Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
የሰው ልጅ በራሱ እጅ ፈጣሪን ባለማመኑና ባለመታዘዙ ራሱ ላይ ሞት የባህሪ መጎሳቆል ስዳተኛ መሆን ሰላም ማጣት የመንፈሳዊ እድገት መቋረጥ የፀጋ ልጅነትን ማጣት አመጣ ከዚህ ሁሉ የሚያድነውም አዳኝ አስፈለገው አዳኝም ከአምላክ በቀር ማንም ሊሆን አልቻለም ስለዚህ ራሱ አምላክ ሰው ሆነና የሰው ልጆች ኃጢያት ካመጣው ፍዳዎች ሁሉ አዳነው ፈጣሪውን አሳወቀው ሀዲስ ተፈጥሮ ሰጠው የመሰኮቱ ባህሪ ተካፋይ አረገው ይህንም የመዳን ፀጋ ለሰው ልጆች ሁሉ ሰጠው ይህንም ያደረገው አንዲያው በፀጋው ነው አንጂ በሰው ስራ በፍፁም አይደለም ይህን እንዲያው በፀጋው ለሰው ልጅ የተሰጠውን ድኅነት መቀበል ግን ከእያንዳንዱ ሰው የሚጠበቅ ድርሻ ነው ።
የሰው ልጅ ከሆነ ሰው መሆን መሞትም ይችላል ሞትን ማሸነፍ እና ንፁ ባህሪ መሆን አይችልምአምላክ ከሆነ ደግሞ አምላክ ሰው አይደለም ሟችም አይደለም ስለዚህ አምላክ ፍፁም ረቂቅ የማዳን ጥበብን መጠቀም አስፈለገው ይህም ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆን ነው ሰው ሁሉን ቻይ ስላልሆነ ሰው ቢሆንም አምለክ መሆን አይችልም አምላክ ግን ሁሉን ቻይ ስለሆነ አመላክ ቢሆንም ሰው መሆን ይችላል ስለዚህም ሆነ የሰው ልጅን ሊያድነው የሚችለው አራሱ እአግዚአብአሐር ብቻ እንደሆነ ኣስቀድሞ በነቢያቱ አፍ በብዙ ቦታዎች ተናግሮ ነበር ኢሳ ኢሳ መዝ መዝ ኢሳ ኢሳ ኛ ጢሞ ቲቶ ስለዚህ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አዳኝ ስለሌለ ራሱ አግዚአብሔር ክርስቶስ ሆኖ አዳነን ሐዋ ስለዚህ ራሱ እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አስታረቀን ታረቅንምኛ ቆሮ የአግዚአብሔር ሀሳቡና አላማው ሁሉ የሰው ልጅን ማዳን ነው እግዚአብሔር አምላክ ለእኛ ያደረጋቸው የተለያዩ የቸርነት ነገሮች ሁሉ እኛን ለማዳንና ስለኛ መደና የተደረጉ ናቸው ለምሳሌ የአምላክ ሰው መሆን አላማው ሰውን ማዳን ነበር ዮሐ ሉቃ ዮሐ ዮሐ ዮሐ የነቢያት ትንቢት ዋነኛ መልዕክት የሰው መዳን ነበርጴጥ ሮሜ የሐዋሪያት ዋናው ተልዕኮ የሰው መዳን ነው ማቴ ማር ቆሮ ቅዱሳት መፃህፍት መፅሐፍ ቅዱስ የተፃፋው ለመዳን ዕውቀት ነው ዮሐ የእያንዳንዱ መንፈሳዊ ትምህርት ሁሉ ዞሮ ዞሮ ዋናው አላማውና ግቡ የሰው ልጅ መዳን የዘለዓለም ህይወት መውረስ ነው ኢየሱስ የሰው ልጆችን አዳነ ስንል ምን ማለታችን ነው። ታችን እኛ ከሞትና ከእርግማን ዮ አንድን ዘንድ ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ አቀረበ ኤፌ ክርስቶስ የመጣው ከኃጢያት ብቻ ሊያድነን ሳይሆን ከሞትም ሊያድነን ነው ዮሐ በጌታችን ሞት ሞት ድል ሆነ ሲኦል ተመዘበረ መቃብር ተከፈተ ለዚህም ምስክሮችና በኩራት እንዲሆኑ ሙታን ከመቃብር ተነስተው ለሰዎች አንዲታዩ አደረጋቸው ማቴ በሞቱ ሞትን ሻረው ለዚህ ነው የኃለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው የተባለው ቆሮ ስለዚህም ጌታቸን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነውና መከራን የተቀበለው ስለኛ አስከሞትና መቀብር ድረስ የደረሰው መከራን በፍቃዱ ለመቀበል ነው ዮሐ ቀላ ሐዋ ሮሜ ኤፌ ቆላ ዕብ ስለዚህ ያኔ ከበላህ ትሞታለህ የሚለው የህግ ትዕዛዝ ከበላህ የዘለዓለም ህይወት ይኖርሃል በሚል ሀዲስ ኪዳን ተለወጠ ዮሐ በብሉይ ኪዳን ዘመን ሰው ሁሉ በሞት ጥላ ስር ተይዞ በሞት ፍርፃት ይኖር ነበር መዝ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ሞት የሚስማማውን የእኛን ስጋ በመዋሃድ ሞታችንን ሞቶ በሞቱ ሞትን አጠፋልን የአርሱን ህይወት ለእኛ ሰጠንሞትን በትንሳኤ ለወጠልን በክርስቶስ ኢየሱስ ያለንን ከሞት ፍርሀት ነፃ አወጣን ዕብ ስለዚህም ሞትን ክርስቶስ ድል ከነሳው በኃላ ሞት ለክርስቲያኖች ወደ ዘለዓለማዊ ህይወት መሸጋገሪያችን ነው ሞት በአዳም በኩል መጣ በዳግማዊ አዳም ደግሞ ህይወት ቆሮ ስለዚህም በክርስቶስ የሚያምኑ የሚሞቱት አፈር ነህና ወደ አፈር ትመመለሳለህ ዘፍ ስለተባለ ሳይሆን ለትንሳኤ ነው ሮሜ ቆሮ ከሞት ከተነሳንም በኃላ ደግሞ ሞት የሚባል ነገር የለም የሚበሰብሰው ስጋችን ቀርቶ የማይበሰብስ ስጋን ለብሰን እንነሳለን ቆሮ ስለዚህ መዳን ስንል በኃጢያት ምክኒያት ከመጣብን ነገር ሁሉ ሞትን እርግማንን ጉስቁልናን ባርነትን ሁሉ አስወገደልን በአንፃሩ ደግሞ ህይወትን ልጅነትንአለመሞትን ሰጠን ማለት ነው ይህ ግን አንዱ እንጂ ብቸኛው አይደለም ፈጣሪውን አንዲያውቅ መሆን አግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ ሲፈጥረው በአምስቱም ቀናት ከፈጠራቸው ስነ ፍጥረታት ሁሉ አብልጦና አክብሮ በአራያውና በአምሳሉ ነበር የፈጠረውየሰው ልጅ ግን ይህን የመሰለ ፀጋና ክብር አቀለለ ስለዚህም ወደ ምድር ወርዶ ከአርሱ በታች የሆኑትን ለአርሱ እንዲያገለግሉ የተፈጠሩትን ፍጥረታት አመለከ ሮሜ ኢሳ የሰው ልጅ ሁሉን የፈጠረለትን አምላክ ረስቶ ለአርሱ የተፈጠሩ ፍጥረታትን እያመለከ አስከመጨረሻው አንዲኖር ግን አምላክ አልፈቀደምየሰው ልጅ አወቅን ተራቀቅን ተጠበብን » እያለ ፍጡራንን ሲያመልክ የሰው ጥበብና አውቀት ሰፊ ግዜ ቢሰጠውም ቅድመ ክርስቶስ የነበሩት ዘመናት ሁሉ ነገር ግን ትክክለኛ አምላኩን ሁሉም የሰው ልጅ ስላላወቀ አምላክ በሚታይ ስጋ በመገለጥ አራሱን ለሰው ገለጠ ጢሞ ቆሮ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ የፈጠረንን አምላክ አኛ በሚገባንና በምንረዳው መልኩ አስተማረን ገና በጥምቀቱም ልዩ ሶስትነቱን ገለፀልን ማቴ በትፅዛዝ ደግሞ ልዩ የሆነ የስም ሶስትነትን ገለፀልን ማቴ ለዚህ ነው ቅዱስ ዮሓንስ አግዚአብሔርን በመለኮቱ ያየው ማንም እንደሌለና ክርስቶስ ሰው በመሆኑ እንደተረከልን የተናገረው ዮሓ ሶስትነቱን ብቻ ሳይሆን አንድነቱንም አስተማረን ዮሓ በብሉይ ኪዳን በስነ ፍጥረቱ በነቢያትና በቅዱሳኑ አፍ ሲያስተምር የነበረ አምላክ በሀዲስ ኪዳን ራሱ ሰው ሆኖ ራሱ አስተማረዕብ ዮ። ዮ እግዚአብሔር ከመዳነ ውጪ ያደረገውና ይህን የመዳን ጸጋ የነፈገው ማንም ሰው የለምሁሉም የተጠራው ለመዳን ነውአግዚአብሔር በአጠቃላይ የሰው ልጅ በሙሉ ይድኑ ዘንድ ይወዳልጢሞ ዮሐ ማንኛውም መዳን የሻተ በርሱ ያመነ ሁሉ መዳን ይችላልስለዚህ መዳን የእግዚአብሔር ቸርነት ለሰው ሁሉ የተሰጠ ጸጋ እንጂ በቅድመ ምርጫ ለተወሰኑ የተሰጠ አይደለም ይህን ፀጋ በመጠቀም የሚድኑት ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ ይህ ግን እያንዳንዱ በራሱ ስንፍና ምክንያት ይቀርበታል እንጂ አስቀድሞ ለመዳን እንዳይችል ስለተወሰነበት አይደለም አንዳንዶች አንደሚሉት የሚድኑ አስቀድመው የተመረጡ ከሆኑ የጌታ ሰው መሆን መውረድ መወለዱ መከራ መቀበሉ ወንጌል መስበኩ ምስጢራትን መስጠቱ ሁሉ ከንቱ ድካም መሆኑ ነው ስለዚህ መዳን በዚህ ዓለም ላሉ ለሰው ልጆች ሁሉ የቀረበ የተዘጋጀላቸው ማዕድ ነው መጠቀም አለመጠቀም የእያንዳንዱ ድርሻ ነው ጌታ ግን ሁሌም ወደ ሠርጉ ነ በሏቸው እያለ እየጠራ ነውማቴ መዳን ድኅነት የእግዚአብሔር ስጦታ ወይስ የሰው ስራ ውጤት እግዚአብሔር የሰጠን የመዳን ፀጋ የቸርነት ውጤት ነው በአርሱ ነዛ ፍቅር እንጂ በሰዎች መልካምነት ወይም ተጋድሎ የተገኘ አይደለም ከፍፁም ቸርነት የተሰጠን ጸጋ እንጂ ድኅነታችን የተገኘው በእኛ ሥራ በፍፁም አይደለም የእግዚአብሔር የቸርነቱ ስጦታውና ለሰው ያለው የማይለወጥ ፍቅሩ መገለጫው እንጂ ኤፌ ቲቶ ወንጌላዊው ዮሓንስም ጌታችን ሰው የሆነውና የሰውን ልጅ የወደደው እንዲሁም ያዳነው እንዲሁ በአባታዊ ፍቅሩ መሆኑን ሲገልፅ አንድያ ልጁን አስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን አንዲሁ ወዲልና ዮሓ አንዲሁ ማለትም ያለምንም ዋጋ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በነጻ ማለት ነው የወደደን የሚወደድ ነገር ስላለን ወይም ስለወደድነው ሳይሆን አንዲሁ በቸርነቱ ነው ሰውማ የፈጠረውን አምላክ ትቶ ለዲያብሎስ ባርያ ሆኖ ነበር እንዲ ሆነን ሳለን ግን ሀያል ወልድን ፍቅር ከመንበሩ ሳበው ከሰውም ምንም ሳይጠብቅ አንዲሁ ነብሱን እስኪሰጥ ወደደውቆላ ሮሜ ሮሜ ጵጥ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሓንስም በስፋት ይገልፃል ዮሓ ስለዚህ ሰው የዳነው በፀጋው አንጂ በራሱ ስራ አይደለም በራስ ስራ መዳን ቢቻል ኖሮ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን ለመዳን ክርስቶስ ባላስፈላጋቸው ነበር ነገር ግን ምንም አንኳ ብዙ መልካም ምግባር ቢኖራቸውም በቅጣት ከመጣው አንዲቱን እንኳን ፈቀቅ ማድረግ አልቻሉም ስለዚህ እንዲሁ የእርሱ ፍቅር አስፈለገ ኢሳ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ይህን የመዳን ትምህርት ከምንም በላይ ትጠብቀዋለች ታስተምረዋለች በተግባርም ትተኖረዋለች ለመዳን እያንዳንዱ ሰው ምን ይጠበቅበታል እዚህ ጋ ነው በማስተዋል ልናጤን የሚገባን በእግዚአብሔር በኩል ሰውን ለማዳን አስፈላጊ የሆነው ያአምላክ ድርሻ ሁሉ ተፈፅሟል ማንኛው ሰው ሁሉ መዳኑ በአምላክ ያልተፈፀመለትና የቀረ የለም እግዚአብሔር ሰርጉን ደግሶ የሚያስፈልገውን ሁሉ አሟልቶ ፈፅሞ አዘጋጅቶ ሁሉም ተዘጋጅቷል ወደ ሠርጉ ነ በማለት እየጠራ ነው ማቴ የእግዚአብሔርን ጥሪ እሽ ብሎ ተቀብሎ የሠርግ ልብስ ለብሶ ወደ ሠርጉ ቤት መግባት የእያንዳንዱ ድርሻ ነው ሁ በራሱ የመዳን ዛደት ውስጥ እያንዳንዱ ሰው ድርሻ አለው ወይስ የለውም። የሚድኑትም የማይድኑትም አስቀድሞ ተወስነዋል ሰው በራሱ መዳን ወይም አለመዳን ላይ ድርሻ የለውም የሚለው ደግሞ የአውግስጢኖስ ትምህርት ነበር በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘን ሁለቱም የተሳሳተ አመለካከት ነው ቢሆንም ግን እስካሁን ባሉ አማኞች ላይ አሻራቸውን ሳያሳርፉ አልቀረምበተለይ ሠው በራሱ ኃጢያት አለመስራት ንፁ መሆን መልካም ፍሬ ብቻ ማፍራት አይችልም ከእግዚአብሔር በሚሰጠው ፀጋ በማመን ብቻ እርሱ ባይፈልግም እንዲሁ በእርሱ ያደረው መንፈስ መልካም ያሰራዋል የሚለው የአውግስጢኖስ ትመህርት ብዙዎችን አሳምኗል ኦርቶዶክሳዊና መፀሐፍ ቅዱሳዊ የመዳን ትምህርት ግን ከሁለቱም አስተሳሰብ ነፃ ነው እንደ ፔላጊዮን ሠው ያለ አምላክ የመዳን ፀጋ በራሱ መዳን ይችላል አይልም እንደ አውግስጢኖስም ሰው ከእርሱ ምንም ሳይጠበቅ ይድናል አይልም የተፈፀመልን የእግዚአብሔር የመዳን ድርሻ አለ እኛም መፈፀም ያለብን የመዳን ድርሻ አለ በመዳን ድርሻ ዋነኛው የክርስቶስ ቢሆንም የሰው ልጅ የራሱ ነፃ ፈቃድ ድርሻ አለው እነጂ በግዴታ የሚጫንበት አይደለም በመዳን ትምህርት የእግዚአብሔርን የማዳን ድርሻ መፈፀም እየጠቀሱ ድኛለው ድኅነቴ ተፈፅሟል እያሉ የሚፎክሩበት ሳይሆን ቅዱስ ጳውሎስ በመፍራትና በመንቀጥቀጥ የየእራሳቹን መዳን ፈፅሙ ፊሊ በማለት እንዳስተማረው እግዚአብሔርን በመፍራትና በተጋድሎ እስከመጨረሻው በመፅናት የምንፈፅመው ነውይህ መልዕክት የተላከው ለፊሊሏሲዩስ ክርስቲያኖች ነው ታዲያ መዳናቸው ተፈፅሞ ከእነርሱ ምንም ማይጠበቅ ከሆነ በክርስቶስ አመነው ክርስቲያን የሆኑትን ለምን የየራሳችሁን መዳን ፈፅሙ አለ ሠው የዳነው በፀጋው መሆኑን በ ላይ በስፋት አይተናል ይህንን ፀጋ ግን በከንቱ እንደማንቀበል ተናግሯልቆሮ ቆሮ ይህ ማለት አምላክ ያደረገልንን የማዳን ፀጋ ከእኛ የሚጠበቀውን ነገር ምንም እንኳን የፈለገ ነገር ብናደርግ ለፀጋው የማይመጥንና እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ማድረግ አለብን ማለት ነው ስለዚህ የሰው ልጅ ለመዳን እግዚአብሔር የፈፀመው ብቻ በቂ ነው ማለት ስህተት ነው ምክኒያቱም እንድያ ቢሆን ድኀነቱ የተፈጸመው ለሰው ልጆች ሁሉ ነውና የሰው ልጅ ሁሉ መዳን አለበት በመፅሐፍ ቅዱስ መሠረት የሰው ልጅ ለመዳን የሚከተሉት የግድ መፈፀም ያለበት ድርሻዎቹ ናቸው እምነት ማመን እምነት ተስፋ ስለምናረገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውን ነገር የሚያስረዳን ነውዕብ ማመን ማለት በዋናነት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ መዳን ያደረገውን ነገር ሁሉ ማመንና መቀበል ነው ። በመፅሐፍ የገለጠውንና ያስተማረውን ሁሉ ማመን ነው ክርስቶስን ከማመን የእግዚአብሔርን መኖርና አምላክነት ማመን ይቀድማል አምላኩን ያላወቀ አምላክ ያደረገውን ማወቅ አይችልምና ስለዚህ እምነት የአምላክን መኖር የእርሱን አምላክነት ፈጣሪነት ልዩ የሆነ ሦስትነት እና አንድነቱን በማመን ይጀምራል ሲቀጥልም ይህ ድንቅ አመላክ ስለሰው ልጆች ሲል ያደረገውን እያንዳንዱን ነገር አዎን ስለኔ ብሎ አድርጉዋልሆኑዋል ተብሎ ይታመናል ማለትም ልደቱን መጠመቁን ዞሮ ማስተማሩንመከራ መቀበሉን ለኛ ሲሊ በፍቃዱ መሞቱን መቀበሩንና በሦስተኛው ቀን ሞትን ዮ ድል አድርጎ መነሳቱን በኛው ቀን ወደ ቀደመ ክበሩ ማረጉንና ባአባቱ ቀኝ መቀመጡን ሁሉ ማመን ለመዳን አስፈላጊ ነውበመፅሐፍ ቅዱስ ያሉትን የአግዚአብሔር ቃላት ትዕዛዛት ህግጋት አንዲሁም ትምህርቶችሁሉ ከዘፍረት እስከ ራዕይ ያላንዳች ጥርጣሬ ማመን ያስፈልጋል ጸራዕ ዮሐ መፅሐፍት ሁሉ ደግሞ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ በግልፅም ይሁን በምስጢር የሚያወሩት ስለ ከርስቶስ ነው ዮሐ ሮሜ ስለዚህ የሰው ልጅ ለማዳን በአንዱ በአግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን አለበት ያላመነ አሁንም በእግዚአብሔር ቁጣ አለ በልጁ የሚያምን የዘለዓለም ህይወት አለው በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ህይወትን አያይም እንዳለ ዮሐ በኢየሱስ ከክርስቶስ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ህይወት አለው ዮሐ ዮሐ የማያምን ግን በፍርድ ውስጥ ነው ዮሐ ለዚህ ነው ሐዋርያትም እድን ዘንድ ምን ላድርግ ለሚላቸው በኢየሱስ አመን አንተና ቤተሰቦች ትድናላቹ እያሉ የሚያስተምሩት ሐዋ ታዲያ ለመዳን ማመን ወሳኝ ከሆነ እንዴት ነው ማምነው ምንስ ብዬ ነው ማምነው የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ነው እምነት ከመስማት ነው መስማትም በአግዚአብሔር ቃል ነው ሮሜ ስለ ኢየሱስ በቅዱስ ቃሉ የተነገረውን ሁሉ ያደረገውን ስለ እኔ ሲል ነው ለእኔ ብሎ ነው ማለት ነው ስለ እኔ ሠው ሆኗል ስለ እኔ መከራን ተቀብሏል ስለ አጌ በፈቃዱ ሞቷል ከዘለዓለማዊ ውድቀት አድኖኛል የዘለዓለም ህይወት ሰጥቶኛል አርሱ የአግዚአብሔር ልጅ ነው አርሱ ራሱ አምላክ ነው ከእራሱ ጋ አስታርቆኛል እኒህን ሁሉ የሚነግረንን ቅዱስ ቃሉንአዎን አሜን አውነት ነው አምናለሁ ብሎ መቀበል እና ኢየሱስ ክርስቶስን በመጽሃፍ ቅዱስ በተገለጸው እውነተኛ ማንነቱ ማመን ማለት ነው ይህም ነው ዘለዓለማዊ ህይወትን የሚያሰጥ አንዳነንዶች እንደሚሉት ሀሳቡ ትክክል ቃሉ ግን ፍፁም ስህተት የሆነ በመፅሐፍ ቅዱስም የሌለና ያልተፃፈ የሰዋስው የቃላት አገባብ ስህተትም ያለበት ጌታን እንደ ግል አዳኝ አድርገ ተቀበል የሚባል የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ያልሆነን ትምህርት ስህተትነቱን ግን ሳንገልፅ አናልፍም በአርግጥ የዚህ ቃል ተጠቃሚዎች ሀሳቡን ሲያብራሩት እያንዳንዱ ሰው የሚጠየቀው በግሉ ነው ማመንም ያለበት በግሉ እርሱ አራሱ ነው የሚሉት ትክክለኛ ማብራርያ ነው ነገር ግን ሲጀመር በማህበር ማመንና መቀበል የሚባል ነገር የለም የማኅበር እምነት የለም በልባችን ያለው አምነት አንጂ የምናምነው ነገር የግል አይደለም ። ከዚህ በላይ ጥምቀት የት ነው ያለው እኛስ የምንጠመቀው እንደ እርሱ ከክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ጋር ለመተባበር አይደል ሪረ ሜሮን ለመዳን የግዴታ አስፈላጊ የሆነው ሌላኛው ምስጥር ሜሮን እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱስ ያስተምራል ሰው ከተጠመቀ በኃላ መንፈስ ቅዱስ ሊወርድበት ግድ ነው መንፈስ ቅዱስ ካልወረደለት ልጅነቱ አይረጋገጥም ጥምቀቱን በትምቀቱ የመሠረተልን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለዚህ ነበር ልክ ከተጠመቀ በኃላ መንፈስ ቅዱስ የወረደበትና አብም የምወደው ልጄ ይህ ነው ማለቱ ይህን ምስጥር ሲያስተምር ነበርማቴ ስለዚህ ሰው ከተጠመቀ በኃላ መንፈስ ቅዱስ ሲወርድበት ልጅነቱ ይረጋገጣል በእግዚአብሔር የምወደው ልጄ ይባላል ይህ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት እጅ በማጫን ነበር የሚተላለፈው ነገር ግን ሐዋርያቱ በዓለም ሁሉ እየፄዱ እያንዳንዱን ሰው እያጠመቁ ለዓለም ህዝብ ሁሉ እጅ እየጫኑ ይህን ስርዓት በፈፀም ስለማይቻል በሲኖዶሳቸው እጅ በመጫን ይተላለፍ የነበረው መንፈስ ቅዱስ በሜሮን አማካኝነት እንዲተካ አደረጉ ር«ሩ ሜሮን ቃሉ የግሪክ ሲሆን የአማርኛ ትርጉሙ ቅባዓት ማለት ነው ሜሮን ከተለያዩ እፅዋት እንደሚዘጋጅ እራሱ እግዚአብሔር ለሙሴ አዘገጃጀቱን ነግሮታል ዘፀ ሐዋርያት እጅ በመጫን ያሳድሩ የነበረው መንፈስ ቅዱስ በሜሮን አማካኝነት ያስተላለፉ እንደነበር መፅሐፍ ቅዱስም ይናገራል ። ለምሳሌ ዮሐ መንፈስ ቅዱስ ይወርዳል ሲባል የፀጋን ስጦታ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ይሰጣል ማለት እንጂ ከሠማይ ወደ ምድር ይወርዳል ማለት አይደለም ለሐዋርያቱም መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው ሲል በልሳን የመናገር ፀጋን ሰጣቸው ማለት ነው ከዛ በፊት ይህ ፀጋ አልነበራቸውም ሐዋ ሩ በነካ እጃቸን አንድ ለማለት ያህል የመንፈስ ቅዱስ ስራ አሰራር በኦርቶዶክስ ዘንድ የለም አይታይምም እሚሉ አንዳንድ ሰዎች አልጠፉም እነደው አለማወቅ እንጂ የመንፈስ ቅዱስ ስራ በኦርቶዶክስ ዘንድ ብቻ ነው ያለው ቢባል ምንም ስህተት አይሆንም ን ዕር በቤተክርስቲያናችን