Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
እላይ እንደተመለከትነው የእስክ ንድርያና መሰሎቿ የተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት የተካሄደ ከኬልቁዶን ጉባኤ በኋላ የመጀመሪያው መሆኑ ነው ።
ክፍል ሁለት የኦርየንታል የተዋሕዶ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ ምዕራፍ የእስክንድርያ የግብጽ የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደምንመለከተው የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ በሆኑ በቢዛንታይን በቱስጥንጥንያ ነገሥታትና የእስልምና እምነት ተከታይ በሆኑ ቅኝ ገዥዎች ቀንበር ሥር ለብዙ ዘመናት በመማቀቋ ምክንያት የምእመናኖቿ ቀጥር በጣም ተቀንሶና አንሶ የምትገኘው የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን በ ዓም እስከተደረገችው እስከ ኬልቄዶን ጉባኤ ድረስ ከሌሎች የዓለም አብያተ ክርስቲያናት በይበልጥ ለክርስትና መጠናከርና መስፋፋት ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አድርጋለች ። ይህም ቤተ ክርስቲያን በአቡነ ክርስቶዱሎስ ፓትርያርክነት ዘመን በ ዓም የእስክንድርያ መንበረ ፓትርያርክ ወደ ካይሮ እስከተዛወረበት ጊዜ ድረስ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ሆኖ ኖሯል ። በዚህ አኳኋን ወንጌላዊው ማርቆስ በቅዱስ ጴጥሮስ በመሾም የእስክንድርያን ቤተ ክርስቲያን መሥርቶና የመጀመሪያው ፓትርያርክ ሆኖ በትጋት ሲያገለግል ከቄየ በኋላ በ ዓም በሰማዕትነት ዐረፈ ። በዘጠንኛው መቶ ዘመን የቬኑስ ነጋዴዎች የቅዱስ ማርቆስን አጽም ሰርቀው ወስደው ቬኑስ በሚገኘው በማርቆስ ካቴድራል ውስጥ አስቀምጠ ውት ሲኖር በእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ መሠረት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ ፖፕ ጳውሎስ ኛ ለእስክንድርያው የኮፕት ፓትርያርክ ለአቡነ ቄርሎስ ኛ እንዲሰጥ አደረገ ። የእስክንድርያ ትምህርት ቤት ለክርስቲያኑ ዓለም እስከ አምስተ ኛው መቶ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ድረስ መንፈሳዊ ትምህርትን በስፋትና በጥልቀት ስትሰጥ ከቂየች በኋላ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ለመጀመሪያ ጊዜ በእምነት ምክንያት ለሁለት ከተከፈሉበት ከኬልቄዶን ጉባኤ ጀምሮ እየተዳከመች ሄደች። ሆኖም ከ ዓም ጀምሮ የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ትሪፖሊና ቤንጋዚ ውስጥ ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ከፍታ እዚያ ለሚኖሩ ጥቂት ምእመናኖቿ መንፈሳዊ አገልግሎትን ታበረክታለች ። በኬልቄዶን ጉባኤ ከተደረገው መለያየት በኋላ በቀሩስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያንና በንጉሥ የሚደገፉት የሁለት ባሕርይን እምነት ተቀብለው እስክንድርያ የሚኖሩት መለካውያን የቢዛንታይን ንጉሥ ታማኝ ደጋፊዎች የተባሉት ክርስቲያኖች በኮፕት ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ተጽእኖ ያደርጉ ነበር ። ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መልእክተኞቿን ልካ በኬልቄዶን ጉባኤ ላይ ባትካፈልም በቅዱስ ዲዮስቆሮስ የተወከለችው የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን የምትቀበለውን ቀጥትኛውን የተዋሕዶ እምነት ተቀብላ በተግባር ላይ አውላለች ። ምንም እንኳ የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን የወንጌል መልእክተኞ ቿን በቀጥታ ልካ አውሮጳ ውስጥ ባታስተምርም ቅሉ የእስክንድርያው ፓትርያርክ ቅዱስ አትናቴዎስ በአርዮሳውያን ተጽእኖ በደረሰበት በሁለ ተኛው የስደቱ ወቅት ወደ ሮም ተሰዶ ከ እስከ ዓም ድረስ ከሮሙ ፖግን ቀዳማዊ ጁልዮስ ዘንድ በእንግድነት በፄየበት ወቅት እንዲሁም ፈረንሳይ በምትገኝ ትሬቪን ከተባለች ከተማ በሰነበተበት ጊዜ በእነ አባ እንጦንስ አሞንዮስ መቃርስ ጳኩሚስ ወዘተ ግብጽ ውስጥ የተመሠረተውን የብሕትውና የምነና ኑሮ ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችና አባላት አስረድቷል ። ይኸው ግብጽ ውስጥ በአባ እንጦንስ የተጀመረው የብሕትውና ኑሮ የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ለመላው የክርስቲያኑ ዓለም ያበረከተችው መንፈሳዊ ሥጦታ በረከት ነው ። እንዲሁም አባ ሺኖዳ የእስክንድርያውን ፓትርያርክ ቅዱስ ቄርሎስን በመከተል በ ዓም ኤፌሶን ውስጥ በተደረገችዋ በሦስተኛዋ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ላይ ተካፍሎ የንስጥሮስን የኑፋቄ ትምህርት ተቃውሟል። በ ዓም በተደረገችው በኬልቄዶን ጉባኤ የእስክንድርያ የኮ ፕት ቤተ ክርስቲያን የካቶሊክንና የግሪክ ኦርቶዶክስን አብያተ ክርስቲያ ናት አውግዛ ከለየች በኋላ በግብጽ ገዳማት ውስጥ የብሕትውና ኑሮ ከዓለማቀፋዊነት ወደ ብሔራዊነት ጠባብ ብሔርተኝነት እየተለወጠ ሄደ። እንዲሁም በሃያኛው መቶ ዘመን ይፋ ኦፊሴል ባልሆነ መንገድ ያደረጉአቸው ግንኙነቶች በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደምንመለከተው በዓለም አብያተ ክርስቲያናት አባቶች ጳጳሳት ኅብረት ከፍተኛ የሆኑ የመሠረተ ሃይማ ናት ትምህርቶች በቅዱሳት መጸሕፍት መሠረትነት በጉባኤ የተወሰኑባ ቸው መናፍቃን የተወገዙባቸው በመጨረሻም አንድ የነበረችቱ ቤተ ክርስቲያን በእምነትና በፖለቲካ በማዕርግ ነክ ምክንያቶች በአሳዛኝ ሁኔታ እርስ በእርዷቧ ተወጋግዛ በሁለት ጎራ የተከፋፈለችበት ወቅት ከ እስከ ዓም ድረስ በነበረው ጊዜ ነው። ይህ ዓይነቱ የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች የፈጸሙት የተሳካ የመሪነት ተግባርና በመንፈሳዊ ትምህርትም የእስክንድርያ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት ካህናት ያበረከተ ችው ታላቅ አስተዋጽኦ የግሪክ ኦርቶዶክስንና የካቶሊክን አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ስላላስደሰተ ስላስቀና በአራተኛው የኬልቄዶን ጉባኤ ከቢዛንታይን ንጉሥ ከመርቅያን ጋር በመመሳጠር የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በመንግስት ድጋፍ በእስክንድርያው ፓትርያርክ በቅዱስ ዲዮስቆሮስ ላይ በግፍ ተነሥተው አሠቃይተው ገደሉት። የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያንም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ባሕርያት አሉት በማለት የሚያምኑትን ሁለቱን አብያተ ክርስቲያናት አውግዛ ለየቻቸው። የቢዛንታይን ንጉሥ ሙሉ ድጋፍ በነበራቸው በኬልቄዶን ጉባኤ ተካፋዮች ሕገወጥ ውሳኔ መሠረት ቅዱስ ዲዮስቆሮስ በስደት በደሴተ ጋንግራ ተሠቃይቶ ከሞተ በኋላ የቢዛንታይን መንግሥት ደጋፊና በተፈጥሮው ፈሪና ድንጉጽ የነበረው አቡነ ፕሮቴሪዮስ ያለ ኮፕት ካህናት ፈቃድ በንጉውሠና በሩስጥንጥንያ ቤተ ክርስቲያን ትእዛዝ ተጽእኖ የእስክንድርያ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ። በሌላው ወገን ደግሞ የኬልቄዶን ጉባኤ እምነት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ባሻገር ፖለቲካ ነክ ለሆኑ ጥቅሞችም ማስከበሪያ ሆን ተብሎ የታቀደ ስለነበር በኒቅያ ጉባኤ በስድስተኛው አንቀጽ የአብያተ ክርስቲያናቱ መሪዎች የማዕርግ ተራ የሮም የእስክንድርያ የአንጾኪያ የኢየሩሳሌም የኤፌሶን የነበረው በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችና በንጉሠ በመርቅያን ተጽእኖ ተሽሮ በኬልቄዶን ጉባኤ ጸድቆ በወጣው በሃያ ስምንተኛው ሕግ ላይ መናገሻ ከተማ ለሆነችው ለቶፉስጥንጥንያ ለአዲሲቱ ሮም ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የአንደኛነቱን ማፅርግ በመስጠት ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፖፕ ጋር አስተካክሎታል። ምንም እንኳ ሁለቱ ወገኖች በኬልቄዶን ጉባኤ ከተወጋገዙ በኋላ ለአያሌ ዘመናት የጎሪጥ እየተያዩ ቢኖሩም አምስቱ የኦርየንታል ኦርቶዶ ክስ አብያተ ክርስቲያናትና የግሪክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ካህናት ከ ዓም ጀምሮ አባላት በሆኑበት በዓለም አብያተ ክርስተያ ናት ንቅናቄ የመቀራረብ የመተባበር መርሆ መሠረት በ ዓም ዴንማርክበ ዓም ኢንግላንድ በ ዓም ስዊዘርላንድ በ ዓ ም ኢትዮጵያ ውስጥ ይፋ ኦፊሴል ባልሆነ መንገድ እየተሰበሰቡ በመወያየት ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት በሚቀራረቡበት ሁኔታ ላይ ተነጋግረዋል። ሸ የኬልቄዶንን ጉባኤ ውሳኔ አንቀበልም ያሉትን የኮፕትን የግብጽን ካህናትና ምእመናንን በማስገደድ ወደ ሁለት ባሕርይ የኑፋቄ እምነት ለመመለስ የተሳነው የቢዛንታይን መንግሥትበሚከተሉት ለስለስ ባሉ የዕርቅ ሰነዶች ፎርሙላ ዎች አማካይነት ሁለቱን አብያተ ክርስቲያናት በእምነት አንድ ለማድረግ ሞክሮ ሳይሳካለት መቅረቱ በግሪክ ኦርቶዶክስና በኦርየንታል በተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ዕርቅና ሰላምን አስፍኖ በሰላም ለመግዛት እንዲያመች በቢዛንታይን ነገሥታት ጉትጎታ በተደጋጋሚ ተሞክሮ ሳይሳካ የቀረው ሄኖቲኮን እንደገና አንድ የሚያደርግ ሰነድ የተባለው ንቅናቄ። ይኸው ጨካኙና ምሕረተቢሱ አቡነ ሲሩስም ወደ እስክንድርያ ተጉዞ በ ዓም ከደረሰ በኋላ በመንግሥት ሹማምንት በመለካውያን ካህናትና ምእመናን በመደገፍ በሰነዱ የሰፈረውን ተቀብለው ከመለካውያን ጋር አንድ እንዲሆኑ ኮፕቶችን ቢጠይቃቸው ክርስቶስ ሰው የሆነ አምላክ በመሆኑ መለኮሱጵና ትስብእት ያለመለየት ያለመቀላቀል ያለመለወጥ ስለተዋሐዱ አንድ አካል አንድ ባሕርይ አንድ ፈቃድ አንድ ግብር መሆኑን በምናምነው መሠረት አሁን ለክርስቶስ አንድ ፈቃድ አለው የሚለው ሰነድ ከመጀመሪያ ጀምሮ የተቀበልነው እምነት ቢሆንም ቅሉ ለሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መለያየት ዋነኛ ምክንያት የሆነው ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ አለው የሚለው ኑፋቄ እስከ አልተወገዘ ድረስ ከቀጥተኛው የተዋሕዶ እምነታችን ዝንፍ አንልም ስላሉት ለዐሥር ዓመታት ያህል የኮፕቶችን ካህናትና ምእመናን በመግረፍ በማሰር በመግደል ወዘተ ከፍ ያለ አሰቃቂ ሥቃይ ፈጸመባቸው ። ይኽውም ከተለያዩ የግሪክ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የተወከሉ ካህናት እንዲሁም ከእስክንድርያ ቤተ ክርስቲ ያን የቅዱስ እንጦንስ ገዳም አበምኔት አባ ዮሐንስና ኢየሩሳሌም ካለው የኢትዮጵያ ገዳም ኢትዮጵያዊው አባ ጴጥሮስ ተወክለው በጉባኤው ላይ በመገኘት ውይይቱ ተጀምሮ ሦስቱንም አብያተ ክርስቲያናት ከሮሙ ፖፕ ሥር ለማድረግ ከእስላሞች ወረራ እናድናችኋለን በሚል ሽፋን የታቀደ ደባ ስለነበር ግቡን ሳይመታ ቀረ ። በ በአቡነ ቄርሎስ ኛና በአቡነ ቄርሎስ ኛ የፓትርያርክነት ዘመን ከዚያም በኋላ በኮፕት ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ዘንድ የተከሰተው መሻሻል ተሐድሶ በኮፕቶች ዘንድ የተሐድሶ አባት በመባል የሚታወቀው ቄርሎስ ኛ የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ እንደሆነ ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የተነሣው ትምህርትን ማስፋፋት ማሰራጨት ስለነበረ በግብጽ ካህናት ዘንድ ሰፍኖ የነበረውን የትምህርት ጉድለት ዝቅተኛነት ለማሻሻል ካህናት ተግተው እንዲማሩ አደረገ ። ቀደም ሲል እንደተመለከትነው ከኬልቄዶን ጉባኤ ጀምሮ የተዋ ሕዶ እምነት ተከታይ ካልሆኑት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት እራሷን አግልላ ስትኖር በእኩልነት መንፈስ እርስ በእርስ ለመረዳዳትና ክርስት ናን ለማጠናከር በሃያኛው መቶ ዘመን ለተጀመረው ለዓለም አብያተ ክርስቲያናት ንቅናቄ ጉባኤ ማኅበር እንደ ሌሎች የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት አባል በመሆን በየጊዜው በሚደረጉት ጉባኤዎች በመካፈል የተቻላትን አስተዋጽኦ ታደርጋለች ። እንዲሁም አዲስ አበባ ውስጥ እንደ ኢትዮጵያ አፄቄጣጠር በ ዓም በተደረገው የኦርየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ ላይ የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ተካፍላለች ።