ብንጠይወቀው ጓደኞቼ ሁሉ አየመነኮሱ ወደ ውጪ ሀገር ሲሄዱ እኔ ለምን አቀራሁ ውጪ ሀገር ለመሄድ ነው የመነኮስኩት አለን እነዚህ ሰዎች ይህን በማሰብ የመነኮሱትም ለሌላ ዓላማ የመነኮሱት ወደ ውጪ ሀገር የሚሄዱት በዋናነት ለሁለት ዓላማ ነው አንደኛው ለመሥራት ሰነፎች ስለሆኑ ሀገር ውስጥ ሠርተው ገንዘብ ስለማያገኙ በምንኩስና ስም በማታተልም መቼም ለሁሉ አይሳካምና ለሥልጣንም ለገንዘብም አልሳካላቸው ሲል ይህን የገንዘብ ጥማታቸውን ለመወጣት ነው ከዚያም የሚሄዱት ሠርተው ለማግኘት ሳይሆን ሰርተው ለማግኘት ተሰደው ከሄዱት ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስት አንደሚያደርጉት ከደመወዛቸው ውጪ ለቤተክርስቲያን ማሰሪያ ለገዳማት መርጂያ እያሉ ለመግፈፍ ነው የዋሁ ሕዝባችንም ለሃይማኖቱና ለሀገሩ ፍቅር ስላለው በስደት ለፍቶ ካገኘው ይሰጣል ሌላው ደግሞ በነጻነት ለማመንዘር ነው ብዙዎቹ መነኮሳት በሀገር ውስጥ ከገጠር ይልቅ በታላላቅ የሀገራት ከተሞች ይልቁንም አዲስ አበባ ኳ መኖርን ይመርጣሉ ከዚህ ባለፈ ደግሞ አሀገር ውጪ መሄድን ይናፍቃሉ ይህ ለጽድቅ እንዳልሆነ ሁሉም ያውቀዋል ታዲያ ለምን ነው ሲባል ገንዘብ ከማግኘት ጋር ለማመንዘር እንዲመቻቸው ነው በሀገራችን በተለይ በገጠር ምዕመናን በቅርበት ስለሚከታተሉዋቸው እውነተኞቹ መነኮሳት ካቆዩን የምንኮስና አኗር የተነሣም በነዚያኞቹ መንገድ እንዲሄዱለት ሕዝባችን ጫና ስለሚያደርግባቸው ተሰውረው ለማወናበድ ስለማያመቻቸው እነርሱም ነዛ ሆነው አይኖሩም በተሳላቅ ከተሞች ግን በተለይ በአዲስ አበባ በአንዱ አካባቢ ሲያመነዝሩ አድረው ውለው በሌላው አካባቢ ጻድቅ በመምሰል ሲቀድሱ ሲያስተምሩ ሲባርኩ ይታሉ ፒያሳና አራት ኪሉ ጭፈራ ቤቶች አድረው ዛደው ጥዋት ቀድሰው የሚያቆርቡ ብዙዎች አንዳሉ ብዙዎቻችን የምናውቀው ዛቅ ነው ያውም የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎች ከነዚህ ብዙዎች ገጠር አካባቢ አስገድዶ በመድፈር የወንድ ሚስት በማባለግ ሆቴል ክሴተኛ አዳሪ ጋር በማደር ተይዘው ተባረው ወደ አዲስ አበባ ገብተው የቤተክርስቲያን አለቃ ሆነው ሚኖሩ ናቸው ዛሬ በነፃነት በየጭፈራ ቤቱ ሲጨፍሩ ያድራሉ የጥቂቶችን ታሪክ በኋላ እናያለን ከሀገር ውጪ የሚሄዱትም አንዱ ዓላማቸው ይህን የዝሙት ፍላጎታቸውን በነፃነት ለመፈጸም ነው ይህ ሁሉ አነርሱን በቅርብ የሚያውቃቸው ሁሉ የሚያውቀው ህቅ ነው ለእውነተኛ የምንኩስና ዓላማ አባ ዓለም በዘዴዎች የሚመነኩሱት በሁለት ዓይነት መንገድ ነው አንደኛው ከዚህ በላይ ለዘረዘርኳቸው ነገሮች ብለው ተዘጋጅተው የሚመነኩሱት አባ ዓለም በዘዴዎች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ መጀመሪያ አውነተኛውን የምንኩስና ሮ ለመኖር አስበው ወደ ገዳም ገብተው መንኩሰው በኋላ ግን የገዳሙን ኑሮ መኖር አቅቷቸው ከገዳማቸው ወጥተው በከተማ የተሰማሩ በግብራቸው ከላይ ለተዘረዘሩት ነገሮች ብለው ከመነኮሱት ጋር የሚመሳሰሉ ናቸው እንዲያውም ምንኩስና አቅጣጫውን አንዲስትና የወንበዴዎች ጭንብል እንዲሆን በር የከፈቱ አነዚህ የገዳሙ ኑሮ አልሆንላቸው ሲል ሰይጠን ወደ ከተማ ያስኮበለላቸው መነኮሳት ናቸው በዚህ ሁኔታ ቀደም ብለው የወጡት በገንዘብ ሲበለጽጉና በሥልጣን ሲደሳደሉ ሲያይዋቸው ከገዳም የነበሩት ጎረቤቱ አሜሪካን ሀገር ሄደ መክበሩን እንደሰማ ሰው ገዳማቸውን ትተው በነርሱ ግብር ተሰማሩ በከተማ በየአብያተ ክርስቲያናት ተጠልለው የኑሮ ጉዳይ ግራ ገብቷቸው የነበሩም ሚስት ማግባት አስበው የነበሩ በመተው አግብተው የነበሩ ሳይቀሩ እየፈቱ ከገዳም የወጡት ሰልጥነው በአጭር ጊዜ ሲከብሩ አይተው ለማጭበርበርማ ከነርሱ ይልቅ በከተማው የኖርንበት እኛ አንበልጥም ብለው ነው መሰለኝ ቆብና ቀሚሳቸውን ከዚሁ ከአራት ኪሎ አያሰፋ መንኩሰናል አያሉ ተሰማሩበት በአሁኑ ጊዜ ከገዳም ወደ ከተማ ከሚፈልሱት ይልቅ በማጭበርበርና በማምታታት ስልታቸው እነዚህ ከዚሁ ቆብ ገዝተው የሚጭኑት በልጠዋል ወጣት ሴቶችን ከጎናቸው አቀፍ አድርገው ሲዝናኑም ፒያሳና አራት ኪሎ አካባቢ ከምናያቸው ወጣቶች ጋር አንድ ዓይነት ናቸው የኖሩበት ስለሆነ ከገዳም እንደወጡት የማፈርና የመንክርፊፍ ሁኔታ አይታይባቸውም ይህም በቅርብ የሚያውቃቸው ሁሉ የሚመሰክረው ጉዳይ ነው በተለይ በማወቅም ባለማወቅም ለዝሙት ሥራቸው ተሳታፊ የሆኑ ሴቶች በግልጽ የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው ባለማወቅም በማወቅም እየቀረቡ ዲቃላ እያስታቀፉአቸው ያለቀሱ ብዙ ሴቶች ስላሉ የነርሱን የማታለል ስልት ከሁሉም በላይ እነርሱ ያውቁታል የነአባ ዓለም በዘዴ አለባበስ አስቀድሞ በመጽሐፍ ቅዱስ የዮሐንስ መጥምቁን አለባበስ ከዚያም ይህን መሠረት አድርጎ በፍትሐ ነገሥት ስለመነኮሳት በተደነገገው የመነኮሳት አለባበስ ምን መምሰል እንዳለበት የተወሰነውን አይተናል ብዙ መነኮሳትም በገዳም ያንን ተከትለው እንደ ትዕዛዙ ሲፈጽሙ ረዋል ዛሬም በገዳማት ያ ዓይነት አለባበስ ይታያል ኣ በአሁን ጊዜ በከተማ የሚገኙ መነኮሳት ነን የሚሉ ዓለም በዘዴዎች ለብሰውት የሜታዩት አለባበስ ግን የምንኩስና ዓለባበስ አይደለም አለባበሱ በቀጥታ የተወሰደው ከፈሪሳውያን ነው ጌታችን በወንጌል ረሻጅም ልብስ ለብሰው መዞር ከሚፈልጉ በገበያም ሰላምታ በምኩራብም የከበሬታ ወንበር በምሳም የከበሬታ ሥፍራ ከሚወዱ ከጻፎች ተጠበቁ የመበለቶችን ቤት የሚበሉ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ እነዚህ የባሰ ፍርድ ያገኛቸዋል ብሎ አለባበሳቸውንና ግብዝነታቸውን ከነማታለያ ዘዴአቸው ትናግሮአል ሉቃ የዛሬዎቹ ከዚህ የተለዩ ከሆኑ ያየ ሁሉ ይታዘብ እነርሱ ግን መቼም ምዕመናን አያውቁም ብለው የለበስነው የምንኩስና ልብስ ነው አያሉ ያታልላሉ ለነገሩ ይህንንም ህዝብ ፊት ለመከበሪያ የሚጠቀሙበት ስለሆነ እንደዚህ ሆነው የሚታዩት በሕዝብ ፊት ነው አንጂ ከዚያ ውጪ ግን ብዙዎች ቁምጣ ነው የሚለብሱት ሰው በማያያቸው ቦታ ሙሉ ኮትና ሱሪ ለብሰው ለብቻቸው በቤት ውስጥ የሚደሰቱም ብዙዎች ናቸው እንደምንኩስና ሕግ ከሆነ ግን የምንኩስና ልብስ የሚወልቀው በጋ የተለበስው ክረምት ሲገባ ክረምት የተለበሰው በጋ ሲገባ ብቻነው የነዚህ ግን የሚለበሰው ለመከበሪያና ለዝነጣ ስለሆነ ይህን ሕግ አይመለከትም ቀን በሕዝብ ፊት የምንኩስና የሚባለውን ለብሰው ውለው ማታ በሱፍ መዘነጥ ነው አርግጥ ከምንኩስና ሥርዓት አንፃር ሲታይ ማወናበጃ መሆኑ ያሳዝናል እንጂ ጽድቅ በአለባበስ የሚለካ ሆኖ አይደለም ጌታችንም ለማታለያ ስለሚጠቀሙበት ነው የነቀፋቸው ስራቸውም አእንደአለባበሳቸው ስላልሆነ ነው ሕዝባችንም እየተታሰለ ያለሰው ጽድቅን በአለባበስ እየመዘነ ሥራቸው እንደ አለባበሳቸው እየመሰለው ነው ምስራፍ ስደስት በምገኩስና ክየተፈጸሙ ያሱ ውጡገብደናዎች ከላይ ባየናቸው ሁኔታዎች ምንኩስና አቅጣጫውን በመሳቱ የተነሳ በየከተማው በምንኩስና ስም እየተፈጸሙ ያሉ በርካታ ውንብድናዎች አሉ አብዛኛዎቹም ሕዝባችን የሚያውቃቸው ናቸው ሆቴል ውስጥ ከሴተኛ አዳሪ ጋር አድረው ማለዳ ቤተክርስቲያን መጥተው የሚቀድሱ ፒያሳና አራት ኪሎ ካዛንቺስ ጭፍራ ቤቶች አድረው ጠዋት ቤተክርስቲያን ገብተው የሚቀድሱ ቀዳሾችና የደብር አስተዳዳሪዎች መነኮሳት ብዙዎች ናቸው ። ይህ ሁሉ ብዙኃኑ የአዲስ አበባ ሕዝብ የሚያውቀው ጉዳይ ነው አሁን አሁን ደግሞ ለገንዘብ ሲሉ እየሰለሙ ቆባቸውንና የያዙትን መስቀል ለሙስሊሞች እያስረከቡ በቆባቸው ምትክ የአስላም ኮፍያ የሚያደርጉ እየበረከቱ መጥተዋል አንዳንዶቹም ከዚያ ተመልሰው በቤተክርስቲያን የሚቀድሱ አሉ አስኪ አኔ ከማውቀው ትንሸ ልጥቀስ ከምንኩስና ጠደ ከዘስፅምና በአስልምና ሃይማኖት መሪዎችና መነኩሴ ነን ባዮች ቤተክርስቲያን ሲቀድሱ በኖሩ ሰዎች በዚህ በአዲስ አበባ ከተማ የክርስትናን ዛይማኖት የሚያንቋሽሸና የሚያራክስ ድርጊት ተፈጽሟል መነኩሴ ነበርን ባዮቹ እንደሚሉት በምንኩስና በቀዳሽነት በቤተክርስቲያን አስተዳዳሪነት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከ ዓመት በላይ ያገለገሉ ናቸው አባባላቸው አውነት መሆኑን ታሪካቸው አረጋግጧል እነዚህ መነኮሳት እስልምናን ተቀብለናል በማለት ቆባቸውንና መስቀላቸውን ቀሚሳቸውን ለሙስሊም ሃይማኖት መሪዎች በማስረከብ በቆቡ ፋንታ የእስልምና ኮፍያ በሙስሊሞች ሲደረግላቸው የደረሰኝ የምስልና የድምጽ ማስረጃ ያሳያል ጥቂቶችን በፎቶ መልክ አንደሚከተለው አቅርቤአቸዋለሁ ኢየሱስ ክርስቶስንና የክርስትና ዛይማኖትን ከመ ስሊሞች በጥያቄና መልስ መልክ በማጥላላት ላይ አንዳሉ ክርስትናቸውን ክደው እስልምናን ሲቀበሉ ከሰለሙ በኋላ በደስታ ከሙስሊሞች ጋር ሊሳሳሙ ከሰለሙ በኋላ የእጃቸውንና የአንገታቸውን መስቀል ለሙሲልሞች ሲያስረክቡ ቆባቸውንና መስቀላቸውን ካስረከቡ በኋላ ከሙሲልሞች ጋረ አብረው ሲጸልዩ ን ከሙሲልች ጋር ቆመው ሙሲልሞች ከአንገታቸውና ከእጃቸው ተረክበው የወሰዱት መስቀል ነ ይህ ድርጊት በሚፈጸም ጊዜ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዛይማናትን ሳይሆን ሁሉንም የክርስትና ሃይማኖቶች የሚያንቷሽቡና የሚያራክሱ በርካታ ቃላት ከነዚህ መነኮሳት ነን ባዮችና በተለይም ከሙስሊም የዛይማኖት አስተማሪዎች ተነግረዋል ኮት ጥቂቶችን ለመጥቀስም ኢየሱስ ከኃጢአት አያድንም ኢየሱስ ፈጣሪ አይደለም ኢየሱስ እስላም ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ቃል ሰዎች የፈጠሩት የውሸት ቃል ነው መጽሐፉም ከውስጡ በውሸት የተበረዘ ነው በምድር ላይ ያለው አውነተኛ ዛይማኖት እስልምና ብቻ እንጂ ሌላው የውሸት ነው እነዚህ ሰዎች መነኮሳቱን ማለት ነው ቆሞሶች ናቸው ለጵጵስና አንድ ደረጃ የቀራቸው ናቸው ነገር ግን የያዙት ዛይማኖት ውሸት ስለሆነ እስልምናን አመኑ እያሉ የአስልምና የሃዛይማኖት መሪዎች ይናገሩ ነበርፊ ማንም ሰው የመረጠውን ፃይማኖት መከተል ነፃነት ቢኖረውም የሌላውን ፃይማኖትና ተከታዮቹን መንቀፍና ማጥላላት ግን ተገቢ አለመሆኑ ሊሠመርበት ይገባዋል እነዚህ ሰዎች ለሰነዘሯቸው ሃይማኖታችንን የማንቋሸሸ ቃላት መልስ መስጠት የሚያዳግት አይደለም ነገር ግን እነርሱ ይህን ድርጊት የፈጸሙት እንደዚህ ያሉ ሰዎች አሰለምን ብለው ከአረብ ሀገሮች ገንዘብ ለማግኘትና ዋናው ዓላማቸው ደግሞ በእስልምናና በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ግጭት ለመፍጠር ነው እናም ለነዚህ ሰዎች መልስ መስጠት የሚያዳግት ባይሆንም ቅድሚያውን ለሰላም በመስጠት የዛይማኖቱ መሪዎች ድርጊቱን የፈጸሙትን ግለሰቦች ይቅርታ እንዲጠይቁ እንዲያደርጉ መንግሥትም ድርጊቱ በሁለቱ ዛኝይማኖት ተከታዮች መካከል ግጭት ለመፍጠር የተፈጸመ ስለሆነ ሰዎቹን በሕግ እንዲጠይቃቸው ስል ቅድሚያውን ለሰላም አሰጣለሁ ይህ ካልሆነ ግን በዛይማኖታችን ላይ ለተደረገው ማንቋሸሽና ነቀፋ ተገቢውን መልስ ለመስጠት እንደምገደድ ለመጠቆም አወዳለሁ በተለይ ሰዎች ምንም ያልተማሩ ቢሆኑም ራሳቸው ብቻ ሂደው እምነቱን መቀበል ሲችሉ የእምነታችን መለያ የሆነውን መስቀል በአንደዚህ ያለ ድርጊት ከአጃቸው ተቀብለውና ካንገታቸው አውልቀው መጣላቸውና የራሳቸውን መለያ ማድረጋቸው በዝምታ የሚታሰለፍአይደለም ከምኘኩስና ጠደ ሽስልቧምና ከሽስፅምና ዉደ ምንኩስና በአንድ ወቅት በነበርኩበት ክፍለ ሀገር አንድ መነኩሴ ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ማደሪያ ስጡኝ ብሎ እንግድነት ጠየቀ በጠየቀው መሠረትም በቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ቤት ተሰጥቶት ተቀምጦ እያለ የቤተክርስቲያን ትምህርት የተማረ ስለሆነ ቅዳሴ ልቀድስ ብሎ ጠየቀ በጠየቀውም ጥያቄ ተፈቅዶለት እየቀደስ ምዕመናን እናቶች በአገልግሎት ላይ ስላዩት ፍትፍት በሳህን እያመጡ እየቀለቡት ለተወሰነ ሳምንታት ከቆየ በኋላ አንድ ቀን በአንድ ትልቅ ሆቴል ገብቶ የምንኩስና ልብሱን እንደለበስ ከሴተኛ አዳሪ ጋር አልጋ ቤት ገብቶ ይተኛል በዚህን ጊዜ የሆቴሉ ባለቤት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲቀድስ አይተውት ስለነበር ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በመተባበር ለፖሊስ ጠቁመው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ፄዶ ይታሠራል በነጋውም ቀድሞ ግንኙነት ያላቸው ኑሮ የሙስሊም መሪዎች ዋስ ሆነው ያስፈቱትና መስጊዳቸው ወስደው የቤተክርስቲያን