ያለመንፈስ ቅዱስ የሚከናወን አንድም ነገር የለም በዓመት ቀን በሚቀደሰው ቅዳሴዋ ቀን ህማማት ላይ ብቻ አይቀደስም ገና ሲጀምር ምንድነው ሚባለው። ይልቅ እንዲ የሚያረገው ምን አይነት መንፈስ እንደሆነ መፅሐፍ ቅዱስ ገልፆታል ማር ሉቃ ስለዚህ ይሄን ካላየ ኦርቶዶክስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የለም የሚል ምስኪን ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ የሆነን ነገር ለወደፊቱም በቤተክርስቲያኒቱ እንደማይኖር ይወቅ ቅዱስ ቁርባን ዮር«ሩ እየተመለከትን ያለነው የሰው ልጅ ለመዳን የግዴታ መፈፀም ያለበትን ከእርሱ የሚጠበቁ ድርሻዎች ነው ሌላኛው ለመዳን ወሳኝ እና ግዴታ የሆነው ነገር የክርቶስ ኢየሱስን ክቡር ስጋ እና ክቡር ደም መብላትና መጠጣት ነው የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋ መብላት ደሙንም መጠጣት መቁረብ ብዙ ፀጋዎች እንደሚያስገኝ ቅዱስ ቃሉ ያስተምራል ሀ የዘለዓለም ህይወት ይገኝበተል የዘለዓለም ህይወትን ለማግኘት ቅዱስ ስጋውና ደሙን መቀበል ግድ ነው ይህን ራሱ ክርስቶስ በማያሻማ ቃሉ ይናገራል እውነት እውነት አላችዋለሁ የሰውን ልጅ ስጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችው ህይውት የላችውም ስጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላዓለም ህይወት አለው ዮሐ ስለዚህ ይህን ያልፈፀመ የዘለዓለም ህይወት የለውም ለ የህይወት እንጀራ ነው ከሠማይ የወረደ ህያው እነጀራ አፄ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘለዓለም ይኖራል እአፄም ስለዓለም ህይወት የምሰጠው እንጀራ ስጋዬ ነው ዮሐ የህይወት እንጀራ እርሱ ብቻ ነው ይህን የህይወት እንጀራ ያልበላ ህይወት አለኝ ማለት አይችልም ሐ የኃጥያት ስርየት ይገኝበታል ዕዋንም አንስቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ ሁላችሁ ከአርሱ ጠጡ ስለብዙዎች ለኃጢያት ይቅርታ የሚፈስ የሀዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው ማቴ ያ ደሜ ነው ብሎ የሰጣቸው ቅዱስ ደሙ የኃጥያት ይቅርታን የሚያሰጥ የሀዱሱ ኪዳን ደም መሆኑን ነገረ በሌላ ቦታም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያነፃናል ዮሐ ይላል ስለዚህ ደሙን የኃጢያት ስርየት ይሰጣል መ ከአምላክ ጋር አንድነት ይኖረናል ስጋይን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ ኖራለው ዮሐ ስለዚህ እርሱ ከእኛ ጋር እንዲኖር የግድ ስጋውን መብላት ደሙንም መጠጣት አለብን ይህን ሳያደርጉ ክርስቶስ በአኔ ይኖራል እኔም በአርሱ ዘንድ አለው ማለት ዘበት ነው ሠ በእረሱ ከሚያምኑት ጋር አንድ ህብረት ይኖረናል የምንባርከው የበረከት ዕዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ህብረት