Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
መ አጥቢያ አለጥቢያ ዓለማየሁ ገላጋይ ዓመ ዓው ሠ ሬ የአፍንጫውን ደም ለማቆም ቀና አለ እንደሱረት ሱሰኛ በእፍንጫው ደጋግሞ አየር ሳበ ያንተ አውነቅጐ አለ አባቴ ፊቱን ሳይመልስ እንደ ቶልስቶይ መሬትህን ለብኩናን አከፋፍልና በድህነት ባቡር ፌርማታ ላይ ሙት ልትለኝ ነውገየ ይሄ የደሃ ቃልቻ ስብከት ነው ተፈጥሯዊው ህግ እንዲገሰስ አማላጅ ሆፔ አልመጣም አለ ሙሉጌታ ምን ማለቱ እንደሆነ ለኔም አልገባኝ አባቴ ግን የተግባባ ይመስላል በማሸሟጠጥ እውነት ትሆን ይሆናል መንገድ ግን አይደለህም አለው እኔ ላንተ እውነትም መንገድም ነኝ አለው ግራ ተጋባሁ በልሳን የሚነጋገሩ መሰለኝ በዚህ መካከል አባቴ ረጋ ባለ ድምጽ አርጥባን ወደ መኝታ ቤትሽ ግቢ አለኝ አትገባም ሲል ሙሉጌታ በሙሉ ስልጣን ተከላከለ ጉዳዩ እሷንም ይመለከታል መባሕውልር መቁ መመ አባቴ ጀርባውን እንደሰጠ ዝም አለ ፍርሃቱን ጭንቀቱን መረታቱን ሁለመናውን ፊቱ ላይ ላለማስነበብ ሆኖ ተሰማኝ ግን ምን። ሰል እራሴን ጠየኩ ሙሉጌታ መናገር ጀመረ «እኔ ቢለወጡ ደስ የሚሉኝ ግን እውነት በመሆናቸው ብቻ የተቀበልኳቸው ብዙ የኋላ ታሪኮች አሉኝ ለምሳሌ የሸርሙጣ ልጅነቴ እናቴ አያቴ አውቆ አእስኪያባርራት ድረስ መቆሚያ ጣቢያ የምትቆም ሴተኛ አዳሪ ነበረች በእውኔ ስትቆም አይቻት ባላውቅም አሁንም የብርሃን ዘንግ መስላ እንደቆመቾ በህልሜ ትመጣለች ይሄን አውራ ጣቴን ያወረሰኝን ባለቀይ አውራ ጣት ዘማች አባቴን ባላውቀውም ስለውርስ አውራ ጣቱ ምስጢር አግኝቼ ብጠይቀው እአመኛለሁ እውነት ነውና ምን ላድርገው። ወዴት ነው የሚሄዱት።
ለንዳይልጠርኝ ለለምፍታ የተወጠረው አካሌ ሲረግብ ተሰማኝ ወደ ማስታወሻ አንድ ሐሳብ ተጫጭኖኝ ከአልጋዬ ተነሳሁ እንዲህ ያለ ስሜት ሲያድርብኝ አባቴ ዕድሜ ላይ ሮጩ የደረስኩበት ይመስል እኩያነት ይሰማኛል የወትሮው ባህሪዬ እንደደመና ተገፎ ግጥጥ ያለ አውነት ግንባሬ ላይ ይወጣል ይሄን የአዘቦት ባህሪዬን አባቴ በዘዴ ያልፈዋል አብዛኛውን ጊዜ ከተጫጫነኝ ሐሳብ የሚያወጡኝ የአነጋገር ፈሊጦች አሉት «ከአባት ጋር መፋጠጥ ለሴት ዝንጀሮ ማን ሰጣትሆ የወንድ ዝንጀሮ ድርሻ ነው ንግግሮቹ ድንገተኞችና ያልተጠበቁ ስለሚሆኑ የእውነቴን ጨረሮች አቅጣጫ ይስታሉ ሳልወድ በግድ ቧልታዊ ንግግሩን የማግፃመናተል ባተሌነት ይጠናወተናኛል እውነቴን እኮ ነው ታፌ አለዋለሁ አባቴን ለምን ታፌ እንደምለው አላውቅም ስሙን አሳጥሮ መጥራት መቼ አእንደጀመርኩም አላስታውስም ምናልባት ገና ኮልታፋ እያለሁ ለአጠራር ስለማያዳግት ያኔ ጀምሬ በዚያው ቀጥዬ ይሆናል አንዳንድ ጊዜ ጥሩ ስሜት ሲሰማኝና መቃለድ ሲያምረኝ ታፈሰ ሀብቱ ብዬ በሙሉ ስሙ እጠራዋለሁ ይሄኔ ፊቱ መስመር ሳያወጣ የውስጥ መፍነክነኩን እየገለጸልኝ እርጥባን ታፈሴ ሲል ሙሉ ስሜን ጠርቶ ብድሩን ይመልሳል አንዲት ዝንጀሮ ለአባቷ የምታቀርበው እውነት ይኖራታል አቀራረቧ ግን ከወንዱ ዝንጀሮ ይለያል ይለኝና «መጀመሪያ የሌሊት ልብሷን ትቀይራለች ብዙ ጊዜ ቤት ውስጥ ቁርስ መብላት እአያሰኛትም ስለዚህ ሬስቶራንት ሄዳ ብርሃናማ በረንዳ ላይ አባቷን እያጎረሰች ጥያቄዋን ታቀርባለች አባት ጉርሻውን እየተቀበለ ጥያቄውን ከቻለ ይመልሳል ካልቻለ ብቸኛ የበላዩ ለሆነው ለእግዚአብሔር ሪፈር ይጽፋል ቁርስ ላይ እስከንቀመጥ መንገዱ ሁሱ ለዛ ያለው ቀልድ ነው አልፎ አልፎ ፀጉራም ቀይ እጁን ከመኪናው መሪ ላይ እያነሳ አንገቴን ዳበስ ያደርገኛል ይሄ የአባቴ ድርጊት ለእኔ ትልቅ መልፅከት አለው የመመካትና በሰዎች የመታጀብ ስሜት ያሳድርብኛል እዚህ ባለአስራ አንድ ከፍል መኖሪያ ውስጥ እኔና እሱ ብቻ ዓለማየሁ ገላጋይ መ ከሰራተኞቻችን ጋር የመኖር መገለል የሚፈጥርብኝ ነጠላነት በዚህ ሰዓት ፈጽሞ ይወገዳል ጥያቄዬ የመነጠል የባይተዋርነትና ሰወየመናፈቅ ከሆነ ምላሽ አገኝና ምን አንደምጠይቀው ግራ ይገባኛል ብዙ ጊዜ ግን ተስፋ መቁረጥ ተጫጭኖናኝ ነው አባቴን የማገኘው አንድ ቀን ለምንድነው የምማረው። አለኝ ቀይ ፊቱ ላይ ያነበብኩት ደግ ነገር አልነበረም «ድህነትን ኤከስፒሪያንስ ማድረግ በልምድ ት መሞከር የሚያስቅ ነገር ነው የሌብነትን የተዋረደ ስሜት ለማወቅ ለመስረቅ የመሞ ት የ ሪቅ ሞከር አይነት የሚያስቅ ምንም ሳያናግረኝ ስድስት ኪሎ አድርሶኝ ዓለማየሁ ገላጋይ ሙግ ከሰዓት ሰኋላ ዶከተር ማርቆስ እንደዘበት በአጠገቤ አያለፉ አባትሽ አብዷል በልጄ ጉዳይ ከገባህ እገድልሃለሁ ይላል አሉኝ ፍርሃት ያነበብኩባቸው መሰለኝ ከመደንገጤና ከሣሰቤ በፊት ሳቄ ነው የመጣወ ከልከ በላይ ቁመት የተሰጠው ሰው ከልክ በላይ ሲፈራ አስቂኝ ይሆናል ዛሬ ግን ቁርጥ ጉዳይ መጥቷል ለዚህ ነው ሐሳብ ተጫጭናኝ ካልጋዬ የተነሣሁት አሁን ከአባቴ ጋር ልጋፈጥ የተዘጋጀሁበት ጉዳይ በአባቴ እንዴት እንደሚስተናገድ አውቃለሁ ግራ እጁ ላይ እንደሚያስረው ወርቅማ ሰዓት ይግማል ደረቱ ላይ እንዳለው ሀብል እሳት ይደፍቃል ከዚያ ከታገሠኝ ያሸሟጥጠኛል ካልቻለም ኃይለ ቃል ይናገረኛል ይመታኛል ብዬ ግን አልጠረጥርም ከአባቴ ጋር ያጋፈጡኝ ዶከተር አይነህሊናዬ ላይ ተጋረጡ የመመረቂያ ጥናቴን ለመስራት በአማካሪነት የተመደቡልኝ ፅለት ቢሮአቸው ሄድኩ በሩ ላይ የሶሲዮሎጂና የሶሻል አትሮፖሎጂ ትምህርት ከፍል ኃላፊ» የሚል ተለጥፏል ስገባ ያኮረፉ መስለው «በምን ላይ ለመስራት አሰብሽኦ አሉኝ ለምን እንደመጣሁ ሳይጠይቁኝ ማወቃቸው አንድ ነዝር አንድጠሪጥር አደረገኝ ነገርሸተተኝ «በልመና ላይ» አልኳቸው ለወራት ያንገዋለልኩት ርዕስ ነበር እ ብለው ወደሚያነቡት መጽሐፍ አቀረቀሩ አማከሩኝ ሳይሆን አዝለው አድርሱኝ ያልኳቸው ያህል ተሰማኝ ፊቴ ላይ የጋረጡትን የተወጠረ የአናት ላይ አብረቅራቂ ቆዳ ተንሸራታች ማሽን እንደተገጠመለት ሁሉ ወደኋላ ጎትተው አኩራፊ ፊታቸውን ደቀኑብኝ ዶከተር ማርቆስ ቢሮአቸው እንግዳ ሲመጣ እንደስስታም ሰው ለምን እንደሚያኮርፉ አይገባኝም በሩ ሲንኳኳ «ይግቡ አይሉም ሲከፈት ቀና አይሉም ቀና ሲሉም ቁጭ በሉ አይሉም እንዲያውም እንግዳውን የሚያውቁትም አይመስሉም በተደናገረ ፊት አያዩት «ምን ነበርኦ» ይላሉ ዶከተር ከፍል ውስጥ እንደዚያ አይደሉም ሲያስተምሩ የሁሉም የቅርብ ጓደኛ ይሆናሉ በስም ለይተው ይጣራሉ ይሄን የለመደ ተማሪ ቢሯቸው ሲመጣ በሚያየው ፊት ይምታታበታል ሲፈትኑ ደግሞ ሌላ ናቸው ሁሉንም ያለአመሳሶ የሚጠሉ ይመስላሉ ተ ው አጥቢያ እ አሉ ደገሙና ልመና ላይ ብዙ ተሰራበት ሌላ አስቢ አቀረቀሩ ልስን አናታቸውን ጋረጠብኝ ልወጣ ስል ቆይ የሚል ልምዝግዝግ ቃል ጀርባዬ ላይ ልከከ አለብኝ ሸዝገኝ ስዞር ቆመው ነበር ቁጭ ሲሉ አጭር ይመስላሉ ሲቆሙ ባለሶስት ቅልጥም ቁመት ይሆናሉ በሰዎች መካከል ሲሄዱ ለሳቸው ብቻ በተዘጋጀ ድልዳል ላይ የሚራመዱ ይመስላሉ ቁመቴ ከማይደርስበት መንደርደሪያ ላይ አገላብጠው አንድ መጽሐፍ አነሱ ለጥቂት ጊዜ ያጠኑት መሰሉሱና አቀበሉኝ ውሰት ነው ይሄንን አንብበሽ ስትጨርሺ በጥናትሸ ላይ እናወራለን አሉኝ መጽሐፍ ሲያውሱ ሁኔታቸው የአራጣ አበዳሪ ነው መጽሐፉ ቭዘ ሲቲ ኦፍ ጆይ በሚል ደማቅ ዓይኖቹ አሻቅቦ የሚያየኝ መሰለኝ ለሶስት ቀንና ሌሊት አንብቤ ጨረስኩት ርፅሱ ብርሃናማ ነው ይዘቱ ግን የድህነት እኝኝ ብላ» ነው «የፈንጠዚያ ከተማ ሲባል የትኛውም አንባቢ መልካም ነገር ለማንበብ ይዘጋጃል ምናልባትም ምርጫው ያልሆነውን ርዕሰ ጉዳይ እንዲያነብ ይገደድ ይሆናል ደራሲው ህንድ ካልካታ ከተማ ውስጥ የፈንጠዝያ ከተማ» የምትሰኝ መንደር ውስጥ የሚኖሩ ድሆች አነጋግሮ የፃፈው ነወው ድሆቹ በዚህ ላይ የሥጋ ደዌ ተጠቂም ናቸው በተጨማሪ ፈረስ ተከተው ጋሪ የሚጎትቱ የጋሪ ፈረሶች መጽሐፉ ጭንቅላቴን ከፉኛ ተጫጫነው ጥቂት የህንድ ሀብታሞች ወደፊት ለመስፈንጠር ሲሉ በመቅዘፊያዎቻቸው ወደኋላ ያሸቀነጠሩዋቸው ድሆች በሽተኞች መፃተኞች የተትረፈረፈ ሕይወቴን በጥርጣሬ እንድመረምር ያደረገኝ መጽሐፍ ነበር ቀጥ ያለውን የሽሮ ሜዳ መንገድ ሳይ እነዚህ የካልካታ ሰዎች በፈራረሰ አካላቸው ጋሪያቸውን እየጎተቱ ተሳፋሪዎቻቸውን ጭነው የሚመጡ መሰለኝ ሰው አንዴት ከከብት እረከሶ ከብት ይተካል ዶከተር ማርቆስ ቢሮ እንደገባሁ ምን ነበር። ታውቂው የለም ስለነሴ ድሆች ፅጣ ፈንታ ታጠኘያለሽ ምን አይነት ሕይወት እንዳላቸው ገቢያቸው ምን እንደሆን የሚዛወሩበት ባቤ ለኑሮዋቸው ያለው ተጽዕኖ ሌላውንም ነገር መስማማቴን ሳያሪጋግጡ የጥ ኩን አጭር መግለጫ በዚህ ሳምንት ይዘሽልኝ ነይ አባትሽጋ ብዙ መረጃዎችን ታዛ ለሽ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት አዚያው መንደሩ ውስጥ ቤት ተከራይተሽ ለመኖር ትወስፒ ህጉ ነው ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ ነው ምት አስተየልኣቸው ከዚህ ቀደም ዶከተር አባቴን የፈሩ የመሰለኝ ተሳስቼ ኖሯል ሀሳባቸው መሰጠኝ በዓላማው ማሎ የጋመ አሣት ውስጥ የሚጣድ ተራወታደር ሆንኩ እንደ ካልካታዎቹ የጋማሰዎች ሰረገላዬን ለመጎተት የፈራረሰ ሁ አ ተክ አንደተጣንኩ ጎብደድ ብዬ ከአልጋ ወረድኩ እንዲህ ያለ ስሜት አጥንቴን ለምጦ ሥጋዬን ደፈጣጥጦ ከዕድሜ መግፋት ጋር መሣለመሣ ያቆመኛል ሌክ አጥቢያ አዛውንቶች ስመለከት የኔ ስሜት የተጫጫናቸው እንጂ ዘለግ ያለ ዕድሜ የኖሩ አልመስልሽ ይለናል አባቴን ከማግኘቴ በፊት ሁኔታዬን ለመሰለል ወደ ቋሚ መስታወት ጠጋ አልኩ የመስታወቱ ከፈፍ እንደ ፀደቀች ነፍስ በወርቃማ ብርሃን ከበበኝ ሮዝ አበባ ያካፋበት ቢጫ የሌሊት ልብሴ እንደምቀኛ ወዳጅ የፊቴ መጠውለግ ያስደሰተው ይመስላል የጉንጮቼ ወደ ወስጥ ማፈግፈግና የፊቴ አጥንት በጥቂዞ ማፍጠጥ የአባቴ የሕይወት ዱካ አንድ ትውልድ አልፎ መታተሙን የሚያረጋግጥ ይመስለኛል ከዚያ በተረፈ መልኬ የአባቴ ተቃራኒ ነው የአባቴ ዓይኖች የከልስ ናቸው የእኔ ግን ጥቁር የአባቴ ፀጉር የክልስ ነው የእኔ ግን ወደ አበሻነት ያዘነበለ መካከለኛ ነው በተለይ በእዚህ ሰዓት ዓይኖቼን ስመለከታቸው ከአባቴ ይልቅ ከፋት የሚነበብባቸው ይመስለኝና ስሜቴን ለማርገብ እሞከራለሁ የመኝታ ክፍሴ በር ተንጓጓ ማን እንደሆነ አውቃለሁ ቦቹ ነበር ቦቹ ውሻዬ ፀጉራም ድንክ የሳሎን ውሻ መኝታ ቤቴን የሚደፍረው እሱ ነወ አባቴ እንኳን ግድ ካልሆነበት በራፉን አይረግጥም መምጣት ግድ ከሆነበት በእጅ ይቆረቁርና ወደ ሳሎን ይመለሳል ቦቹ ግን ይሉኝታ በማያወቅ አፈጣጠሩ መጥቶ በሬን በጭራው ማወናወን ያንኳኳል ብዙ ጊዜ አባቴ ሳሎን ቆሞ እኔን የሚጠብቅ ከሆነ ነው ቦቹ በሬን የሚደበድበው ቦቹ በፀጉር የተሞላ ፊቱ ላይ ጭልጭጭ የማሚሉ ጥቋቁር የብርሃን ኩሬዎች አሉት ጆሮው ወገቡን እንደተመታ አባብ ይላወሳል እንጂ አይቆምም የሚገርመኝ ስሜት የማጥናት ችሎታው ነው ከተቆጣሁ ጣቢያው የተሳሳተ ሬዲዮ ዓይነት ድምጽ እያሰማ ፊቱን ይሸፍናል ስሜቴ ከተነቃቃና ጨዋታ ካማረኝ ደግሞ ይቀበጣል አግሬን እጄንና ያገኘውን አካሌን ሁሉ ከማመም ይልቅ ሳቅ በሚያመጣ አኳኋን ይነክከሰኛል ይሮጣል ይደበቃል ድንገት ብቅ ይላል እንስሳ መሆን ያማረኝ ቀንና አባቴ ቤት ውስጥ በሌለበት ሰዓት ሳሎን ውስጥ ከቦቹ ጋር አሯሯጣለሁ አደበቃለሁ ድንገት ብቅ አልበታለሁ አንድ ቀን ውሻውን ባወጣሁለት ስም ስጠራው ሰምቶ ለምንድነው የደሃ ሥም ያወጣሸለት። ያም ሆነ ይህ ከእኔ ጋር ግንኙነት ያላቸው ድሆች መ ደ እንድትሰሪ አልፈቅድም ከተማው በድሆች ምንጣሮ ላይ ንዱ ጠጋ ብለሽ ጥናትሽቨን ስፈ ብሎ ፊቱን ወደ በሩ መለሰ ወደፊት ከላካቸው ቃላቶች ወ ቶት ውስጥ ጥቂቶቹ ወደ አባቴን ሸኝቶ ወደኔ ተመለሰ ነላ ቀሩ ምን አይነት ዕዳ ቦቹ ዓለማየሁ ገላጋይ መ ሁለት ከሌሊት ልብስ ያልተሻለ የስፖርት ቱታ ለብሼ ከመኝታ ቤቴ ወጣሁ ቦቹ በሩን ስለዘጋሁበት እዚያው ሆኖ አለቀሰ ሰራተኞቹ ይከፈቱለት ብዬ የሳሎኑን ደረጃ ትቼ በጓሮ በር ብቅ አልኩ ፊት ለፈት ያለው የመኪና ማቆሚያ ውስጥ አንድ መኪና ብቻ ቆማለች ግቢያችን አጥሩ ረዥም ከመሆኑ የተነሳ ፀሐይ እንኳን እንደልቧ አትገባበትም በውስጥ በኩል የአጥሩን ግንብ እየታከከ ከፍ ያለ የድንጋይ መደብ ተበጅቷል መደቡ ሆዱ በለም አፈር ተሞልቶ አበቦች ተተከለውበታል የፈዘዙት ሽማግሴ ዘበኛ እነዚህ አበቦች ላይ ተደፍተው ሲነቅሱ ይውላሉ አሳቸውን የምቆጣጠር እንዳይመስላቸው ብዬ አበቦቹን ቀረብ ብዬ አይቼ አላውቅም እኔን ሲያዩ በመሽቆጥቆጥ ኮፍያቸውን ከጭንቅላታቸው ላይ እንደ በግ ቆዳ ይገፋሉ እንገቴን ቀንጠስ አድርጌ አልፋለሁ ለእፒህ ሽማግሌና ለአባቴ ሾፌሮች ስል ግቢያችንን ጠልቼዋለሁ ሾፌሮቹ በፈረቃቸው ሰዓት ከፈዘዙት ሽማግሌ ጋር በሹከሹከታ ያወራሉ እኔ ወደ ግቢው ከወጣሁ መኮንኑን እንዳየ ተራ ወታደር በመሽቆጥቆጥ ስሜት ሰላምታ ያቀርባሉ ይጨንቀኛል ወሬያቸውን አቁመው የጎረሰውን ሳይውጥ እንደተያዘ ወጥቤት አፋቸው እንደተከፈተ ከንፈሮቻቸውን ገጥመው ወደ ሌላ አቅጠጫ ያያሉ አባቴ ቤት ውስጥ ከዋለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ እንደተሳቀቁ ይውላሉ ስለዚህ ወደግቢው ለመውጣት ይከብደኛል አባቴእነዚህን ሰዎች ከምንም እንደማይቆጥራቸው አውቃለሁ ቀሰስተኛው ዘበኛ አባቴን ሲያዩት ቀስ ብለው የጨርቅ ኮፍያቸውን ከጭንቅላታቸው ላይ ይገሸልጣሉ ከዚያም አጃቸውን እስከ ኮፍያቸው ደረታቸው ላይ አመሳቅለው ወገባቸው እስኪታጠፍ አጎንብሰው ሰላምታ ይሰጣሉ አባቴ ልብ አይላቸውም ወሬ ከያዘም ለአመል አንኳ አያደናቅፍም ሾፌሮቹም ከዚህ የተሻለ ትኩረት ከአባቴ አያገኙም እንዲያውም አንዳንዴ አባቴ መኪና ውስጥ እኔ ኖሬ ድንገት የቤተሰብ ጉዳይ ከተነሣ መንገድ ሳይ ያስቆምና ሾፌሩን አስወርዶ እሱ እየነዳ እንሄዳሰ በእንዲህ ያለ ጉዳይ አባቴን ወቅሼ አላውቅም ያለበት የሥራ ጫና ለጥቃቅን ጉዳይና ለጥቃቅን ሰዎች ትኩረት ለመስጠት የሚያበቃው እንዳልሆነ አውቃለሁ አሱም አዘውትሮ ወደፊት የዚችን አገር ዕጣፈንታ ከሚወስኑት ጥቂት ሰዎች ውስጥ አንዱ እሆናለሁ ቀጥሎ እንቺ እልጋ ወራሼይላል ማሬ አን ወደ አሎምፒያ መብራት የሚያወጣውን ቀጭን ኮሮኮንች ት ይሄ መንገድ ምቾት አይሰጠኝም ጭር ያለና በብዙ መኖሪያ ቤቶች ቅርጫ የገባ ነው ጭርጭር ዶከተር ማርቆስን ቢሮአቸው አገኘኋቸው ለልማዳቸው ያህል ባኮረፈ ስሜት ኅምን ነበር። አባትሽ እሱ ቦታ ላይ ጥናት እንዲሰራ አይፈልግም ዶክተር ላይ ባሳደርኩት ስሜት ፀፀት ተሰማኝ እኔ አእንጃ ሌላ አማራጭ አለ ቀና ብለው በትዝብት ተመለከቱኝ «ማለቴ ከጦር ሜዳ የሸሸ ወታደ የሚያድርበት ስሜት ተሰማኝ «ማለትሽ ገብቶኛልኑ የተቆጡ መሰለኝ ከእንግዲህ አንቺ ልጅ አይደለሽም አባትሽም ሆነ እኔ አሳማኝ ምከንያት ሲኖረን ነው ልትቀበይን የሚገባው የአህሪቱ ግንባር ቀደም ዩኒቨርስቲ በከብር የሚያስቀምጠው ጥናት ነው የምትሰሪው ቆሙ በእቅድ ያልተሰራው የግብር ይውጣ ቁመናቸው ከፍሉን ሞላ «ይሄ የሚያሳየው የጥናቱና ሀሳብ ቀደም ሲል አለመቀበልሽን ነው ሌፅ አስበሽ ነይ ጨርሰናል ዓለማየሁ ገላጋይ ዱሠሙሙ ከከፍሉ አልወጣሁም አንደውም ተቀመጥኩ እውነቱን ለመናገር የጥናቱን ሀሳብ ወድጄዋለሁ የሚያስከፍለው መስዋዕት የአባቴን ልብ ማሻከር ሲሆን ግን የጨረስን መሰለኝ» አሉ ዶክተር በኩርፈያ ትልቅ ሰው ያውም ግዙፍ አካል ያለው ሰው እንደትንሽ ልጅ ማስገደዱ በኩርፊያ ሲሆን ያስቃል ዶከተር ተዉት ብዬ ብወጣ እንኳን እንደማይለቁኝ አውቃለሁ በምን አ አላውቅም ብቻ አውቃለሁ ነገር ግን ከማፈንገጤ በኩርፊያ ልምጭ ሊያግዱ ይሞከራሉ አሰራዋለሁ አልኩ አርግጠኛ አትመስይኝም ለሌሎች ልጆች አሰጠዋለሁ» እሰራዋለሁ ጥሩ ሀሳብ ነወ በጉዳዩ ላይ ከዚህ ቀደም አልተሰራበትም ወደፊትም አሳሳቢ ከመሆኑ አንፃር ብሰራው እወዳለሁ ይኸው የጥናቱ አጭር መግለጫ ብዬ ቱታ ኪሴ ውስጥ አጣጥፌ ያስቀመጥኩትን ሦስት ቅጠል ወረቀት ሰጠኋቸው ሁኔታዬ ልከ አለመሆኑ የተሰማኝ ካደረኩት በኋላ ነበር በኮምፒውተር ሳይፃፍ ረቂቁን ሥኑሥርዓት በጎደለው መልከ መስጠቴ በንቀት ሊተረጎም ይችላል ባ ደነገጥኩ ዶክተር ኩርፊያቸውን ለመገላገል እያማጡ ረቂቁን አነበቡና የት ድንገተኛ ደራሽ ለቀቁ «የሚስተካከለውን ከነገሩኝ በኋላ በአግባቡ አፅፌ አመጣዋለሁ ብ አሉና «ጥሩ ነው ግን ሶሻል እስታተስአይሚን የኑሮ መግለጫ በመቶኛ ቢጨመርበት ጥሩ ነው በተለይ ምግብ መጠጥና አልባስ ከየት እንደሚያገኙ ለምን ያህል ጊዜ። ርዩፍ ሰፈሪዕ ያምሥዕጠፉው ለኛ ኢኅሪዎሥታቻሁ መሆናምን አራት ኪሎዎች ከአቅሙ በላይ በሆነ ምከንያት ሞቱን የተቀበለ ፍርደኛ መስለው ታዩኝ አባቴ በነገሩ ውስጥ ተሳተፈም አልተሳተፈም እነዚህ ሰዎችና መኖሪያቸው ከመፍረስ አይድኑም ስል የመጽናኛ ስሜት አበቀልኩ ግን ይህ የሚያጽናናኝ አልሆነም አባቴ ለመኖር ብቻ የመነኮሱ የሕይወት አመበለቶችን በማንአለብኝነት ለመጨፍጨፍ እጁን አንስቷል እኔም የአርሱ ዘር በመሆኔ እንደ ድርጊቱ ተካፋይ የተቆጠርኩ መሰለኝ ለሦስት ዓመት ልብ ያላልኩት የዩኒቨርስቲ ውስጥ ባይተዋርነቴ ከዚህ ድርጊት ጋር ተያያዘብኝ እዚህ ግቢ ከሸዊት በስተቀር ማንንም ለማነጋገርና ለመቅረብ ጥረት አድርጌ አላውቅም የትኛውም ተማሪ እኔን ለመቅረብ ሞከሮ አያውቅም ከአንድ ተማሪ በስተቀር እሱ ያቀረበልኝ የፍቅር ጥያቄ ከዚህ ታሪከ ጋር ተያያዥነት የሌለው በመሆኑ ባልፈው ይሻላል ነገር ግን ለሦስት ዓመት ያስተናገድኩት ባይተዋርነት ከአሁኑ የአባቴ ድርጊት ጋር ተያይዞ አብከነከነኝ ሸዊትም ትሁን ብቻ አንድ ሰው በመጣ» ስል አሰብኩ ሦስት ነገሮችን ማሳጠር እንዳለብኝ እየተሰማኝ ነው በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ላቅ ያለውን ሥፍራ መያዝ ያለባቸው ማስታወሻዎቹ እንደሆኑ እሙን ነው ግን ን ከማቅረቤ አስቀድሞ ያሱት የእኔ ጉዳዮች መጨበጫ ልጓም ታጥቶላቸው ይንፎለፎሉ ጀመር ቼ ግላቸው ይን ጀመር ያም ሆነ ይህ ያለፈው ትረካዬን ትቼ መጪውን ለአንድ ሳምንት ያህል በአባቴና በዶከተር ማርቆስ መካከል የምመላለስ ባዶ የሸማኔ መቂናጥ ሆፔ ነው ያሳለፍኩት አባቴ የተለመደ ምሳሌያዊ አነጋገሮቹን ያዥጎደጉዳል ከቀን ወደ ቀን ለእኔ ያለው የተመጠነና የተቆጠበ ስሜቱ እየጠፋ በምትኩ እንደ አቋም ተቀናቃኙ ጠንከር ያሉ ቃላቶቹን ይወረውርብኝ ይጸዚል እንደውም አንዳንዴ የያዝኩትን ጥናት ካልተውኩ መአት እንደሚወርድ በነብዩ ኤርምያስ ልሳን ያስፈራራኛል ይህን የአባቴን ሁኔታና የእኔን አቋም ዶከተር ማርቆስ ሲሰሙ ከመላጣቸው ጀምሮ ያለው ሾጣጣ ፊታቸው ይበራል መሐል አናታቸው ጉብ ያለ ስለሆነ ግንባራቸው ረጅም ይመስላል አባትሽ ወጣት እያለም ደሃ ይጠላ ነበር ሀብትን ለሰው ልጅ እንደ አንድ አስፈላጊ አካሉ ይቆጥረዋልና ድሆችን ብፈቃዳቸው እራሳቸውን የሰለቡ ጃንደረቦች እያለ እስከመሳደብ ይደርሳል ሳር ቅጠሉ ኮሙኒዝምን በሚያንቆለጳጵስበት በዚያ ዘመን እንኳ ብቻውን አንድ ጎራ ይዞ ይከራከር ነበር በቦዙ ዓይኖቻቸው ያለፈ ዘመን ለመጥራት ትንቅንቅ ይገጥማሉ ብዙ የኮሙኒስት አፍቃሪ ወጣቶች አሱን ለመግደል ይፈልጉ ነበር ንግግሩ አበሻቃጭ ስለሆነ የተቀደሰ ሀሳብሸን መጥፎ ሽታ ሰጥቶ ለውሻ የሚጣል ያደርገዋል እኔንማ ማርቆስ ብሎ ጠርቶኝ አያውቅም ማርከስ ነው የሚለኝ ይሄንን ወደፊት በሰፊው አጫውትሻለሁ ያለፈ ትውልድ የርዕዮተ አለም ንትርከ ውስጥ የገባሁ መሰለኝ ያም ሆነ ይህ ይሄን ትተን ወደ ዋናው ጉዳይ አገግባ አዲስዘመን ጋዜጣ ላይ ስለአራት ኪሎ የጻፈውን ሰው ለማግኘት እጅግ ጣርኩ የአምዱ አዘጋጅ ረድታኝ በመጨረሻ ስልኬን ሰጠችው ደወሰልኝ ድምጹ ጎርነን ያለ ነበር ን ዓለማየሁ ገላጋይ ባለጉዳይ ነበር መደወል ያለበት» አለኝ ስልኩን እንዳላገኘሁና እሱን ፍለጋ አራት ኪሎ ሁለት ጊዜ መሄዴን ነገርኩት ፐሩ ከእንግዲህ ይደውላል ብለሽ እንዳትጠብቂ አለኝ የማያውቃትን ሴት የሚያናግር አይነት ድምጸት የለውም ግዴለም እኔ አደውልሎታለሁ አልኩት ተቀጣጠርን ምልከቱ አስገርሞኝ ነበር የነተበ ሱፍ ኮት አለብሳለሁ ኮሌታውን አቆማለሁ» አለኝ ከኑሮ ጉብታ ወደ ኑሮ አዘቅት ወርጄ ጥቂት ፍተሻዎችን ላደርግ እንደሆነ ስረዳ ልቤ አንደመደንገጥ አለ ሰው ኑሮውን ይመስላል በሚለው ብሂል አምናለሁ ባላምንም የሚታየው ይሄው ነው በየመንገዱ ለከብራቸው ደንታ ሳይኖራቸው ካገኙት ጋር አየተናቸፉ የሚጓዙት ብዙውን ጊዜ ዝቅተኛ አኗኗር ውስጥ ያሉ ሰዎች ናቸው ካካባቢው የተነጠለ ቁመት ባለው ቀውላላ የኑሮ ማማ ላይ ተንጠልጥዬ መቅረት እንደሌለበኝ ግን አምናለሁ እድሉ ደግሞ ይሄ ጥናት ነው ዶከተር ማርቆስ አንዳቀዱልኝ ቤት ተከራይቼ መካከላቸው መኖር ግን የማይታሰብ ነው ምናልባት እጅግ መቅረብ ሳይኖርብኝ አይቀርም ይሄም ቢሆን ያስፈራል አራት ኪሎን ካንዴም ሁለት ጊዜ ሰልዬዋለሁ ያየኋቸው ሰዎች ሁሉ የሚያስቀርብ ፊት የላቸውም የኑሮ ጣጣቸው የሥጋ ምርጊታቸውን ቦዳድሶት በተመልካቹ ላይ ስጋት ። ርዕሱና ጭብጡ አይሄድም ድሆቹ የሚኖሩበትን የመከራ መንደር የፈንጠዝያ ከተማ ብለው ነው ስም ያወጡለት ያንን ይዞ ነው ፀሐፊው ዘ ሲቲ ኦፍ ጆይ ያለው እሺነ አለኝ ለመስማት ሁለመናውን ጆሮ አእድርጎ ይሄን መጽሐፍ አለማንበቡ ደስ አለኝ መልሼ በደስታዬ አፈርኩ ምቀኝነት እንዲህ ነው የሚበቅለው ስል አሰብኩ «በጣም የወደድኩት መጽሐፍ ነው ያስጨንቃል አንድ ሰሞን ተበጥብጩ ነበር ሰው ጋማከብት ተከቶ ጋሪ ሲጎትት የሚውልበትን ጨካኝ ዓለም ያሳይሃል በዚህ ላይ ሥጋ ደዌ የሱን ያህል የራስ በራስ ተመስጥአ አላሳየሁም ነበርና ንግግሬ የጣፈጠልኝም አልመሰለኝ ሙሉጌታ ግን በኔ ትረካ ይሁን በሌላ ሳይገባኝ በሐዘን ትከዝ እንዳለ ነበር «ሰው በሰው ላይ የሚጨከነውን ያህል በአንስሳትና በአራዊት ላይ አይጨከንም» አለኝ ቀዘዝታው እንደተጫጫነው አንዲት ባለምግብ ቤት አውቃለሁ ልጅ ያዘሉ ነዳያን በራቸው ላይ ተኮልኩለው ሲጠባበቁ እሳቸው ግን የምግብ ቤታቸውን ትርፍራፊ ለሰፈር ሁሉ ውሾች ይዘው ይመጡ ነበር አንድ ሰሞን የውሾች ቁጥር ከነዋሪው ሰላይ ሆኖ እንደነበር አስታውሳለሁ» እኔ ከነገርኩት ጋር ምን አንደሚያያይዘው አልገባኝምና ቀልቡን ያልሳብኩት ሟሚሰለኝ ዓለማየሁ ገላጋይ ሰው የጋማ ከብት ተክቶ አሪፍ አገላለጽ ነው የጋማ ከብትኮ አልጠፋም ህንድ ወውስጥ አለ ግን ሰው በሰው ላይ የሚጨከነውን ያህል በእንስሳት ላይ አይጨከንምና ሰውን በጋማ ከብት ተካው ግሩም ግንዛቤውና ትንታኔው አስደነቀኝ መምህሬ ቢሆን ስል አሰብኩ ተማሪውን የሚያዳምጥና ያዳመጠውን የሚተነትን መምህር ስለመመረቂያ ጽሁፌ ድንገት ጠየቀኝ ለማስረከብ አምስት ወር ያህል እንደቀረኝ ስነግረው መጣደፍ እንደማያስፈልግ መከሮኝ በአንክሮ መመልከት ያለብኝን ነገሮች ጠቆመኝ የአራት ኪሎን አመሻሽ ላይ መሟሟቅ የህፃናቶቹን ለሸቀጥ ሽያጭ መራኮት የመጠጥ ፍጆታ የሥጋ ፍጆታ የሸርሙጥናው ገበያ መድራት ይሄን በተመስጦ ከጠቋቆመኝ በኋላ አንድ የሚያስገርም ታሪክ አከለልኝ አያቱ እንደነገሩት አልደበቀኝም በአፄ ኃይለሥላሴ ዘመን ነው አለና ብናኝ ጢሙን ከድራፍት አመዳይ በቀይ አውራ ጣቱ አጽድቶ አዚህ ከፓርላማ ጀርባ ያለውን የባለወልድ ደብር ያስተዳድሩ የነበሩት አለቃ ቤተመንግሥት ተጠሩ ፓትርያርኩ ከጃንሆይ ጋር በመመካከር ነበር ያስጠሩዋቸው እንዲህ አሏቸው የባለወልድን ደብር ገዳምልናደርገው አስበናል ለአርስዎ የኡራኤልን ደብር አንድታስተዳድሩ ልንሰጥዎ ነው አርስዎን ማማከሩ ተገቢነት ስላለው ነው የጠራንዎዖ እና ምን ይላሉ። የሚል የሚያስተጋባ መልዕከት ውስጤ ገብቶ ስሜቴን አጣበበው የሙሉጌታ ሁኔታ ከጥናቴ ጋ የተያያዙ ጥያቄዎችን እንዳቀርብለት የሚጋብዝ አልነበረም እጅግ ተጨንቋል እሁንም አውራጣቱ አላረፈችም ሲያስብና ዓለማየሁ ገላጋይ ዓመ መ» ሲጨነቅ አውራ ጣቱ መፍጠን ትጀምራሰች ማለት ነው ስል አሰብኩ እንደ መጀመሪያው ቀን ሆዱን ከፍቶ መጠጣት አልቻለም ሦስት ድራፍት እንደመጣለት የእኔን ለስላሳ ጨምሮ ከፈለና ይዞኝ ወጣ ከቀበሌው መዝናኛ ብዙም ሳንርቅ አቁሞኝ ወደ ማዶ እያመለከተ ባለፈው የገባበትን የመንደር ሸንቁር ጠቆመኝ ነጭ የተቀባ ቋጥኝ የመሰለች ሴት ተኮፍሳ መግቢያው ላይ ቁጭ ብላለቾ ያመግቢያ መቆሚያጣቢያ ይባላል መንደራችን ውስጥ ያሉት ሴተኛ አዳሪዎች ስለሚቆሙበት ነው የሸሙጥ ስሙ የወጣለት ከዚያ አንስቶ እስከ አራት ኪሎ ሆቴል ግርጌ ድረስ ፈራሹ መንደር ይመለከተዋል» አለኝና «ከዚህ ጀርባ ያለው ኩታንኩት መንደር ውስጥ ለውስጥ ከመቶ በላይ ቤተሰቦች ይኖሩበታል ጦር ሜዳ የተፋጠጠ ጠላት እንኳ ይቺን ያህል ኩርማን መሬት ለማስለቀቅ የዚህን ያህል ሰው አይፈጅም ቤተሰቡን ቢያንስ በአምስት አባዥው አለኝ ሙሱጌታ የተቅበጠበጠ መሰለኝ እጅግ ተረብሺ እኔን በማሰብ እንጂ ከዚህ በላይ የሚረበሽ ይመስላል የሚያደርገው በማጣት አትኩሮ ተመለከተኝ ፊቴ ላይ ምን እንዳነበበ እንጃ ያዘነልኝ መሰለኝ የሚያደርገው ሲያጣ ኮምሬድኔ የሚል ጥሪ ሰማን ሙሉጌታ ጎሸ ናኔ አለው ኮምሬድ ቆሎ በጥብቆው እንዳሳቀፉት ልጅ ሱሪውን ጨምድዶ እንድ እግሩን እየጎተተ መጣ የግራ እጁ ትንቧና ተከታይ ጣቶቹ ታጥፈው ሳንቲም ይዘዋል በሦስቱ ጣቶቹ ጨበጠን ዕውቀቴን ወደ ገንዘብ ለመለወጥ ነው የመጣሁት «ጥሩ ምን አዲስ ዕውቀት አለህ አያለ ወደ መንገድ ዳር ይዞት ወጣ ከስሜቱ መገላገያ ሰበብ አድርጎ ተቀብሎታል ስል አሰብኩ ሰለ ሰው» አለ ኮምሬድ ጥሩ ሰው ምንድነው። አሰብኩት ቆሌ ምናምን ተአምራቸው እኔ ላይ ሰርቶ አይደለም ግን ኮምሬድ እኛ መንደር ያደጉ ልጆች ፅጣፈንታ ላይ ስለሚገኝ ከእነሱ ጋ ተደበላልቆብኝ ነው አንድ የኛ አብሮ አደግ የጀመረውን ህይወት እየጨረሰ እያጠናቀቀ ይመስሰኛል ከኮምሬድ ሕይወት ጋር የተቀላቀለብኝን የአንድ ጓደኛዬን ታሪከ ልንገርሽ እንደመባነን ብሎ መፈለግና አለመፈለጌን በሚፈትሽ አኳኋን አየኝ እሺ» አልኩት ንገረኝ እፈልጋለሁ አሰብ አድርጎ በምሰጣ መናገር ጀመረ በአጠቃላይ ስለኛ መንደር ልጆች ሳስብ አንድ ጥቅስ ይመጣብኛል ጥቅሱ የቻይናዊው የላኦዙ ነው ሂከፎ ፐኮፍየ ሂከፎ ሃህ ህክበፎየክባ ጸርቪክ ርቪክ ሳኦ ዙ አለመመልከቱ ነውጂ እንቅስቃሴ አልባ እንቅስቃሴ ፍንተው ብሎ የሚታየው የእኛ መንደር ልጆችጋ ነው ትካዜው የሚጫጫን ሆነብኝ ቀጠለ ፌየኛ ሰፈር ልጆች እንደ ዛፍ ዕድገት ወይም እንደ ንጋትና ውድቅት ድንበራቸውን ሳትለይላቸው አድገው ጎርምሰውና በስተመጨረሻ ወድቀው ታያቸዋለሽ ለጥቂት ጊዜ ካልተለዩዋቸው ለውጣቸው ልብ ሳይባል ነው የሚከናወነው አንድ ቀን ተወልዷል አንድ ቀን አድጓል አንድ ቀን አስፋልት ወጥቷል አንድ ቀን ሰከሮ ታይቷል አንድ ቀን ትምባሆ ጨብጦ ታይቷል አንድ ቀን ጫት ቅሞ ተስተውሷል አንድ ቀን ታስሯል አንድ ቀን ችግር ጠንቶበት ታይቷል አንድ ቀን ታሞ ተጠይቋል አንድ ቀን ሞቷል ይሄ የአብዛኛው የሰፈራችን ልጆች አጭር የሕይወት ታሪከ ነው ድራፍቱን ለኮፍ አድርጎ ተወው ልጆች እያለን በዕድሜ የሚበልጠኝ ደመኛዬ ነበር መሳፍንት ይባላል በቅጥል ስም ከንቱ ይባላል ደመኛዬ የሆነው በድሎኝ አልነበረም እንዲሁ ሳየው የምወግረው ይመስለኛል ሆዱ ወደ ውስጥ የሰመጠና ሲራመድ ልምጥ ልምጥ የሚል ነበር እና ሳየው ልቤ ይንቀዋል ነገር ፈልጌ ስያያዘው አልቸለውም እማማነ ብዬ አጮሃለሁ አያቴ ይወጡና ይጣሉታል ከኑሯቸው መከፋት የተነሳ እናቱ እሱኑ ተቆጥታ ነገር ማብረድ ትመርጣለች በዚህ መሳፍንት ጥቃት ይሰማውና ጭንቅላቱን ግራ ቀኝ እያማታ የቴኒስ ኳስ የሚያካከል እንባ ያዘንባልደስ ይለኛል» ይሄ ሰው ስለከፋቱ እያወራ ነው ግን አይመስልም ሐዘን የተጫጫነው ግንባሩ ላይ እንደደመና ፀሐይ ብልጭ ያለች ፈገግታ ታይታ አፍታም ሳትቆይ ጠፋች እሱ ያኔ ጎረምሳ ነው እኔ ገና ከመንደር አልወጣም ነበር አባቱ በሥራ ጅማ ነው የኖረው አናቱ ከመሳፍንት በታች አምስት ሴቶች ከሌላ ወልዳ ነው አባቱን የጠበቀቸው ቤታቸው ሁልጊዜም በሊጥ የተቀባባ ነበር አናቱ ኖራ የመሰለ ጤፍ እያቦካች ትጋግራለች ጫማው ልብሱ መጋረጃው ድስቱ ሁሉ በሊጥ የተነካካ ነበር እናትየው ጥንቃቄ አልባነቷ አከሰራት ጠብጠቦ የሚል ቅጽል ስም ወጣላት ወሬ ከጀመረች ማባሪያ አልነበራትም ዘወትር እየተንጠለጠለ የሚያስቸግራትን ለሃጧን ለመሳብ ስትል ብቻ ነበር ወሬዋን ገታ የምታደርገው በዚህ ጠብጠቤ የሚል ቅጽል ስም በስተርጅና ወጣላት ማን እንጀራ ይግዛ። ሸዊትን ጠየኳት «እ ዌል ምን መሰለሺ እያለች ነገሩን ጎለጎለቸው ግንባሯ ላይ እንዳለው ሰማያዊ ደም ስር የምትናገረው ነገር ሁሉ ይወሳሰብባታል ጉልህ ሆኖ የሟታየው ደማቁ አለባበሷ ብቻ ነው ሸዊት ብዙ ጊዜ አፍቅራለች ጊቢ ውስጥ እንኳን ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ፍቅር መስርታ እንዳፈረሰች አውቃለሁ እኔ ስሸሽ ምንም አያስፈራም ትለኝ ነበር ኬር ትሰጪዋለሽ ምቾት አንዲሰማው ይከፋሸና እናቱ ሲቆጡት ታለቅሻለሽ እኔን ምቱኝ ትያለሽ ቢመቱት ይቅርብኝ እኔ ብላ አንተ ትይዋለሺ አንደነገሩ ሊፒስቲከሽን ትቀቢያለሽ ማች አልሆን ይልሻል ልብስሽ ሲያጠና እሱ አንቺ እቅፍ አርገሸው ትከሻውን ከጥቢያ ምንም የያዝኩት የለም በደፈናው እንደስካር እንደ እብደት እንደ መሞላቀቅ እንደ ረሃብ ነው ብትለኝ ይሻል ነበር ሁሱንም ባላውቃቸውም ለመገመት ግን ቅርቦቼ ናቸው ስለሙሉጌታ ጠየኳት «ብሎሽ እንዳይሆን አጣብሺኝኦ አለችኝ እሱን በኋላ እነግርሻለሁ አልኳት እንዳትነግሪኝ በኋላ ያስፈራል ይቀፋል ምቾት አይሰማሸማ አይጠብቅማ አራሱን ኢቭን ኢፍ አያበጥረውም ፀጉሩን ከብር እንዲሰማው እራስሸን የምታደርጊው ባለማነጋገር ነው ከደረጃሽ ዝቅ ያሉትን ኢቭን ኢፍ አልፎተርፎ ላፍቅርሽ ቢል ደርሶ ደፍሮሻል ንቆሻል ሰድቦሻል ማለት ነው ከንግግሯ ጋ ሀሳቧን በአቀማመጥ ታፋልሰው እንጂ አንዳንድ ጊዜ ትከከል ነች በተለይ አንድ ነገር ላይ ጓጉቼ ከጠየኳት አማርኛዋን የሚያስተዳድረው የእንግሊዘኛ ሰዋሰው ይከፋል የእሷን ቋንቋ እያረሙ ማሰብ እንዴት የሚሰለቸ ነው ብዬ አሰብኩ ቢሆንም አቋሟ የሚናቅ አልነበረም የከብር ጉዳይ ማንኛውም ሰው መስፈርት ውስጥ መካተት ይኖርበታል ምን ሳስብ እንደቆየሁ ካሰብኩት ምን እንዳገኘሁና ምን አቋም ላይ እንደደረስኩ መመዘን አቃተኝ ዓለማየሁ ገላጋይ አምስት ለሦስት ቀን ሙሉጌታን አላገኘሁትም መንደሯ ከቀራት አጭር ዕድሜ አንፃር ከታየ ትልቅ የጊዜ ኪሳራ ነው ግን ደግሞ ጥናቴ ላይ ከማተኮር ይልቅ በተናጠል ለሙሉጌታ ዕጣፈንታ መበከንከኔ አቁስሎኛል ተልዕኮዬ መመረቂያ መስራት መሆኑን ዘንግቼ የእነሙሉጌታን አኗኗር ለመታደግ ከአባቴ ጋር ተነታረኩ አባቴ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ረጋ ብሎ የነብይ ምሳሌውን ሳያዥጎደጉድ የፍላጎቱን ቸረኝ እየሽ ይቺ አገር በግለሰብ እጅ የነበረ ጥሪቷን ለደሃ ደግሳ በማብላት አባከናለች ለብዙ ሺህ አመታት በቅዱሳንና በፖለቲካ ሥም ሀብታም የተባለው ለደሃው ግብር ሲያበላ ነው የኖረው ይሄ ባህል ድሆችን ከማጥፋት ይልቅ እያንሰራፋ መጣ ግዛቶች ሁሉ በድሆች ተወረሩ ያለፈው መንግሥት ደግሞ ጭራሽ ድሆችን ባለእርስት የሚያደርግ ፖሊሲ ይዞ መጣ ድሆች ብቻ አይደሉም እነዚህ ሰዎች ሰነፎችም ናቸው ርስታቸው ላይ ተኙበት በስንት ድካም የለማ እርሻ በመንግሥት ከለላ የነጠቁትም የገጠር ሰነፎች እንደከብት ያለሀሳብ በመራባት ለመጋጥ ተሰማሩ ይሄ አንድ ቦታ ላይ መቆም አለበት ያ ቦታ ደግሞ ይሄንን ቤት ያጠቃልላል እኔንም ያካትታል አንድ ባለሀብት ሺህ ሰነፎችን አዝሎ መጓዝ የለበትም የአኔ አቋም የዚህችን አገር ዕጣፈንታ ይወስናል «የዚች አገር ዕጣፈንታ የሚወሰነው በመጨካከን ነው። ስል አሰብኩ። ስል አሰብኩ «እናቴ ለሁሉም ነገር መልሷ እንቢ ነበር አያቴ ደግሞ እሺ እንደ እናቴ ቢሆን ኖሮ እኔ ሰው አልሆንም ነበር ብዬ አስባለሁ አያቴ ግን ሁሉንም በእሽታ እየተቀበሱ አነጹኝ ንግግሩን እያብሰለሰልኩ ዝም አልኩ ጭንቅላቴ አንደወትሮው አልፈጥንልሽ አለኝ ስካር ይሄ ይሆን። ዓለማየሁ ገላጋይ ። ዱ አሠፋ ይርጉ አዋጅ የሚያነበው ጋዜጠኛ ከማርሽ ሙዚቃ በኋላ «ከጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ ሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ በአምባገነንነትና በማን አለብኝነት የአገርህን ዳር ድንበር በመድፈር ተጠብቆ የቆየውን የነፃነት ታሪኪ «ሁሉም ወገን እራሱን ቤተሰቡንና አገሩን ለመከላከል ዝግጅቱን ማጠናቀቅ አለበት መቼም የዚህን ጋዜጠኛ ድምጽ ሲሰማ የማይርድ የለም ሱማሌ የኢትዮጵያ ምሥራቃዊ ከፍል በመውረርና በወቅቱ የነበራት ኃይል አዲስ አበባ ሊያስገባት ይችላል ተብሎ ስለተፈራ በጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት በኩል ይሄ መግለጫ ተሰጥቶ ነበር በዚህ ሠዓት ላይ እኛ ቤት አያቴ አልጋው ላይ ቁጭ ብሷል እኔ ሁልጊዜም የምቀመጥበት እግሩ ስር ካለች በርጩማ ላይ ተቀምጫለሁ አያቴ በንዴት የያዘውን በአረቄ የፈላ ሻይ ለኔ ሰጥቶ ጊዜውን ይረጋግም ጀመር ሴት አያቴም እየተርበተበቱ መላመላ ያሉትን ሁሉ ለወንድ አያቴ ያማከራሉ ወንድ አያቴም አልፎ አልፎ «ፍሬፈርስኪሽን ተይውኔ እያለ ይቆጣቸዋል ትዝ ይለኛል ከሴት አያቴ መላ አንዱ በረብሻ ምከንያት ከቤት መውጣት ባይቻል የመንደራችንን ቤቶች ግድግዳ እየቀደዱ ተያያዥ ነውና አንዱን ቤተሰብ ከሌላኛው ቤተሰብ ጋ ውስጥ ውስጡን ማገናኘት ነበር በእርግጥም መንደራችን ካቀፈቻቸው ከሰባ በላይ ቤቶች ግድግዳዎቻቸው ቢነደሉ አንድ ጥሩ ዋሻ ይወጣቸዋል ያለማጋነን አንድ ሰው ከጣሪያ ላይ ሳይወርድ መንደራችንን ሊያካልላት ይቸላል የአንድ እርምጃ ያሀልኳን መራራቅ በየቤቶቹ መሀል አይገኝም እንደቤቶቹ አሰራር ሁሉ የመንደሩ ነዋሪዎች ገመናቸውን ሳይቀር ደበላልቀው ነው የሚኖሩት ጎረቤት አያውቀው ምስጢር ወንፊት አያጠራው እፈር የለም» ይሉሻል እኛ መንደር ነው እያንዳንዱ የመንደሯ አባል ማንምን እንደበላ እና ማን ጾሙን እንዳደረ በየጎረቤቶች መዝገብ ላይ ሰፍሮ ይገኛል ከዚህ ድብልቅልቅ ማህበራዊ አኗኗር ውስጥ ማፈንገጥ አይቻልም መንደርተኞቹ ሲያድሙ እና ሲተባበሩ እንደ አንድ ሰው ሆነው ነው የመንደራችን ነዋሪዎች ኑሮ እየሸነቆጠች የምታሯሩጣቸው በመሆኑ እንደ ግራዋ አበባ በየአቅጣጫው ይረጫሉ በዚህም ምንም ተደብቃ የምትደረግ ነገር የለችም ከተበተኑበት ሲሰበሰቡ አፋቸውን ገጥመው ስላጋጠማቸው መረጃ መለዋወጥ ነው ዛሬ እገሌ ከእገሌ ሚስት ጋር እዚህ ቦታ ታይተዋል የእገሌን ልጅ ፎሊስ እያዳፋ ወስዶታል ትዬ እከሊት ውቃቢ ቤት አድረው ሲወጡ ታይተዋል ትዝ ይለኛል ልጅ ሆፔ ከትቤት ከፎረፍኩ አንዷም ሳትቀር የነበርኩበትና ያደረኩት ለሴት አያቴ ጆሮ ይደርሳል እኔ አገር ሰላም ብዬ ስመለስ ዛሬ ቢያሳ ምን ታደርግ ነበር። ሴት አያቴ እናቴን ወለዱ እናቴም እኔን ወለደች በቃ ይቺው ናት የዝምድና ሐረጋችን ርዝመቱ እኔም እንደ እናቴ ያለ ወንድምና እህት አያቴ ቤት አደኩ እናቴ አያቷ ቤት በማደጓ ለእናቷ ያላት ስሜት እኔ ለሷ ካለኝ ስሜት የተለየ አይመስለኝም እትዬ ብላ ነው የምትጠራቸው እኔ እሷን በስሟ ስጠራት አያቴን ደግሞ አንቱ እማማ በልጅነቴ ሲበዛ ታማሚ ነበርኩ አያቴ ሲያወሩ አንድ ጊዜ ሳንባ ነቀርሳ ሐኪም ቤት ይዘውኝ ሄደው ሲመለሱ የጆሮና የአንገት ወርቃቸውን በተስፋ መቁረጥ አውልቀው ለሐዘን በመዘጋጀት ነበር ሴት አያቴ ለኔ ዝምድና ማሳየት የጀመሩት አየበረታሁ መታየት ከጀመርኩ ወዲህ ነው እናቴ እኔን ለመውለድ ከአምስት ቀን በላይ አምጣለች በመጨረሻ ስትገላገል አያቴ ከኔ ይልቅ ለልጃቸው ነበር ትኩረት የሰጡት እኔ በከርታስ እንደተወለድኩ ወዲያ ብለውኝ ልጃቸውን በስስት መመልከት ጀመሩ አሁን ድረስ አከስቴ እያልኩ የምጠራት የከርስትና አባቴ ሚስት ውይ ነፍስ አለውነ ትላለች ማንም ስለኔ የተጨነቀ አልነበረም አያቴ እንኳን ልጄን የለቀቃት ጂ የራሱ ጉዳይኔ ይላሉ «እከስቴ ናት አንስታ ያጣጠበቸኝ እንግዲህ ዛሬ ለአያቴ ከልጃቸውም በላይ ዓለም ላይ ያለሁት አንድ ብቸኛ ዘመዳቸው እኔ ብቻ ሆኛለሁ በአፋቸው ባይናገሩትም እኔ አንድ መሆኔ በውስጣቸው ያብሰለስሉታል ካወጡትም የቆጫቸው ላለመምሰል እየተጠነቀቁ ነው «የልጄን ሆድ ረግጦ ወጥቶ ይላሉ አንድ ልጅነቴ ሕይወታቸውን እንስፍስፍ አድርጎታል ትዝ ይለኛል አድጌ የትም በምዞርበትና አንደውም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በገባሁበት ዕድሜዬ አያቴ እኔን አቅፈው እንጀራ ይጋግሩ ነበር ጎረቤቶች ሲያዩ ይስቃሉ እኔን ካልከበደኝ ነው የመልሳቸው መከፈቻ አንዳንዴ መቼ ይሆን የምከብዳቸወ። ብዙ ጊዜ በካልቾ ብሎ ወጡን ለግድግዳ ዳርጎታል በዚህም አያበቃም ዱላ ያስከትላል አማማ ከሱ ጋር ከተጣሉ ለመሸምገል የሚሞከር መንደርተኛ የለም እማማ ሲያወሩ ሴላው ቀርቶ እቤቱ እንድገባበት የሚፈልግ የለም ይላሉ ይሄንን አንስተው እሁን ሲጫወቱ እየሳቁ «ምናምን እንደቀመሰ ውሻ እኔ ስሄድበት ሁሉም ደጃፉን ይዘጋል ይሉና ሳቃቸው ጠየም ብሎ አንድ ቀን መሐል አናቴን ተርከከውኝ ብቻዬን ፎሊስ ጣቢያ ስሄድ በኋላ አማረች ቢገድሉኝም ይግደሉኝ ብላ ቲከተለችኝ ይላሉ ወንድ አያቴ ፀብ ያለሽ በዳቦ ስለሆነ ሰው ሁሉ ይከነቀቃል ዓለማየሁ ገላ ተ የአያቴ አንድ ግርም የሚለኝ ባህርይ ነበረው ከቤቱ አልፎ ተርፎ የሰው ልጆች ይቀጣል ይሁን ልጆች ናቸው የሰው ሚስትም የሚደበድብበት ጊዜም አለ ምናባቷ ሆና ነው ወንዱን ልጅ እንዲህ አድርጋ የምታዋርድ ይቺ ውሻ ሻጭነ ይላል በዝ ባሏ ወንድ እያቴን በቅጡ የማስታውሰው በጡረታ ተገልሎ ቤት ውስጥ መዋል ከጀመረ ወዲህ ነው ከዚያ በፊት «ሊጋባ ቢሮ ከሚባለው መሥሪያ ቤቱ ወስዶ ሜዳው ላይ ሲለቀኝ ይዞኝ ጠጅ ቤት ይገባና ለኔም አንድ ብርሌ የሚያስቀዳልኝ ነበር «ልጅ አይደለምዴነ ሲሉ አያቴ ያፈጥና «ምናገባህየ ወደሥራህኔ ሲላቸው ያቺን አንዷን ብርሌ ገንጨዬ ስመጣ አማማ ሲያዩኝ እንደሰከረ የምሆነው እማማም ልቡን አፈንድተው ይግደሉት እያሉ አያቴ ሳይሰማ የሚያልጎመጉሙትና በጠዋት ተነስተው እርጎ የሚያዘጋጁት ከዚህ ሁሉ በምሬት የማስታውሰው የቤተከርስቲያኑን ነው በቅዳሴ ሰዓት ሲነሱ ቆሜ ሲያጎነብሱ አቀርቅሬ ሲንበረከኩ ተንበርከኬ ከዚህ ዝንፍ ካልኩ ዳ ኩርኩም ወንድ አያቴ ሲበዛ ጥንቁቅና ጠርጣሪ ነበር በሱ አስተያየት የወንድ ልጅ መስፈርቱ ብዙ ነው «ወንድ ልጅ አንዴት ደጃፍ ሳያዘጋ ሱሪውን ያወልቃል። እንዳይደነግጡ እንዳይናደዱ እሳቸውም «ዋፓያወቁብህ ጊዜ ነፍስህን ነው የሚያወጡት ይሉኛል ዓለማየሁ ገላጋይ መ ልጅ ሆና ሰው ቤት ትገባና «ውጨ ሲሏት ድርቅ ብላ «አልወጣም» የምትል ትንሸ ልጅ ነበረች እናቷ ለልጆቻቸው ግድ የሌላቸው አዝማሪ ነበሩ ከግዴለሽነታቸው የተነሳ ማታ ለማዘመር ሲሄዱ የት ወደቅሸ ምን ትበያለሽ» ሳይሏት ነው ለባብሰው እብስ ታዲያ እኛ ቤት አምሽታ አራቷን በልታና አባዬ አግሯን አሳጥቧት ከፍት የተተወ ቤቷ ወስደን እናስተኛታለን እናቷ በጠዋት ተነስተው መንደርተኛውን መሳደብ ይጀምራሉ እዚህ ጠቅጥቀው ጠቅጥቀው ቅዘኗ መከራነ ይጠቅጥቅሽሸ አባሽነ ይላል አያቴ ግልፍ አያለው ሸንጋራዋ እናት ፀጥ ይላሉ አፈር ብይና ልጅ ማሳደግ አንዲህ ነውን ቆይ ብሎ ይዝታል እንደማይለቃቸው ስለሚያውቁ ለተወሰነ ጊዜ በሸንጋራ ዓይናቸው ይጠነቀቃሉ ሴይጣን ከበረደ በኋላ ግን ሳያስበው አግሩ ላይ ይወድቃሉ ወይንም አማላጅ ይልካሉ አሱም ሲያንገራግር ጠቅጥቀህ ጠቅጥቀህ ትበለኝ» ይላል ወንድ አያቴ ሊያሰርጽብኝ ከሚጥረው ባህርይ ውስጥ አንዱን ብቻ እስከ ዛሬ ድረስ አደግፈዋለሁ ከኛ ከልጆቹ ውስጥ ሲያልፍና ሲያገድም የሰው ቤት መለስ ብሎ የተመለከተ ልጅ አሳር ፍዳውን ያያል አእንተ ውሻ የሰው ቤት ምን ያሳይሃል ውሻ ነው የሰው ቤት የሚመለከት ይላል ተቆጥቶ የሚገርመው ግን ከመንደሩ ልጆች ውስጥ እኛ ቤት ውለው የማያመሹት በጣም ጥቂቶቹ ናቸው አያቴ ከኛ ከልጆቹ ይልቅ ለተጎሳቆሉት የመንደር ልጆች ከፍተኛ ፍቅር ነበረው በዚህም የሚቀርቡት ሁሉ አሱን አባዬ እማማን ደግሞ እማዬ» ብለው ነው ያደጉት በዚያ ለምደው አሁን ድረስ አንድ አምስት የሚሆኑ የወለዱና ትልቅ የሆኑ ልጆች እማማን አማዬ» እያሉ ይጠሩዋቸዋል እያቴ ልዩ የሆነ ባህሪው ይበዛ ነበር ማለት ይቻላል እድሜ ልኩን ውኃ ጠጥቶ አያውቅም ውኃ ወደአፉ የሚገባው ሊጉመጠመጥ ሲል ብቻ ነው የውኃ ጥሙን የሚያረካው ጠጅ በመጠጣት ነው ከዚህ ሌላ አያቴ ከሰሩት ምግብ ውጪ ቤት ውስጥ ሲበላ ታይቶ አይታወቅም ጎረቤቶቻችን ደግሰውኳ በሰሀን ይዘውለት ሲመጡ ለኛ እሰተላልፎ ይሰጣልጂ ሰዎቹን ለማስደሰትኳ አይቀምሰውም እኛም ብንሆን እትበሉም። አንዳንዴ አያቴ እያየ ሳንቲሟን ለለማኝ የምሰጥበት ጊዜ ነበር ታዲያ በዚህ ድርጊቴ የሁለት ወር ደሞዜን አቆነደዳለሁ አያቴ አገሩ ጎጃም ዳሞት ነው ከአገሩ የወጣው ገና የአሥራ አራት ዓመት ልጅ ሳለ አንድ ቄስ ደብድቦ ቄሱ ከነፍስ በሚጠበቅበት ጊዜ ነው ጨካኝ ነበር ጨካኝነቱን የምትገነዘቢው ስለ ሀገሩ በሚያወራበት ጊዜ የመጨረሻ ልጅ መሆኑንና ከሰባት ወንድሞቹ ውስጥ በመጨረሻ አገሩን የለቀቀው እሱ መሆኑን አውርቶ የወላጅ መካን የሆኑትን ወላጆቹን ሲያነሳ ምንም የሐዘን ስሜት አይሰማውም ይሙቱ ይኑሩ አላወቅም አስካሁን ይኖሩ ብላቸሁሶ ይላል ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር እስከ መቃብርን ሳነብ የበዛብህን ወላጆች የሱ እንደሆኑ ሆኖ ስለተሰማኝ አይ ጎጃም» አላለሁ ሌላው የአያቴ ጨካኝነት የሚታየኝ ብዙ ጊዜ ከቤታችን በግ አይጠፋም ግልገል ገዝቶ ያሳድጋል በጎቹ አሱን ከመልመዳቸው የተነሳ ምሳ እስኪበላ ጠብቀው እጁን የጠራረገበትን አንጀራ ይጎርሳሉ አያቴ በጎቹም ቢሆኑ ሥርዓት እንዲኖራቸው ይፈልጋል የሚታሰሩበትን ገመድ አንገታቸው ላይ ይጠመጥምና ወደመናፈሻ አስከትሏቸው ይሄዳል አንዳንድ ሰዎች በጎቹን ከኋላ ያዝ ሲያደርጓቸው ይጮኃሉ አያቄ ዞር ይልና እባከህ ልቀቀው ይላል አያቴ በዚህ አይነት ለብዙ አመታት በጎችን እንደ ልጅ አድርጎ ቢያሳድግም ጊዜያቸው ሲደርስ ለማረድም ወደኋላ አይልም እማማ ቀድሞ አለማቅረብ ካቀረቡ በላይ ማረድ ደግ ነውኦ ይሉታል «ዝም በይነ ይላል አያቴ «ከብት ነው ሌላ ምን መሰለሽ። የአፍ እሩምታ ተሰማኝ ብዙ ሰዎች ነበሩ ሙሉጌታ ድብዳብ የተነጠፈ ሳጥን ላይ ተቀምጧል ሲያዩት ግማሽ ፍልሚያ ላይ በተሰጠው ጥቂት ጊዜ ለማረፍ የሚሞከር ቦከሰኛ እንጂ የተረታ ሰለባ አይመስልም ግራ አይኑ ዙሪያ ዘጉኖ ከስሩ የተጎለጎለ የሥጋ እንቡጥ ይታያል ለምን በቁስል ፕላስተር እንዳልሸፈኑት አልገባኝም አፍንጫው ተደልድሎ ከጉንጮቹ ጋር ተቀላቅሷል ለመተንፈስ አንደሱረት ሱሰኛ የጠበበው የአፍንጫው ቀዳዳ ይተናነቃል ፈገግ ለማለት ሲሞከር የፊቱ ንቅናቄ ቁስሉን ስለቆሰቆሰበት ስቃይ ተነበበት «ነይ እዚህ ነይ እዚህነይ እዚህ» የሚል ሩምታ ተተኮሰብኝ አሱውጋ ትሁን አሉ አንድ ጠና ያሉ ሰው አስተያየታቸው ሴትነትን ያስታውሳል ሁለት ሴቶች መካከል ተወሸቀው ሌላ ሴት ላይ ዓይናቸውን ያንገዋልላሉ የሙሉጌታ አያት ባለሶስት አግር በርጩማ ሳጥኑ አጠገብ አስቀመጡልኝ ሙሉጌታ ከደቀመዝሙሮቹ ጋር በመጨረሻ እራት ላይ ያለ መሰለኝ ዛሬ አባቴፊቴን ሲያጠና የነበረበት ሁኔታ አሁን ገባኝ በሙሉጌታ ላይ ያደረሰውን የጥቃት መጠን ሲፈትሽ ኖሯል አባቴ ድንገት ከሕይወቴ ከመውደዴ ውስጥ ምንጥቅ ብሎ ስተፋው ታወቀኝ ዶከቲር ማርቆስ ላይ እንደሚዝተው ሁሉ ሙሉጌታንም እያስፈራራ ስለመሰለኝ ቁብ አልሰጠሁትም ነበር ዓለማየሁ ገላጋይ ከጠያቂዎቹ መካከል ድንገት ቺ ያጥፋኝ እንዲህ ያደረገውን አውቀዋለሁ የሚል ድምጽ ስሰማ ባነንኩ ሁለቱ ሴቶች መካከል የተወሸቁት ጠና ያሉ ሰው ነበሩ አባገሬ መሆናቸውን አልተጠራጠርኩም «ገሬ አባብዳው አለች አንዲት መጠጥ ያነበዛት ሴት ከወደበሩ አርሶኮ ከዚያ ጉዳይ በቀር ሌላ አያውቁም ነገር እንዳያበላሹ አፏን በነጠላ ሸፈነች ለመከላከል ያሰበችው የመጠጥ ሽታ ግን ቀድሞ ወጥቶ ነበር ያጥፋኝ አልዋሽም እንደግዲህ መጠጥ ቤት ብር ሲያወጣ አይቶት ነው አሉና በጨረፍታ አጨበጨቡ ከሙሉጌታ ጋር ተያየን ድንገት መጽሐፍ ሳላይ የማውቃቸው ገፀ ባህርይ ኑሮዬ ውስጥ ጥልቅ ያሉ ያህል ግርታ ተሰማኝ ከዚህ በኋላ የራሴን ጉዳይ አያብሰለሰልኩ የተጨዋወቱትን አላዳመጥኩም ሙሉጌታ ፊት ላይ የማየው የአባቴን ጨካኝ ገጽታ ነበር አባቴ የሚፈልገውን ለማግኘት አውሬ እስከመሆን ይዘልቃል ብዬ ጠርጥሬ አላውቅም ነበር ምን ማድረግ እንዳለብኝ አወጣሁ አወረድሁ አባቴ በእኔ እንጂ በሌላ በማንም ላይ እንዳልዘመተ ተረድቻለሁ ማጥፋት የፈለገው ሙሉጌታን ሳይሆን የእኔን መንገድ ነው ስል አሰብኩ ይጥቀመኝም ይጉዳኝም መንገዴ ብዬ የያዝኩት አቅጣጫ ከአባቴ ፍላጎትና ጥምቅ ጋር ስላልገጠመ ብቻ የሚጎዳ ሰው የሚበጠበጥ ቤተሰብ መኖሩ ጨነቀኝ አባቴ ዘና ባለ መንፈስ ቁልፎቹን እጆቹ ላይ እንደለማኝ ሳንቲም እያንቀረቀበ እጅ እንድሰጥ የጠየቀኝ መሰለኝ «የአንቺ አሱንና አካባቢውን መተው መድህኑና ህይወቱ ነው ሐብሉ አይንተገተግም ወርቃማ ሰዓቱ የኮቱ እጅጌ ወስጥ አድፍጧል አንድ አዛውንት ድንገት መጥተው ከሐሳቤ አናጠቡኝ የሚሉት ጠርቶ አይሰማም ኃይለሚካኤል እፉፉ መሆናቸውን አልተጠራጠርኩም ሙሉጌታ መመለስ ስለተሳነው አያቱ «ከፉ ቀኽ ከፉ ቀንኘ አሉ ከአሳቸው መልስ ጥያቄውን ገመትኩ የማየው ነገር ሁሉ ወቀሳ ሆኖ አሸበረኝ እዚህ የተሰበሰቡና ሌሎቹም መንደርተኞቾ ሁሉ የአባቴ የግብታዊነት ሰለባ ሆነው በደላቸውን የሚያስጎበኙኝ መሰለኝ ሙሉጌታን ቀና ብዬ አየሁት ለመተንፈስ ሲተናነቅ ሲጢጢጥ የሚል የአየር መጨናነቅ ይሰማል ከዚህ ቦታ መሄድ አማረኝ አያቱን ተከትዬ ወደጓዳ ገባሁ ምን ያህል ብር እንደያዝኩ አላውቅም በጭለማ ውስጥ የታከሲ አስቀርቼ ሰጠኋቸው እየተግደረደሩ እንቢ አሉኝ አልጋው ላይ አስቀምጩ ወጣሁ ሙሉጌታ ሐሳብ እንዳፋፋመው ዲዳ ሆኖ ነበር አንደምንም ብሎ ብዙ የምናወራው አለ» ብሎ አቋረጠ ቤቱ ውስጥ ያሉት ምንትያ ፊቶች በተመሳሳይ አትኩሮት አንደሚመለከቱን ልብ አልኩ ሙሉጌታ ጥቂት ህመሙን አስታግሶ «ከተነጋገርን በኋላ ሁሉም ይደርሳል» አለ ውስጤ ምን አነበበ። ስል አሰብኩ አልመሰለኝም ታዲያ የሱ ብቻ ለምን። ፍቅሬ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀባዥረ ዝናብ ጣለ ተሳስቶም አይመስል ከምሩ ነው የዘነበው ከፉኛም ብርድ ይሰማኝ ጀምሯል ልጅና ፊት አይበርደውም የሚባልልኝን ዘመን እርቄ ማለፌን ልብ እንድል አድርጎኛል ልጆች ሆነን በእንደዚህ ያለ ከረምት ወቅት ፓርላማ ፊት ለፊት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተሰራበት ሜዳ ላይ ኳስ እንጫወት የነበረው ያለ አንድ እራፊ ጨርቅ አራቁታችንን ነበር ምክንያቱም ልብሳቾን ከበሰበሰ አሣር ማየት ስለሚከተል መላ ልብሳችንን አእናውልቅና ትላልቅ ድንጋይ አንከምርበታለን ወይም ለፓርላማ ዘብ ፖሊሶች እንሰጥና እርቃናችንን መጫወት ነው ፊታቸውን የሚሸፍነውን ዝናብ ቶሎ ቶሎ በእጃቸው እየጠራረጉ የላስቲከ ኳስ ተከትለው ግር የሚሉ ብዙ ደራቁቻ እርቃን ሕፃናት ዝናቡ ሲቆም ጭቃው ልጆቹን ከጭታ ተድቦልቡለው የተሰሩ ሲያስመስላቸውና አብዛኛውን ጊዜ የአቅራቢያችን ቤተከርስቲያናት የኔ ቢጤዎች የሚታጠቡበት ምንጭ ላይ ገላቸውን ለመለቃለቅ ግር እያሉ የሚሽቀዳደሙ እግዚአብሔር ፍጥረትን እንደገና ከጭቃ ጠፍጥፎ መስራት የጀመረ ቢመስል አያስገርምም አነዚህ ሕፃናቶቹ መሀል እኔ መኖሬን እጠራጠራለሁ ግን አለሁ አይ ልጅነትዝ ይኸውልሽ እነዚህ ህፃናት ታሪኳን ለጀመርኩልሽ ለዚያች አስገራሚ መንደሬ የራሳቸው አስተዋፅኦ አላቸው በመንደርተኛው የዕለት ተዕለት አኗኗር ላይ በልጆች በኩል ከተመለከትሸው መንደራችን ቅርጺን እንዳትስት ይዘቷን እንዳትለቅ ጥረት የሚያደርጉ ሊመስል ይቸችላል ፍቅሬ መንደራችን የድሆች መንደር ናት ብዩሻለሁ ድህነት በይበልጥ በፀጋ ላልተቀበሉት አንገፍጋፊ ነገር ቢሆንም የድሆች ፈጣሪ ደግሞ ይሄንን አንገፍጋፊ ሸከም ፍጡሮቹ ችለው እስከ ፅለተ ሞቿ ይዘልቁ ዘንድ ማባበያ አለው ምኞት ዓለማየሁ ገላ ይ ጉተ ተ ተ መሓ የመንደራችን ነዋሪዎች ዘንድ ሳይዳላ የተካፈሉት ይህ የከፍተኛ ምኞት ጥሪት ነው ምኛታቸው ደግሞ በየትኛውም አቅጣጫና እምነት ይሁን ብቻ እንዲሳካ ነው የሚሹት ስለዚህ የመንደራችን አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች የሚያመልኩት ሁለቱንም ቃልቻንና እግዚአብሔርን ነው ወደ አንዱ ብቻ ወግነው ከሌላው የሚሰጠው በረከት እንዱጣመልጣቸው አይሹም ዛሬ የማሪያምን ጽዋ አውጥተው ነገ ቃልቻ ቤት ቢያድሩ አዲስ ነገራቸው አይደለም ከመንደራችን ነዋሪዎች ቃልቻ ቤት የማይሄዱት በጣም ጥቂቶቹ ቢሆኑ ነወ እነሱም ለቃልቻ ያላቸው ከበሬታና ፍርሃት ቤቱ ከመሄድና ከመስገድ የሚያስንቅ ነው ታዲያ ይሄ አምነት ለኛ ለውሪዎቹ የቀልድ መፍለቂያ ምንጫችን ይሆናል በትንሽ እራፊ ጨርቅ ላይ አመድ ነጭሽንኩርት የአንቁላል ቅርፊት ኮረሪማና የተቆላ ቡና አድርገን አንዷ በር ላይ መጣል ነው በቃ ሰፈሩ ይታመሳል የተመለከተ ሁሉ እንዳይጠረጠር በመፍራት ባሊ ውኃ እያመጣ አዚያ ሟርት ላይ ሲቸልስ ይውላል እንዲህ ያለው ቀልድ የምናዘወትረው የጠላኮማሪቷ ረታች ላይ ነው ረታች ልብስ ደራርበው መልበስ ይወዳሉ ታዲያ ከላይ ይከመሩና እግራቸው ጀምረሽ ስታያቸው ባለላባ ሰው ይመስሉሻል እስፒል አይን አላቸው እንባቸው ከነዚያ የአተርፍሬ ዓይኖቻቸው የሚወጣ አይመስልም በአንገታቸው ምቀኞቻቸውን አብዝተው ይገምቷቸዋል ስለዚህ እሳቸው በር ላይ ሟርታችንን ከጣልን ድምጻቸውን ቀጠንዘለግ አድርገው ሀብታቸው እንደማይገኝ ከተነተኑ በኋላ እሳቸው የሚሄዱበት አዋቂ ጠንቋይ ለእንዲህ ያለው ስራ አጠፈታውን እንደሚያከብደው ዘርዝረው በመጨረሻ ሆድ ብሷቸው ያሰለቅሳሉ ይሄ ሁሉ ለኛ ለውሪዎቹ ቲያትራችን ነው ቀልዳችን በሌላ መልኩ ጠቀሜታ እንደነበረው አሁን አሁን ይታወቀኛል እኛ ለጨዋታ የሰራነው ሟርት ብዙ የመንደሩን ሰዎች አነካከቶ አሳምቶ አዋቂ ቤት ድረስ አስጎትቶ በመጨረሻ በአንደ ላይ ይላከካል ይሄንን የሚያደርጉት አዋቂ የተባሉት ጠንቋዮች ናቸው እማማ ረታች ቡና ለመጠጣት ከሄዱ ወሬያቸው ይሄው ይሆናል ይሄንን ያደረገቸው ቀይ ናት አንቺ ላይ ከፍተኛ ምቀኝነት አድሮባታል ለሕይወትሸም የምትመለስ አይደለችም ወዘተ ተብያለሁ እያሉ ይንጨረጨራሉ ይዝታሉ አውቄያታለሁኤ ይቺ ለሕይወታችን ጠቀሜታ ያላት ጉዳይ ናት ምናልባት ያ ልምዳችን አንድ ዕውነት ባይፈነጥቅልን ኖሮ እንደ ሕፃናቶቹ ከወላጆቻቸው ጋር ጠንቋይ ቤት ማደር ይሄኔ ጥንቆላን ውርሳቸን አድርገነው ውሎአችን አዋቂ ቤት በሆነ ነበር ትምህርት ሰጪ ኮሜዲ ድራማ የተገኘው ግሪከ ሳይሆን እኛ መንደር ነው ብል ማጋነን ይሆናል። እዚሁ የኖሩበት እኛ እንቀብራቸዋለን አሉ በእርግጥም መንደርተኛው ከመቅበር ሌላ ማድረግ የቻለው አልነበረም አንድ ቀን ከቤት ወደ ውጭ ስወጣ አመት ወደሬ አልጋቸው ላይ ቁጭ ብለው በመስኮት ውጭ ውጭውን እያዩ ልክ እንደ ህፃን ልጅ እእ ኤ እያሉ ያለቅሳሉ ጠጋ ብዬ ምን እንደሆኑ ጠየኳቸው አራበኝነ አሉኝ ይሄንን ገጠመኝ ሳስበው እንባዬ ይመጣል አሁን እንኳን እያለቀስኩ ነው የምጽፈውን ለዚያ ቀን እኪሲ የነበረቸውን አንዲት ብር አውጥቼ ትንሽ ልጅ አስልኬ የሚበሉት አስገዛሁላቸው ይህ የመጨረሻ አልሆነም በተደጋጋሚ ገንዘብ በሌለኝ ሰዓት ላይ ያንጀት የሚበላ ለቅሷቸው አጋጥሞኛል እመት ወደሬ ብዙም ሳይቆዩ በዚያው አካባቢ አረፉ አሁንም ቢሆን መተላለፊያዬ ላይ ያለው መስኮታቸው የሐዘኔ መነሻ የፀፀቴ መንገሻ ነው ፍቅሬ ሁሉም ነገር የከንቱ ከንቱ ከንቱ ሆኖ የሚታየኝ ይሄን ጊዜ ነው የሰው ልጅ። ተፈላጊው ተደብቆ ተደብቆ ሲሰለቸው የሚመጣበት ቦታ ሆኖ ይጠብቀዋል በምንም አይሸነፍም ስል አሰብኩ ሲያገኘኝ አሳሳሙን ጠበቅ አድርጎ ጉንጩ ላይ ቆየ ደስ አለኝ ሰው የበዛልኝ የተከበብኩ መሰለኝ ለባርነት የምፈነገለው እነዚህን ስሜቶች እንደ ክፍያ ቆጥሬ ነው የተለመደው ቤት ቁጭ እንዳልን ትንሽ ቆየት ብሎ ፊቱን አስገረመና ዛሬ አንድ አዛውንት አዝማሪ የመሰንቋቸውን ጭራ በዕጣን እያሟሹ የተቀመጡበት ሆነው አዩኝ አንዲህ በማለት ግጥም ገጠሙ» አንጋጠጠና ለማስታወስ እየሞከረ ሊቃውንት አዋቂ ከሆናችቸሁማ በሉ ቀን ፍጠሩ ሳይውጠን ጨለማ መልሶ ፊቱን ከመደነቅ ወደ መደበብ ወሰደው የሚለቃቅመው እውቀት ብቻ ሳይሆን የሚሰካበት ስስ ብልት አያስገረመኝ ነው ይሄን ግጥም ለምን እንደነገረኝ አውቃለሁ እኔንም ስለሚመለከት ነበር በአርግጥም ለሚፈጠረው የመንደሯ ምስቅልቅሎሽ ሳይሆን እኔን ለሚወለከቱ ሁለት ሰዎች ብቻ አሰብኩ እዚያ መንደር ዓለማየሁ ገላጋይ ውስጥ አራትና አምስት መቶ ሰዎች ጨለማ ሲውጣቸው እኔ ቀን እየፈጠርኩ ያለሁት በአባቴና በፍቅረኛዬ ልብ ውስጥ ለራሴ ብቻ በረጅሙ ተነፈስኩ ደበተኝ ሙሉጌታም እንደደብተኝ አውቆ የተወኝ መሰለኝ በሁለት እግሬ ባለ ተቃራኒ የፍቅር ለመንጠላጠል እየሞከርኩ ነበር አባቴ ሙሌ አሁንም የታየኝ የሳጥናኤል ሰይፍ ስንዘራ የመልአኩ ሰይፍ ምከቶሽ የሁለቱ ሰይፍ ግጭት የሚፈጥረው ብልጭታ ዝ ጨንቆኛል ጧ። «ማንም የማያደርገውን ሽኝት ስላደረጉልኝ አመሰግናቸዋለሁ» ጉንጩን ቆንጠጥ አደረገኝ ነፋስ እንደገፈፈው ነጠላ ብቸኝነት ከላይ ላይ ተነስቶ ሲንሳፈፍ ታወቀኝ እናም ኮንፊሽስ ደቀመዝሙሩን ወደዚያ ግዛት እንዲሄድ ፈቀደለት ዓይኖቼ አሁንም የተዝረበረበው ሰማይ ላይ ነው ጉሙ አስደናቂ ትርኢት በማሳየት ላይ ያለ ይመስላል በነፋስ ኃይል ቅርጹን ይለዋውጣል አንዴ የሰው ቅርጽ ይመጣል ሌላ ጊዜ እንደጉድ ውልድ ሁለት ራስ ያለው ጥጃ ቆየት ብሎ ደግሞ የአበባ ዝንጣፈ ዓለማየሁ ገላጋይ ጆሮዬን ወደ ሳሎን ላኩት ምንም ይዞ አልተመለሰም ሆዴ ውስጥ የሚፈርስ የሚናድ የሚርድ መሬት ያለ መሰለኝ ወደ ሳሎን አመራሁ አባቴ ሰሞኑን ከቤት ወጥቶ አያውቅም እኔ ስገባና ስወጣ እንደሜዱሳ ፀጉሩ እባብ የሆነ ይመስል ሲንቀሳቀስ ይታየኝ ነበር በአንድ ቀልብ ከሚያነበው መጽሐፍ ላይ ውሃ እንደተጎነጨ ዶሮ ቀና ብሎ ሀሳቡን ይውጥና መልሶ ያቀረቅራል ወይም ስልክ ይደውልና ያስታወሰውን ለሰራተኞቹ ያስታውሳል ሳሎን ስገባ አባቴ ከሚያነበው መጽሐፍ ላይ ለአመል ተፋትቶ አየኝና መልሶ ንባቡ ላይ ዓይኑን ጣደ እግሮቹን ጠረጴዛ ላይ አጣምሮ ትከሻውን አስደግፎ ቀና እንዳለ ነው የሚያነበው የለበሰው ተመሳሳይ ነጭ ሸሚዝና ሱሪ ከጥቁር ሴዘሩ የሶፋ ልብስ ጋር ተነጻጽሮ አባቴን አየር ላይ የተንጋለለ አስመስሎታል መጽሐፉ ወደሱ ስለተደፋ ልባሱ በደንብ ይታየኝ ነበር አርበናይዜሽን ኤንድ ኢንቨስትመንት ይላል አባቴ እፍረት የማብዛቱን ጉዳይ አውቀዋለሁ አሁን ድርጅቶቹ ሁሉ እራሳቸውን እየቻሉ ነው እንደ ልጅ ነው ድርጅቅ ይላል «ማዘል የሚያስፈልግሽ ዕድሜ አለው የምትታቀፊው የሚድህበት ቆሞ የሚሄድበትና አንቺን መልሶ የሚደግፍበት ማቹርድ ፔሬድ አለው» አሁን አብዛኞቹ ድርጅቶች ከትትል ቢያስፈልጋቸውም አሱን ሙጥኝ አይሉትም ይሄን ሁኔታ አባቴ የሚወድደው አይመስልም ስለዚህ አዲስ አራስ ድርጅት አቋቁሞ ወደ ማዘሉ ይሸጋገራል የአራት ኪሎው ፕሮጀከት ለአባቴ አዲስ ውልድ መሆኑ ነው ሳሎኑ ተጫጫነኝ ሽንቴም የመጣ መሰለኝ ሙሉጌታ በቅርብ ደቂቃ ውስጥ ከአባቴ ጋ ሊፋጠጥ ይመጣል መቼም ወዳጃዊ ውይይት ሊሆን እንደማይችል ግልጽ ነው አባቴ ለሙሉጌታ ያለው መስተንግዶ የታወቀ ቢሆንም ሙሉጌታ እንዴት ሊስተናገድ አስቦ ይሆን። አባከህ ሙልዬ አትምጣ ወደ መጸዳጃ ለመሄድ በማመንታት ላይ ሳለሁ የግቢ መጥሪያ ጮኽ አባቴ በመጽሐፉ አናት አስታኮ አየኝ የልቤ ምት ሐዘን እንደገባው ሰው ወደፊት ገፋገፋ እያደረገ ሲንጠኝ ታወቀኝ ደግሞ ጮኸ ነፍሴ ስቅቅቅቀ ሲለው ያሰማው ድምጽ መሰለኝ ወደውጪ ልወጣ ስነሳ ቦቹ ከወደ ጓዳ እንደቁልቁለት ላይ ጓል እየተንከባለለ መጣ ደውሏን ሲሰማ በር ሊከፈት እንደሆነ ያውቃልና ለእፍታ ነፃነት ካለበት ቦታ ይመጣል በሩን ስከፍት ቀድሞኝ ወጥቶ የማድያት ጉም የሚያንዣብብበት የድንጋይ ንጣፍ ላይ የውሻ ወጉን ለማድረስ መልከስከስ ጀመረ አባቴ ቤት ሲውል ታስሮ የሚቆየው ሾፌር አለባበሱን አሳምሮ ጋዜጣ ያነባል እኔን ሲያይ ጋዜጣውን እጥፍ ከወገቡ ዝንጥፍ ብሎ ሰላምታ ሰጠኝ ፈዛዛው ዘበኛ ሰው እኔን ከፈለገ በደወል እንዲጠሩኝ የነገርኳቸው ቢሆንም እንግዳውን በመጠርጠር ወደጊቢው አላስገቡትም የሰው መውጪያውን በር ገርበብ አድርገው ይመረምሩታል ይግባ አልኳቸው ኮፍያቸውን ከራሳቸው ላይ ገሸልጠውልኝ በሩን በጥቂቱ ለቀቁለት ዘበኛው ሁልጊዜም ሰው አስገቡ ሲባሱ ቅር የሚላቸው ነዢር አለ «እባከህ ሙሌ አልኩት በዓይኔ ዓይኑ ዝም አለኝ ሳንነጋገር ወደ ሳሎን በር ቀደምኩ ቦቹ አዲስ ሰው ሲመለከት የውሻ ወጉን ለማድረስ ጮኸ የገረመኝ ደግሞ አንደትልቅ ውሻ ለማስፈራራት ማጉረምረም ይደባልቃል ሆን ብዬ ቦቹን ወደውጪ አስቀርቼው ገባን ሙሉጌታ ለጊቢውም ለቤቱም ለሳሎኑም ቁብ ሳይሰጠው በዓይኑ ሰው ይፈልግ ነበር በአጋጣሚ እዚህ ቤት የሚመጡ አንግዶች ቀድሞ አድናቆታቸውን የሚገሰው ጊቢውና ሥነስርዓቱ ነበር እንደውም አንዳንዶቹ ሳሎን ሲገቡ ምንጣፉን እያየ ጫማ ካላወለቅን እያሉ ይገላገላሉ ሙልዬ ግን አባቴ ተከታትለን ስንገባ በመጀመሪያ በግርታ እኔን አየኝ ሙሉጌታን ስላላወቀው ይመስላል አቤቱታ አቅራቢ መስሎት ሳሎን ይው ስለገባሁ በዓይኑ እኔን ወቀሰኝ ቀጥሎ ሙሉጌታ አእምሮው ውስጥ ትውስታ እየገዛ ሲሄድ ሰማዩ ላይ ያየሁትን የጉም ትርኢት የመሰለ የቅጽበት መለዋወጥ ፊቱ ላይ ተነበበ አያንዳንዱ የስሜት ለውጥ በገሃድ ታየኝ ግር መሰኘት ግር ከመሰኘቱ በኋላ ወገግ እያለ የሚሄድ የመደነቅ ጀንበር ፊቱ ላይ ወጣች መደነቁን መደፈር ገሰሰው ከዚያም ዓለማየሁ ገላጋይ ኀዓኀ ዱራ ዓዓ ዓሠ ንዴቱን ለእኔም አካፈለኝ መጽሐፉን ቀስ አድርጎ አጠፈ ጠረጴዛው ላይ ከተዘሩት ሞባይሎች ጋር አስቀመጠ ቀስ ብሎ እግሮቹን አወረደ ቀስ ብሎ ተነሳ ሙሉጌታ ስንገናኝ ያደረገውን ኮት ከነአህያ ጆሮ ኮሌታው ለብሷል ታጥቦ ያልተተኮሰ ሱሪ ታጥቋል ከዓይኑ ሥር ያለው ቁስሉ አርጥብ ኩበት መስሎ አኮፍኩፏል ፊቱ ላይ ምንም አይነት ስሜት አይነበብም ፍፁም እንደተረጋጋ ነው በዓይኖቹ ሰይፍ የተቀመጠው መጽሐፍ ላይ አኮብኩቦ አባቴን መመልከት ጀመረ እኔ መሀል ላይ ውሃ ሆንኩ «ከሰስከኝ።