ቅዳሴ ስለተማረ ጥሩ ድምጽ ስለነበረው አዛን የእስልምና የፀሎት ጥሪ የሚጮህላቸው ያደርጉታል ትንሽ እንደቆየም ወደ አዲስ አበባ ይመጣና እንደገና መነኩሴ ነኝ ብሎ በአዲስ አበባ አድባራት ሲዘዋወር አዲስ አበባ በመጣሁበት ጊዜ አገኘሁት አንዳንጆቹ እንደሚሉት ደግሞ በቀዳሽነት ተቀጥሮ ሲሠራ ነበር ብለውኛል ሆቴስ ጡስፕ ክሴተና ሸጻሪ ጋር ተደባጅኮ የተባረረው የደብር ከስታ በዚያችው ሴተክርስቲያን ከላይ ያየነው ታሪክ በተፈጸመበት ወቅት የነበረው የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ የነበረው ሌሳው መነኩሴ ያችኑ ቤተ ክርስቲያን እየበጠበጠና ቤተክርስቲያን የሚመጡትን ወጣት ሴቶች እያባበለ በመድፈር ተከሶ ስላስቸገረ ምናልባት ቢሻለው ተብሎ ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ለጊዜው ተዛውሮ እንዲቁይ ተደረገ በዚያው በተዛወረበት ቦታም ሆቴል ውስጥ ገብቶ ባንኮኒ ተደግፎ ሲጠጣ ለዝሙት ከጠየቃት ሴተኛ አዳሪ ጋር ተጣልቶ በጠርሙስ ጭንቅላቱን ፈንክታው በዚህም ምክንያት የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ አባረውት አዲስ አበባ መጣ ዛሬ ይህ ሰው በአዲስ አበባ አድባራት በአለቅነት እየተዘዋወረ ይሠራል የሚዘዋወረውም በተመሳሳይ ድርጊት እየተከሰሰ ነው ለዚህም ዶክመንቱ በየ አድባራቱ ይገኛል በየጭፈራ ቤቶች ከሚያድሩት የቤተክርስቲያን አለቅችም አንዱ ይህ ሰው ነው የሚገርመው ደግሞ ከላይ በጠቀስኩት ታሪክ ሙስሊሞች ዋስ ሆነው ያስፈቱት መነኩሴ በታሠረ ጊዜ አንዱ ከሳሽ አርሱ ነበር ይህ ሁሉ የሚያሳየን ምንኩስና ምን ያህል የወንበዴዎችና የሌቦች ጭንብል መሆኑን ነው ገንዘብና የሌላውን የቤተክርስቲያን ንብረት ዘረፋስ መቼም ቆጥሮ መጨረስ አይቻልም ከብዙ በጥቂቱ ከዚህ በላይ ያየናቸውን መጥቀሴ የእነርሱን ኃጢአት በመዘርዘር ጽድቅ ለማግኘት ወይም ለነርሱ የግል ጥላቻ ኖሮኝ አይደለም በምንኩስና ስም እንደነዚህ ያሉ ሌቦችና ወንበዴዎች እየበረከቱ ስለመጡ ምፅመናን ራሳቸውን እንዲጠብቁና ቤተክርስቲያንንም እንዲጠብቁ ለማድረግ ነው በመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት ጌታችን የጸሐፍትና የፈሪሳውያንን የኃጢአት ሥራ ዘርዝሮ መናገሩ ሕዝቡንና ደቀ መዛሙርቱን ለማስጠንቀቅ ነበር ሕዋርያው ጳውሎስም በተመሳሳይ ሁኔታ ተናግሯል ማቴ ሉቃ ሮሜ ምስራፍ ስባት ጽጵጵስናና መስፈርቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ጳጳስ ማለት በግሪኩ ኤሏስ ቆጳስ የሚለው ሲሆን ትርጉሙም ጠባቂ ተቆጣጣሪ ማለት ነው ሐዋርያው ጳውሎስ ጳጳሳት ኤሏስ ቆጸጳሳት የሚላቸው የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችን ነው ለቲቶ በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት የቤተክርስቲያን ኃላፊ ሽማግሌ መሾም ያለበት አንዴት ዓይነት ሰው እንደሆነ ከነገረው በኋላ ያንኑ ተቧዉሚ ሽማግሌ ኤሏስ ቆጳስ ብሎታል ቲቶ የኤፌሶን የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችንም ጳጳሳት ብሏቸዋል የሐዋ ከሐዋርያት በኋላ ክርስትና እየተስፋፋ ክርስቲያኖች እየበዙ ሲሄዱ ግን ጳጳስ ወይም ኤሏስ ቆልስ የተለየ ማዕረግ እየሆነ ሄደ ከሐዋርያት ቀጥለው ከተነሱት አበው ጆምሮ ማለት ነው ዞሮ ዞሮ የቤተክርስቲያን ጠባቂ ተቆጣጣሪ አስተዳዳሪ ማለት ነው ብቭ አዚህ ላይ ጳጳስ ወይም ኤሏስ ቆጸጳስ ማለትና መነኩሴ ማለት የተሰያዩ መሆናቸውን ለይቶ ማወቅ ይገባል ከመቹ ጀምሮ እንደሆነ ባይታወቅም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተነሱ ለሹመት ያደሩ መነኮሳት ቢሸፋፍኑትም መጽሐፍ ቅዱስ ግን ጳጳስ መነኩሴ አለመሆኑን ከነመስፈርቱ ሰይቶ አስቀምጦታል ጳጳስ እንዴት መሾም እንዳለበት ሐዋርያው በግልጽ አስቀምጦታል ለቲቶም ለጢሞቴዎስም በጻፈላቸው መልዕክት አንግዲህ ኤጺስ ቆጾስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል የማይነቀፍየአንዲት