Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
ቀጥሎም ኪነጥበብ ከቀዋሚ የኑሮና የመደበኛ ሥራ ክፍሎችም ጋር እያደር ተደጋግፎ ሲጠና እንደየሥራው አንፃር ለምሳሌ በሠርግና በቀብር ሥርዓት አማካዩን የዘፈንና የሙሾ ግጥሞች በግብርና የግብርና ጠቀስ ግጥምና ዜማዎችን በሃይማኖትና በአምልኮ ባዕድም የኒሁኑ ጠቀስ ባስመዝሙር ባለጸሎት ባለወረብ ባለወሸባና ባለዝየራ ግጥሞችን ተከባክቦ ይታያል እዚህ ሳላይ ዋና ዋናው ተግባር ያው ሠርጉ ቀብሩ ግብርናው ሃይማኖቱና እምልኮባዕዱ ሲሆን ለየጉዳዩ የተደረደረው ግጥም ግን ለየተግባሩ ተቀጥላነትንና ማሞካሸትን ይዞ ኖረ ማለት ነው። ምክንያቱም በጠቅላላው የኪነ ጥበብ መልእክት ከሰው ተፈጥሮ ወደስው ሆኖ ተቀባይነቱም እንደየዘመኑና እንደየትውልዱ የጣዕምና የዝንባሌ ዳኝነት የሚመጠን ስለሆነ ነው። የሁለቱ የታሪክ ልዩነት ይኸ ነው። እንደዚሁም የአክሱማውያን ሥልጣኔ ተነስቶ በደመቀበት ከክርስቶስ ልደት በፊት በሰድስተኛውና በይበልጥም እሰከ አራተኛው ዓመተዓለም ግድም እንደነአሰታርና አልሙጋህ ያሉትን የሳባውያን ሥርዓተአምልኮባዕድምና የኩሽንም ወገን ሥርዓተአምልኮባፅድ ተንተርሶ ከኒህና ከሌሎችም ቋንቋዎች ተወራርሶና ተዳቅሎ የተፈጠረው የግዕዝ ቋንቋ በየጊዜው ቀምሮት ከነበረው ከሥነግጥሞቹ የመሠረት ሥርዓተድንጋጌዎች ውሰጥ ዛሬም በኒሁ ቋንቋዎች በተለይም በኩሽና በሳባዊው የአረብ የስንኝ ሰልት ድንጋጌዎች ውሰጥ ማለት የወል ቤት እንዳልነው ባለሰድስት ሁለት ባለሦስት ሐረግ እንደሆያሆዬና እንደ ሰንጎ መገንና ከቡሄ በሉ ቤት አፈራርቆ እንደሚደረደረውና እንደሚደረደሩት ብዙዎች የኩሽና የሳባውያን አረብ ዲቃላ ቋንቋዎች የዘልማድ ሕግጋት ሳይሆን የቁጥሩን መለያ መሠረት አንድ ራሱን በስምንት የሰንኝ ሰልት ድንጋጌ ላይ ስለምደረድረው ብቻ ነው። ቹ ከዚህም ሌላ ለአንባብያን ላሳሰታውስ የምወደው ለምሳሌ እናት ማለት ህዳ ለሚለው የኦሮምኛ የኩሽ ቃል ዳ ለተሰኘው ትክክለኛ የልሣን ምልክት በቀደምቱ በኢሮግሊፊክ ፊደል እንጂ በኋለኞቹ ወራሾች በሴማውያን ወይም በግሪክና በላቲን ፊደሎች ውስጥ ሰላልተመደበለት እነሆ ለጊዜው ደ በተሰኘው የሳባውያን ወይም የግዕዝ ፊደል አናት ላይ ይኽን ቁምሠረዝ በማከል እያስኘሁ መጠቀሜን ነው። ይህም ማለት የዘልማድ ንፍገት ያጥሳሳውን እውነታ ደሞ አባብሰን በይበልጥ ለማጐልደፍ ሳይሆን ይልቅሰ ውስጣዊና ሕያዊ ባሕርዩን መርጦ አንቅቶ ውበት አክሎ በአሰተዋይ ኅሊናችን ውስጥ ቁሰሉን የመፈወሱም ጥረት ለሥነግጥም ያው የኖረ ጠባይዋና ደመሕይወቷ ነው። ደባርቅ ሀድ መርካቶ ን ጉለሌ ሀ ቆቃ ሁሱቃ እንዳሥላሴ ቀበና ሊበን ዓድዋ ሰድሰት ኪሎ ፅ ቢሾፍቱ እዲባባ ሚኩ እከካም ተማሪ። ለአንዲት የቅኔ ምሽት ረሃብ ስንት ቀን ይፈጃል። ጥቅምት ፒያሳ አዋሽ እስከመቼ ይሆን አዋሽ። ያባቶችህ ያይን ድንበር ክተረከዘ ሎሚ ሳያልፍ አንተ ግን ጆቢራውዘራፍ ጠረፍ አይወስንህ ጉብል ጥሎህ በዘመንህ ዕድል ዓይንህ ባት አልፎ እንዲዋልል ቴህ ወዲያ ጀግንነት የለ ተዚህ የከረረ ግዳጅ ባደባባይ የዱር ገደል ስትናደፍ የእግር አዋጅ ሌሊቱን በየሌት ግለብ ቀኑን ጭምር በጠራራ ሲነጋ እንደጧት ጆቢራ በከተማህ ስታቅራራ በዕድሜህ መንከራተት ሥራ ካንዱ ቢሮ ሌላው ቢሮ አቦል በረካውን ብለህ ያገሩን ወሬ ተንትነህ ተጨቃጭቀህ ተለፋልፈህ አመሳጥረህ አቆላልፈህ የዚያን ጉዳይ ከዚህ ጉዳይ ዘጋግነህ በቡና ምዝ አምተህ ደክመህ ስተለያይ በዚህ ብቻ ሳታስቀረው ደሞ አዲሱን የአዝዢ ጠባይ ከልማድ የቡና ሱስ ጋር የዘመኑን ሳትለያይ እስቲ ደሞ አራዳ ወጥተህ በክተማው አደባባይ ያንዷን ካንዷ ዳሌና ባት እግሯን ከአግር ጋር አስተያይ። ቢልህ ፈጥጦ በግልምጫ ስኅሲናህ ማጋለጫ ናቀው እርግፍ አርገህ ተወው ቴህ ብጤው ጋር አትንጫጫ።
ቃል እውነት ነውና። ቃል ሕይወት ነውና። ያቺ ዓድዋ ሕይወት ቢራ ቢሮ መሸ ደሞ አምባ ልውጣ። ደባርቅ ሀድ መርካቶ ን ጉለሌ ሀ ቆቃ ሁሱቃ እንዳሥላሴ ቀበና ሊበን ዓድዋ ሰድሰት ኪሎ ፅ ቢሾፍቱ እዲባባ ሚኩ እከካም ተማሪ ለእንዲት የቅኔምሽት ረሃብ ሰንት ቀን ይፈጃል። ይኸ ይሆን አሰቀድሞ ቃል። ያንቺሳ ምሥጢር ምንድነው ቢራ ቢሮ እንወያይ አንቺ የዕፀዋት አዋዋይ ከፀደይ ጋር ፀደይ መሳይ ከአበባም አበባ መሳይ ምን አለበት ላንዲት ሰሞን ቢራ ቢሮ እኔ አንቺን ብሆን በፍስሃሽ ብጥለቀለቅ ብነግሥባት ባንቺ ጽዮን። እና እምታውቁት ንገሩን እውነት ራብ ሰንት ቀን ይፈጃል። ስንት ያዘልቃልገ እውነት ራብ ስንት ቀን ይፈጃል። ጥቅምት ፒያሳ አዋሽ እስከመቼ ይሆን አዋሽን። እስከመቼ ይሆን አዋሽ። እሰከመቼ ይሆን አዋሽ። አዋሸ አባ ሮሮ ቅርሱ የዘለዓለም ንዳድ ጉርሱ አዋሽ ቡቡ በረኸኛ የአረህ ሸለቆ በረኛ የአሸዋ ዋሻ መተኛ የበረሀ ዋነተኛ የምድረ በዳ ብቸኛ የዘለዓለም መንገደኛ የአበቅቴ መወራረሻ የዕፀዋት ዕድሜ መቁጠሪያ በፀደይ የአልባሳት ማዕጠንት የዘመን ላቦት ወዝ ማጥሪያ የእንቁጣጣሽ ማዳበሪያ የአዝርእት ሰብል ማጥለያ በክረምት የዶፍ ረከቦት የሰማይ ምጥ መቀበያ የደመና እምባ ማጠቢያ የማዕበል ሰደድ ማከያ የተራሮችን ለቅሶ ቻይ የጅረት የምንጮች አዋይ ጭምት መሳይ ያለዐመሉ ዘራፍ ባይ በመስክ ሙሉ አባ ጭራቅአክናፍ ቀንዶ አዋሽ ዘጠኝ ራሳ ዘንዶ ቁልቁል እንደምሽት ጥላ ከሰማየ ሰማይ ወርዶ ሞልቶ ተንደላቆ ኮርቶ የሰንት ዓለም ምድር ጐርዶ ቀይ ደመና ተክናንቦ ጋራ እንደአሻንጉሊት አዝሎ ስንቱን በረት እንደጉድፍ አውተፍትፎ አንጠልጥሎ አውድማውን አንገዋልሎ ወርካውን ግቻ አሳክሎ አመንምኖ አስልሎ እንደዘጠኝ በገና አውታር በየረድፉ ተሰድሮ በአገር ምድር ዙሪያ ጥምጥም እንደመቀነት ተቋጥሮ አዋሽ ቁጣ አባ ዱታ የሰማይ ጥጉ ቱማታ አዋሽ አባ ሻኛው ጋራ ኩሩ እንደነማታ ሐራ የግርማ ሞገስ መርገፉ እስከነምድረአቀፍ ዘርፉ አባ ገርስስ ሞልቶ ደራሽ አባ አደፍርስ አባ ኩርፋድ ከተፍ እንደመብረቅ ግማድ በምድር ቁና ድንገት ሲጣድ አዋሽ ንፉግ አባ መዓት የገጠሬ አታምጣ ምጣት አዋሽ ደርሶቀማውመብረቅ አባ መዝረፍመውሰድመንጠቅ ግሣንግሱን አግበባስብሶ በምድረ በዳ ለማጨቅ ህሩር ጉረሮ ለማመቅ የአሸዋ ሆድ ለመጠቅጠቅ ህራም ብሎ አብሮ ስመጥለቅ እምድረ ከርስ መቀመቅ እስከመቼ ይሆን አዋሽ። አዋሽ አባ ሮሮ አገሩ ያሸዋ ማኅፀን ድንበሩ የምድረ ዓለም ኬላ በሩ ኩሩ ብሶት እንደልቡ ቅምጥል የሸዋ ቡቡ የሰማይ አድማስ ግድቡ ንዳድ ስንቁ አረህ ግቡ እስከ መቼ ይሆን አዋሽ። ታድያ እስከመቼ ነው አዋሽ። አዋሽ የመጫ ሥር ፍሳሽ የሸዋ የእምብርትሸ ላቦት የምንጮችሽ የምጥ አማጭ የአለትሸ የተራሮችሽ የጉልጥምጥሚትቭሸ ፍላጭ እስክመቼ ይሆን አዋሽ ወዝክን አሸዋ እሚውጥህ። እስክመቼ ይሆን አዋሽ ተስፋ መቁረጥን እማታውቅ። እስክመቼ ይሆን አዋሽገ መቸም ሌላ ንግርት የለህ እንደ ሴቴ ሸረሪት ፅንስ ራስክን በራስህ ዋጥ ያለህ እስከመቼ ይሆን አዋሽ።