Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
አዎን የፊቱና የድምፁ ሁኔታ ከመቅፅበት ተለወጠና ክፍሉን እንደገና ዙሪያውን ቃኘ ከልብስ ሰፊው ነው የተከራየሽው። ህሌም በአንድ ክፍል ውስጥ ነው የሚኖሩት። አዎን ከመሸቭ ወዲያ ወደዚህ መምጣት ያስፈራኛል አላት እየተከዘ ሶንያ አሁንም መረጋጋት አቾቷት በጣም ጥሩሰዎች ናቸው የቤት እቃውም የእነርሱ ነው ልጆቻቸው በየጊዜው እየመጡ ይጠይቁኛልስትል መለሰች መናገር የተሳናቸውን ማለትሽ ነው።ስትል ተናገረች ሶንያ እጆቿን አጣጥፋ ተስፋ በቆረጠ አንደበት ይሂን ስትናገር ገርጥቶ የነበረው ፊቷ እንደገና ፍም መሰለ አይኗ ቦዘ በሰውየው ንግግር በጣም እንደተቀየመች ስሜቷን በቃላት መግለፅ እንደፈለገችና ከሚስስ ማርሜሳዶቭ ጎን እንደቆመች በገሀድ ይታይ ነበር ። ያልተወጣቸው ስሜት በፊቷ ላይ ተነበበ እንዴት ትመታሽ ነበር ትለኛለህ። ዛሬ እንዴት ነው ያለቀሰችው። በዛሬው እለት ያበቃለት ጉዳይ መሆኑን ለመቀበል ተገደደ ለማመን የሚያስቸግር ድርጊት ተፈፀመ ክብሩን የቀነሰበት ጥቁር እባብ ሌሊቱን ሙሉ ሲበላው አደረፁ ሚስተር ሉዚን ያዳምጥ እንጂ ልቡ ሌላ ቦታ ነበር።
የሚል የደነገጠች ሴት ድምፅ ተሰማ እኔ ነኝ ልጠይቅሽ ነው የመጣሁት ሲል ራስኮልኒኮቭ መልስ ሰጠና ጠባብ ወደሆነችው ኮሪዶር ዘለቀ ከተሰበረ ወንበር ላይ ከሚገኘው ከመዳብ ከተሠራ የሻፃ ማስቀመጫ ላይ የሻማ ብርሀን ጭልጭል ይሳል ሶንያ እንደቆመች ክው ብላ አንተ ነህ እንዴ። ሲል ፊቷን ሳይመለከት ጠየቃት ሕይወቷን የሚወስን ነገር የገጠማት ይመስል አዎን ቤት ያከራየችኝ ሴት ሰአት ገና አሁን እንደደወለ ሰምቼአለሁ አምስት ሰአት ሆኗል እያለች አጉረመረመች ራስኮልኒኮቭ ለመምጣት የመጀመሪያው ጊዜ ቢሆንም ልጠይቅሽ የመጣሁት ለመጨረሻ ጊዜ ነው ምናልባትም እስከ መቼውም ላንገናኝ እንችላለን አለ ፊቱን ጨፍገገፃ አድርጎ ወደውጭ መሄድህ ነው እንዴ። ብላ ጠየቀችው ራስኮልኒኮቭ በመገረም ተመለከታት ርካሽ ስራዋ የቱን ያህል ልቧን እንዳደማው ተረዳ ከዚህ ስራዋ እንዳትገላገል አንቆ የያዛት ምን እንደሆን አሰላሰለ እነዚያ የሙት ልጆች በሳንባ ነቀርሳ የምትሰቃየውና በተበሳጨች ቁጥር ግድግዳውን በጭንቅላቷ የምትላተመው ምስኪኗና ቀውሷ ሚስስ ማርሜላዶቭ ለእርሷ ያላቸውን ትርጉም የተረዳው ገና አሁን ነው ከጠባይዋና ካላት አነስተኛ የትምህርት ደረጃ አንፃር ሶንያ በእንዲህ አይነቱ ኑሮ ልትገፋበት እንደማትችል ተረዳ ባህር ገብታ ለመገላገል ድፍረቱ ከሌሳት በሕብረተሰቡ ውስጥ እንዲህ አይነት ቦታ መያዚ የአጋጣሚ ጉዳይ ነው ብሎ ገመተ የቀሰመችው ትምህርት ውሱን ባይሆንና የእስካሁን ድረስ ሕይወቷ ተፅእኖ ባያሳድርባት ኖሮ ይሄን አይነቱን አስከፊ የሕይወት ጎዳና ለመዝለቅ አንድ እርምጃ ከመጓዝ ይልቅ ራሷን በገደለች ነበር ይሄን አይነቱን ሕይወት እንድትገፋበት ያደረጋት ምንድነው። ሶንያ መፅሐፉን ገልጣ ቦታውን አገኘኝች እጆቿ እየተንቀጠቀጡ አንደበቷ ከዳት የመጀመሪያውን ፊደል ለማውጣት እየተሳናት ለሁለት ጊዜ የማንበብ ሙከራ አደረገች አላዛር የተባለ ሰው ታሞ ነበር ብላ በስንት