ሚስት ባል ልከኛ ራሱን የሚገዛ አንደሚገባው የሚሠራእንግዳ ተቀባይለማስተማር የሚበቃ የማይሰክር የማይጨቃጨቅ ነገርግን ገር የሆነ የማይከራከር ገንዘብ የማይወድ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር ሰው ግን የራሱን ቤት ማስተዳደር ባያውቅ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል» ይላል ጢሞ ለቲቶ በጻፈው መልእክቱም ተመሳሳይ ቃል ነው ያስቀመጠው ቲቶ ልብ አንበል በዚህ የሐዋርያው ትዕዛዝ መሠረት ጳጳስ መሾም ያለበት በአንድ ሚስት የጸናና ልጆቹን በሥርዓት ማስተዳደር የቻለ ነው እንጂ ያላገባ ይሾም አላለም በአማራጭም አላስቀመጠም ያላገባና ልጆቹን በሥርዓት መምራት ያልቻለ መሾም እንደሌለበት ሲያስገነዝብም «ሰው የራሱን ቤት ማስተዳደር ባያውቅ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል። ም መ በሲኖዶሱ እንዳይሳተፉ መከልከላቸው ብቻ አይደለም በጳጳሳት የተወሰኑትን ውሳኔዎች ለማስፈጸም ዋና ዋና ቁልፍ የሥልጣን ቦታዎች በነርሱ በጳጳሳቱ የተያዙ ናቸውፎ ሁለት ምሳሌዎች ላንሳ ቀደም ሲል ከፓትርያልኩ በመቀጠል በቤተክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ላይ የሚያዝዝ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሚሾመው ከጳጳሳት አልነበረም ያልመነኮሰም ይሾም ነበር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ያልመነኮሰ ወይም ጳጳስ ያልሆነ አንዴት እኛን ጳጳሳቱን ያዝክናል በማለት ጳጳስ ያልሆነ የቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዳይሾም ብለው ከልክለዋል ይህ የሥልጣን ክፍል በሲኖዶስ የሚወስነውን የቤተክርስቲያን ጉዳይ ሁሉ የሚያስፈጽም የሥልጣን ክፍል ነው የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞች በሙሉ የሚሠሩት ከፓትርያርኩ በመቀጠል ከዚህ ቦታ በሚቀመጠው ጳጳስ ትዕዛዝ ብቻ ነው የሀገረ ስብከቶችንም ስንመለከት በየወረዳው በየአጥቢያው የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት የሚንቀሳቀሱበት በሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ትዕዛዝ ብቻ ነው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅና ሌሎችም ሠራተኞች የጳጳሱ አገልጋዮች እንጂ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ጉዳይ ላይ የወሳኝነት ድርሻ የላቸውም ሥራ አስኪያጁ እንኳን ከጳጳሱ ትዕዛዝ ትንሽ ቢያፈነግጥ ጳጳሱ ለጠቅላይ ቤተክህነት አመልክቶ የማስቀየር ወይም ከሥልጣኑ እስከ ማስነሣት መብት አለው ከዚያም በምትኩ ራሱ የመረጠውን ስው አቅርቦ የማሾም ሥልጣን አለው ያም ፀጥ ለጥ ብሎ ካላገለገለ የዚያኛው አድል ስለሚገጥመው ፀጥ ለጥ ብሎ ይገዛል ባጠቃላይ በጠቅላይ ቤተክህነትም ሆነ በየሀገረ ስብከቱ ያሉትን የአስተዳደር ሁኔታዎች ስናይ ጳጳስ ጌታ ያልመነኮሰ የቤተክርስቲያን ሠራተኛ ደግሞ አገልጋይ ሆነው ነው የሚኖሩት ወይም አንደ ፊውዳሉ ሥርዓት ጳጳስ አንደባለ ጉልትና ባለ ርስት ሌላው ሠራተኛ እንደጭስኛና ገበሬ ሆነው ነው የሚኖሩት በጠቅላይ ቤተ ክህነትም ሆነ በየሀገረ ስብከቱ ያሉ ሠራተኞች ለጳጳስ የሚሰግዱትን ያህል ለኢየሱስ ክርስቶስ አይሰግዱም ውስጣቸው ደስተኛ ባይሆንም እንኳ ለነፍሳቸው ለኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋቸው ለጳጳስ መስገዳቸው አይቀርም ምክንያቱም ካልሰገዱላቸው ጨካኞች ስለሆነ ከሥራቸው ያባርሯቸውና በርዛብ ይገድሏቸዋል በዚህ ጉዳይ ስንቶቹን ያለበቂ ምክንያት አባረዋቸው በርዛብ እየተሰቃዩ ያሉ ስንቶች ናቸው አነዚህን በመሳሰሉት አንድ ጳጳስ በቤተክርስቲያን ያለውን የፊውዳሉ ሥርዓት የፈላጭ ቆራጭነት ሥልጣን በማየት ሰአውነተኛው ጽድቅ ሳይሆን ጳጳስ ሆነው ፈላጭ ዋቆራጭ ሰመ የሚመነኩሱ ብዙዎች ናቸው እንዲያውም ከሌላው ይልቅ ለዚህ ብለው የሚመነኩሱ ይበዛሉ ከጵጵስና ማዕረግ በታች ያሉት መነኮሳትም ቢሆኑ ቀሪው የሥልጣን ክፍል በነርሱ እንዲሸፈን እየተደረገ ነው ከጵጵስና ማፅረግ በታች ያለው ሌላው የሥልጣን ክፍል አንዱና ዋነኛው የአጥቢያ ቤተክርስቲያን አለቅነት ነው ይህ የሥልጣን ክፍል አብዛኛው የተያዘው በመነኮሳት ነው በአዲስ አበባ ብቻ ብንመለከት ከዘጠና አምስት በመቶ በላይ የቤተክርስቲያን አለቆች መነኮሳት ናቸው በአሸበረቁ የቤተክርስቲያን ሕንፃዎች መነኮሳት ብቻ እንዲቀድሱባቸው ማድረግ እልቅና ሌላ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች አንዳንድ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን ሕንፃዎች ሲሠሩ ባለትዳር ካህናት እየወጡ መነኮሳት ብቻ እንዲቀድሱባቸው እየተደረገ ነው መነኮሳት ብቻ እንዲቀድሱ መደረግ የሚገባው ቦታው መነኮሳት የሚኖሩበት ገዳም ቢሆን መልካም ነው ጉዳዩ አየተደረገ ያለው ግን አንዲያውም መነኮሳት ሊኖሩበት በማይገባው በከተማ ነው ይህ ደግሞ ምንኩስና ገዳማዊ ሥርዓቱን ለቆ አሁን እየታየ ባለው ሁኔታ በሥርዓት አልበኝነት መንገድ እንዲስፋፋ ለማድረግ እየተካሄደ ያለ ሕገ ወጥ ድርጊት ነው ሕገ ወጥ የሚያደርገው አስቀድመን እንዳየነው የቤተክርስቲያኗ የሥርዓት መጽሐፍ የሆነው ፍትሐ ነገሥት መነኮሳት በከተማ እንዳይኖሩ ስለሚከለክል ነው ፍትሐ ነገሥቱ መነኮሳት በከተማ አይኑሩ እያለ በመንኩሴ ከገዳም ዓሣ ከባሕር ከወጣ አይረባም አንዲሉ በታላላቅ ከተሞች የሚሠሩ የቤተክርስቲያን ሕንፃዎች ባለትዳር ካህናትን አያስወጡ መነኮሳት ብቻ አንዲቀድሱባቸው ማድረግ ሥርዓት አልበኝነት ነው ደግሞ አኮ ሲጠየቁ መነኮሳት ብቻ አንዲቀድሱበት የሚደረገው ቦታው ገዳም ስለሆነ ነው ይላሉ ይህም በራሱ አንድ ስሕተት ነው እንዴት ሆኖ ነው ከተማ መካከል ገዳም ሊሆን የሚችለው ገዳም ማለት አኮ በመጽሐፍ ቅዱስ አንደምናየው ሰው የማይደርስበት ምድረ በዳ ማለት ነው በግዕዙ «ወሰዶ መንፈስ ለአግዚእ ኢየሱስ ገዳመ» ያለው በአማርኛ «ጌታ ኢየሱስን መንፈስ ወደምድረ በዳ ወሰደው» ነው የሚለው ማቴ «ወበውእቱ መዋዕል በጽሐ ዮሐንስ መጥምቅ እንዘ ይሰብክ በገዳመ ይሁዳ» ያለውንም በአማርኛው «በዚያን ወራት መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ» ነው የሚለው ማቴ በነዚህ በሁለቱ ጥቅሶች ላይ ስንመለከተው ገዳም የሚለው ቃል ምድረ በዳ ተብሎ ነው የተፈታው በምንኩስና የአኗኗር ታሪክ ስንመለከትም ገዳም ማለት መነኮሳት ብቻ የሚኖሩበት ዓለማዊ ሰው የማይኖርበት ምድረ በዳ ማለት ነው ታዲያ የዛሬዎቹ ከየት አምጥተው ነው መሀል ከተማ ያሸበረቀ ሕንፃ ሠርተው ገዳም ብለው መሰየማቸው ምንኩስናው ከተሜ ከሆነ ዘንድ ገዳሙም ከተሜ ይሁን ተብሎ ይሆን። መልሱ ይሆናል ብዬ የማስበው ያው አስቀድሜ አንዳልሁት ሰነፎችና አውደልዳዮች ስለሆኑ ተግተው ስለማይማሩ ደህና ነጥብ ሲያመጡ ስለማይችሉ ነው ይህንንም እንደነርሱ በማውደልደልና ጊዜያቸውን ያሰአግባብ በማሳለፍ በኋላ ቆብ በመጫን በአቋራጭ ሥልጣን ላይ የወጡ መሰሎቻቸው ስለሚያውቁ ችግራቸውን በመረዳት በዝቅተኛ ነጥብ እንዲገቡ ፈቅደውላቸዋል አስቀድሜ አንዳልሁት ይህ ሁኔታ ሳይማሩ ሥልጣን ላይ ከሚወጡ በአንደዚህ ሁኔታ ወደ ትምህርት አንዲመጡ አድርጐ ማስተማሩ ባይከፋም በሌላ መልኩ ደግሞ ጊዜውን በዋዛ በፈዛዛ ያሳለፈ የከተማ ወንበዴ ሁሉ የምንኩስናና የክርስትና ዓላማ ሳይኖረው በዝቅተኛ ነጥብ ለመግባትና የኑሮ አማራጩን ለማመቻቸት ቤተክርስቲያንን የወንበዴዎች መናህሪያ ሊያደርጋት ይችላል የምንኩስና ሥርዓቱ እንዲህ በሥርዓት አልባነት እስከቀጠለ ድረስ መነኩስኩ ለማለት እንደሆነ ችግር የለም እንደድሮው ሁለት ሦስት ዓመት በአመክሮ ይፈተን አይባል ከፈለገ እሁድ መንኩሶ ሰኞ መግባት ይችላል አመንኳሾቹም በእንደዚህ ዓይነት ምንኩስና እንዲስፋፋ ስለሚፈልጉ ደስታቸው ነው እንኳ ልመንኩስ ብሎ ጠይቆ መንኩስና ወደ መንፈሳዊ ኮሌጅ ላስገባህ ካልመነኮስህ እድሉ አይሰጥህም እያሉ የሚያባብሉ ጳጳሳት ብዙዎች ናቸው ሌላው ደግሞ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከሚደረገው አንድ ምሳሌ ላንሳ በ ዓም የተፈጸመ ሁኔታ ነው ወደትምህርት ቤቱ ለመግባት በርካታ ትምህርት ፈላጊ ተማሪዎች ለመወዳደር በግቢው ተሰብስበዋል በዚህ ጊዜ የሚፈትኑት ጳጳሳትና ሌሎችም የቦርዱ አባላት ፈተናውን ለመፈተን ከገቡ በኋላ ቅድሚያ ለመነኮሳት በሚለው እቅዳቸው አንዳንድ ሀገረ ስብከቶች የመነኮሰና ያልመነኮሰ እያደረጉ ልከው ስለነበር የሀገረ ስብከቶችን ስም እየጠሩ የመነኮሰውን እየተቀበሉ ያልመነኮሰውን ቦታ የለህም በማለት በፈጸሙት ግፍ ብዙዎቹ የተማሩት የቤተክርስቲያን ልጆች እድሉን እናገኛ ለን ብለው መጥተው በአዲስ አበባ ከተማ ለአንድ ወርና ለአሥራ አምስት ቀናት ከተጉላሉ በኋላ በእንደዚህ ያለ ግፍ ሲከለከሉ እያለቀሱ ሄዱ ብዙዎቹ በእምነታቸው ያልፀነ ስለነበሩ በብስጭት አምነታቸውን ሰወጡ እኔም በወቅቱ ከዚያ ስለነበርኩ የብዙዎች በርሃብ መሰቃየትና በዕለቱ ያነቡት እንባቸው አስከአሁን በውስጤ ስላለ ምንኩስናን ለማስፋፋት አየተፈጸሙ ካሉት ብዙ ግፎች አንደምሳሌ አነሳሁት ይህንን ድርጊት የፈጸሙት በዋናነት በወቅቱ የነበሩት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ጳጳስ ናቸው እንዲያው ለምሳሌ እነዚህን በዋናነት አነሳሁ አንጂ ምንኩስናን ለማስፋፋት እየተፈጸሙ ያሉ ድርጊቶች እነቪህ ብቻ አይደሉም ካልመነኮስህ ሥራ አትቀጠርምየትምህርት አድል አታገኝም ብትመነኩስ ግን እድሉ ይስጥዛልወደ ውጪ ሀገር አልክዛሃለሁየቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ አደርግሃለሁ አያሉ በመስበክና ማባበያ በመስጠት ሄያ ዓመት ያልሞላቸውን ሕፃናት ሳይቀር እያባበሉ የሚያመነኩሱ ጳጳሳት አሉ ይህ ሁሉ ነው እንግዲህ ምንኩስና ፈሩን አንዲለቅ ያደረገው አንደዚህ የሚያደርጉት በወንዶችን ብቻ አይደለም ወጣት ሴቶችንም አያታለሉ ገዳም ይዝፔሽ ልሂድ እያሉ ለነርሱ በሚመቻቸው ገዳም አሰንብተው መንኩሺ ብለው ቆብ አስጭነው መነኩሴ ናት በሚል ሰበብ አንደ ቅምጥ አድርገው ይዘው የሚናሩ አሉ በነገራችን ላይ አሁን አሁን ሴቶች መነኮሳትም በማታለሉ ሥራ እየተሳተፉ ናቸው ለወንዶች መነኮሳት እናንተ ከምትመጡ እኛ አንምጣላችሁ ብለው ነው መሰለኝ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አካባቢ ውብ ውብ የሆኑ ሴቶች መነኩሴ ነን እያሉ ቆብ ጭነው ከጳጳሳቱና ከሌሎችም መነኮሳት ሥር ሥር ሲሄዱ ይታያሉ ሆኖም ግን ከዚያው ከወንዶቹ መነኮሳት በመጠጋት ገንዘብ ለማግኘት እንጂ በክህነት ስለማያገለግሉ ምዕመናንን ሰማታለል እስከ አሁን የወንዶችን ያህል በሴቶች የጎላ ነገር አይታይም ወደፊት እንጃ እንጂ ጠደ ፊት ምገኩስናኘ ስስመስክቶ የደራሲው ዓሳማና ራስደ በመጽሐፍ ቅዱስም በፍትሐ ነገሥትም አንደተገለጸወ ምንኩስና የፈቃድ ቢሆንም ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው በትዳር አጋር ፍቅርና በልጅ ፍቅር ልቡና ሳይከፈል አንድ ልብ ሆኖ አግዚአብሔርን ለማመስገንና ወንጌልን ለመስበክ ከጋብቻ ያለ ጋብቻ መኖር መልካም ነው ቆሮ ስለዚህም ምንኩስና አያስፈልግም ሳይሆን ወንጌልን መሠረት አድርጐ የሚሰተካክለው ተስተካክሎ የሚሻሻለው ተሻሽሎ ከዘመኑ ጋር አብሮ በሚራመድ መልኩ ቢሆን ነው የደራሲው ዓላማ ለዚህ የሚከተሉት አደረጃጀቶች ቢኖሩት እመኛለሁ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ተግባራዊ ለማድረግም አጥራለሁ ገዳማዊ አደረጃጀት እና የመነኮሳት አኗኗር የአመክሮና የትምህርት ገዳም በዚህ ገዳም ውስጥ ወንጌልና ወንጌልን መሠረት ያደረጉ የቤተክርስቲያን ትምህርቶች የሚሰጡበትና ዘመናዊ ትምህርትም አብሮ የሚሰጥበት ለመመንኮስና ወይም ለመማር የፈለጉ ምዕመናን የሚኖሩበት ማድረግ ከዚህ በኋላ በመንፈሳዊና በሥጋዊ ትምህርት አዕምሮአቸው እንዲያድግ ማድረግ በዚህ ገዳም ውስጥ ከተማሩ በኋላ በምንኩስና አንኖራለን ለሚሉና ከዚያ ወጥተን ትዳር መሥርተን ቤተክርስቲያንን እናገለግላለን ለሚሉ ምርጫ መስጠት በትዳር ተወስነን ቤተክርስቲያን እናገለግላለን ለሚሉት ቤተ ክርስቲያንን በስብከተ ወንጌል በአስተዳደርበልማት ወዚተ የሚያገለግሉትን ተጨማሪ ትምህርትና ሥልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታዎች በማመቻቸት በትዳር የሚወስኑበት አቅም በመፍጠር ቤተክርስቲያን በየተሰጥኦቸው ተሠማርተው እንዲያገለግሉ ማድረግ የተሻለ ይሆናል የምናኔ ገዳም ይህ ገዳም በአመክሮና በትምህርት ገዳሙ ውስጥ ሳሉ ከዚህ በኋላ በምናኔ በምንኩስና አንኖራለሁ ብለው ለመረጡ ተጨማሪ ወንጌልን መሠረት ያደረገ ሐዋርያዊ የምናኔ ትምህርት ተሰጥቷቸው በምንኩስና ራሳቸውን ወስነው በገዳሙ ውስጥ በትምህርት በጸሎት በልማት ተሠማርተው አንዲኖሩና ከሹመት ከገንዘብ ካስተዳደር ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው ገንዘብ በአጃቸው ሳይሰጣቸው ቤተክርስቲያን ቀለባቸውንልብሳቸውን እንዲሁም ለሌሎች ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ወጪ ሁሉ እየሸፈነች ከገዳማቸው መጥተው በማያድሩበት ሁኔታ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በማስተማር ብቻ ቤተ ክርስቲያን እንዲያገለግሏት ማድረግ ጌታች ወንጌልን መስበክ ከመጀመሩ በፊት በገዳም ተፈትኖ ሰይጣንን ድል አድር» ትምህርቱን አንደ ጀመረ መነኮሳትም በገዳማቸው በወንጌል ታንጸው ሰይጣንን ድል አድርገው ከዚያ በኋላ የወንጌል ሐዋርያ ቢሆኑ ዓለም አታሸንፋቸውም ገዳማት በወንጌል ትምህርት ስላልታነጹ ነው ከአሁን በፊት ምንኩስና የወንጌል መስበኪያ ያልሆነው እናም ከእንግዲህ ገዳማት የወንጌል መስበኪያ መሆን እንዳለባቸው ምኞቴና ራፅዬ ነው የሴቶች ገዳምም ተመሳሳይ አደረጃጀት እንዲኖረውና ተምረው በልማትበትምህርት ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ ማድረግ በዩ ምስራፍ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ የቤተክርስቲያኗን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በበላይነት የመምራትና የመቆጣጠር ችግሮች ካሉም የመፍታት ኃላፊነትና ስልጣን ያለው ይህ ሲኖዶስ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀውና የማይካድ ሐቅ ነው ሆኖም ይህ ሲኖዶስ የተሰጠውን ኃላፊነት ተወጥቷል ለማለት ከማያስደፍርበት ደረጃ ላይ እንዳለ ቤተክርስቲያን ያለችበት ሁኔታ በቂ ምስክር ነው ይህ ሲኖዶስ ኃላፊነቱን ቢወጣ ኑሮ የቤተክርስቲያኗን ችግር እፈታለሁ የሚል ሌላ አካል ባልተነሳም ነበር ቤተክርስቲያንም እንዲህ ግራ ከሚገባ ደረጃ ላይ ባልደረሰች ነበር እፄም ይህ ሲኖዶስ ችግሩን ቢያስተካክልና ቢቆጣጠር የበቀል አርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ለጥያቄዎቼ ቀና መልስ በመስጠት የቤተ ክርስቲያንን ችግር ለመፍታት ቤተክርስቲያን አንዳስተማረችኝ የበኩሌን አስተዋጽኦ እንዳደርግ እድሉ ቢሰጠኝ ኑሮ አንደዚህ ዓይነት ጽሑፍ መጻፍ ባላስፈለገኝ ነበር ነገር ግን ጩኸቴን የሚሰማና ችግሩን ከማስተካከል ይልቅ የስዎችን ጥያቄ በሰዎች ላይ የበቀል አርምጃ በመውሰድ መፍታት በሚለው ጸረ ወንጌል በሆነው ከነገሥታቱ ተወርሶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሥር ሰዶ በቀረው ፊውዳላዊ አስተሳሰብ በመመራት ጥያቄዎቹን ከመስማት ይልቅ በእኔ ላይ እርምጃ በመውሰድ ጩኸቴን ለማፈን በመመከሩ እንዲህ በይፋ ለመጻፍ ተገድጃለሁ አሁንም ጽሑፌ በዚህ ብቻ ስለማያበቃ ሌሎች ጽሑፎችን ከማውጣቴ በፊት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለሲኖደሱ አቀርባለሁ ጥቄዎቼን ሰምቶ ተገቢውን መልስ የሚሰጠኝ ከሆነ እንደዚህ ያሉ ጽሑፍ መጻፍ የቤተ ክርስቲያኗን ችግር ይፈታል ብየ አላምንም ጥያቄዎች ጥያቄ ክፍል አንድ አስቀድሜ በዚች መጽሐፍ ከዘረዘርኋቸው ስለምንኩስና ክሚናገሩ የሥርዓት መጻሕፍትና ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ሌላው ቀርቶ ከቃለ አዋዲሁ ጭምር አንዛር ሲታይ አሁን እየተፈጸመ ያለው የምንኩስና ሁለንተናዊ ሁኔታ ልክ ነው ወይ ልክ ካልሆነስ ሲኖዶሱ የማያስተካክልበት ምክንያት ምንድን ነው።