ያለው አይደለምን ። ይህ ማለት ደግሞ አምነት ብቻ ነው የሚያድነው ማለት አይደለም ቅዱስ ጳውሎስ በእምነት ብቻ አላለም የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ አያስፈልግምም አላለም ምግባር ትሩፋት አያስፈልግም አላለም ስለዚህ ስለ ሕገ ኦሪት ያወራውን ሁሉ ሕግ የምትለዋን ቃል ብቻ ነጥሎ በመውሰድ መልካም ሥራ የመስራትና የአግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ለመዳን ምንም ጥቅም የለውም ማለት ትልቅ ስህተት ነው መልካም ምግባርና የአግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ለመዳን የግዴታ እንደሆኑ ከላይ አይተናል ሕግን የሚጠብቅ ነገር ግን በአንዲቱ የሚሰናከል ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል ያዕ የሚለውን በመጥቀስ እንድ እንኳን ኃጢያት ብንሰራ ይፈረድብናል ሰው ደግሞ ሁሉንም ሕግ መጠበቅ አይችልም ስለዚህ በፀጋው ነው እንጂ ሕጉን በመጠበቅ ርስቱ አይወረስምይላሉ በመጀመርያ ደረጃ አውነት ነው በቸርነቱ እንጂ በስራችን አይደለም ርስቱን ምንወርሰ ሲቀጥል ደግሞ የሰው ልጅ አንድም ኃጢአያት ያልሰራ ባይኖርም ኃጢአያት አለመስራትና ፍፁም መሆን ግን ይችላል ሐዲስ ተፈጥሮ በሚለው ርዕስ ውስጥ በሰፊው ተዳሷል ከአምላክ ባህሪ ተካፋይ ሆነ የሚለው ላይም በስፋት አይተናል ሲቀጥል እዚህ ጋር ያፅ ላይ ቅዱስ ያዕቆብ እያወራ ያለው ስለ አሰርቱ ትዕዛዛት ሲሆን አንዱን ጠብቆ አንዱን ስላለመጠበወቅ ነው የሚገልፀውእስከ ቁጥር ይመልከቱቱን ትእዛዛት መጠበቅ ደግሞ ከባድ አይደለምበአጭሩ ባልንጀራውን የወደደ ሁሉንም ፈጽሞታለ ሮሜ ስለዳንኩኝ እንጂ ለመዳን አይደለም የምሰራውይላሉየምንሰራው ድኅነትን ስለተቀበልን ብቻ ሳይሆን ግን የተቀበልነውን ድኅነት እንዳናጣውም ጭምር ነውይህንም ከላይ አይተናል ብዙ አሉባልታዎችን ያወራሉ ኦርቶዶክሶች ገዳም ካልተኬደተራራ ካልተወጣቁልቁለት ካልተወረደበዙ ካልተሰገደ ድኅነት የለም ይላሉይላሉይሄ ግን ያለማወቅ አሉባለታ ነው « ማጠቃለያ ድኅነት የትምህርት ሁሉ ራስ ሲሆን ይህም የሰው ልጅ በራሱ እጅ ካመጣው ወድቀቶች እና ድቀቶች ሁሉ በዘለዓለማዊ መድኃኒት ስለ መዳን በሰፊው ያትታል የሰው ልጅ በራሱ እጅ ፈጣሪን ባለማመኑና ባለመታዘዙ ራሱ ላይ ሞት የባህሪ መጎሳቆል ስዳተኛ መሆን ሰላም ማጣት የመንፈሳዊ እድገት መቋረጥ የፀጋ ልጅነትን ማጣት አመጣ ከዚህ ሁሉ የሚያድነውም አዳኝ አስፈለገው አዳኝም ከአምላክ በቀር ማንም ሊሆን አልቻለም ስለዚህ ራሱ አምላክ ሰው ሆነና የሰው ልጆች ኃጢያት ካመጣው ፍዳዎች ሁሉ አዳነው ፈጣሪውን አሳወቀው ሀዲስ ተፈጥሮ ሰጠው የመሰኮቱ ባህሪ ተካፋይ አረገው ይህንም የመዳን ፀጋ ለሰው ልጆች ሁሉ ሰጠው ይህንም ያደረገው አንዲያው በፀጋው ነው አንጂ በሰው ስራ በፍፁም አይደለም ይህን እንዲያው በፀጋው ለሰው ልጅ የተሰጠውን ድኅነት መቀበል ግን ከእያንዳንዱ ሰው የሚጠበቅ ድርሻ ነው ።