ጭንቀት ከተናገረች በኋላ ያለቅጥ ተወጥሮ እንደተበጠሰ ሲባጎ ድምጺ ተቋረጠ መተንፈስ አቅቷት ልቧ ተጨማደደ እየቆየች ግን አንደበቷን የዘጋውን ፍርሀት ተቋቋመችና ማንበቡን ቀጠለች አንብባ እንደጨረሰችም መፅሐፉን ዘግታ በአፋጣኝ ከመቀመጫዋ ተነሳች ስለአላዛር ከሞት መነሳት የተባለው ሁሉ ይህ ነው እያለች በድንገት ተናገረችና ፊቷን ከእርሱ መልሳ ደርቃ ስትቆም ቁራጩ ሻማ በተጣመመው የሻማ ማስቀመጫ ውስጥ ሆኖ ጭልጭል እያለ ነፍሰ ገዳይና ሴትኛ አዳሪ ላሉበት የተራቆተ ክፍል ደብዛዛ ብርሀን ማዳረሱን ቀጠለ በሁለቱ መካከል ከአምስት ደቂቃ በሳይ ዝምታ ሰፈነ ራስኮልኒኮቭ ብስጭት ባልተለየው ሁኔታ ጎላ አድርጎ የመጣሁት ስለአንድ ጉዳይ ለመወያየት ነውአለና ተነስቶ ወደሶንያ ሄደ በዝምታ ተውጣ አንገቷን ቀና አደረገች አረመኔያዊ ቆራጥነት በተንፀባረቀበት ሁኔታ በቁጣ ተመለከታት እናቴንና እህቴን ከእነአካቴው ስለተውካኳቸው ከእንግዲህ ወዲህ ወደእነርሱ ጭራሽ አልሄድም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሊያይተናልአላት ሶንያ እየተገረመች ለምን። ብላ ጠየቀችው ለምን ትያለሽ እንዴ። አለች ሶንያ ሌሊቱን በቅዥት አለም ስትዘል ስታለቅስ እጆቿን ስታወራጭ ስለፖልያስለሚስስ ማርሜሳዶቭ ስለሊሳቬታ ፊቱ እንደበረዶ ነጥቶና አይኖቹ ፈጠው ስላደረገችው የመፅሐፍ ቅዱስ ንባብ ስታልም አሳለፈች በቀኝ በኩል ተቆልፎ የነበረውን በር አልፎ የሚከራይ ቤት ስለነበር ሶንያ ክፍሉ እንዳልተያዘ አድርጋ ቆጥራለች ይሁንና ያንን ሁሉ ጨዋታ ሚስተር ስቪድሪጋሉቭ ከዋናው ክፍል በር ላይ እንደአይጥ አድፍጦ ቆሞ ይሰማ ነበር ራስኮልኒኮቭ ወጥቶ እንደሄደም ትንሽ ከአሰላሰለ በኋላ በሶምሶማ አካሄድ ወደ ክፍሉ አምርቶ ወንበር አመጣና ወደሶንያ ክፍል ከሚያገናኘው በር አጠገብ አስቀመጠ የሁለቱ ጨዋታ በጣም አስደስቶት ነበር ወንበር አምጥቶ ከበሩ አጠገብ ያስቀመጠውም ወደፊት ምናልባትም ነኸ አንድ ሰአት ሙሉ በእግሩ ቆሞ ከመቸገር ከወንበሩ ላይ አረፍ ብሎ በሶንያ ክፍል የሚሰማውን ውይይት ተዝናንቶ ለመኮምኮም ነው በማግስቱ ከረፋዱ አምስት ሰአት ላይ ራስኮልኒኮቭ ወደፖሊስ ጣቢያው ምርመራ ክፍል አምርቶ መምጣቱን ለፖርፊሪ እንዲነግሩለት በጠየቃቸው ጊዜ ለአስር ደቂቃ ያህል እንዲጠብቅ መደረጉ አስደነቀው ወዲያውኑ አፈፍ የሚያደርጉት መስሎት ነበር እርሱን የማያስተውሉ ሰዎች ሲወጡና ሲዝቡ ከእንግዳ መቀበያው ክፍል ቆሞ ነበር ቢሮ ከሚመስለው ከሚቀጥለው ክፍል ስለ ራስኮልኒኮቭ ማንነት ደንታ ያልነበራቸው ጥቂት ሠራተኞች የፅሀፈት ስራቸውን ተያይዘውታል። ከዚህ በመነሳት ሰውየው ለፖሊስ ምንም ነገር አሳሳወቀም ወይም ደግሞ የሚያውቀውና ያየው ምንም ነገር የለም ብሎ ገመተ ትናንት የገጠመው ሁሉ በሕመሙና በመሸበሩ የተነሳ የተጋነነ ሕልም እንጂ ሌሳ እንዳልሆነ ተገዘበ ሁኔታውን በጥልቀት በሚገመግምበትና ለአዲሱ ፍልሚያ ራሱን በሚያዘጋጅበት በአሁኑ ወቅት ብርክ ስለያዘው ለዚህ ደረጃ ያበቃው በአስቀያሚው ፖርፊሪ ላይ ያደረበት ጥሳቻ መሆኑን ተረዳና ተበሳጩ ከሁሉም በላይ ያስፈራው ያን ሰው እንደገና መገናኘቱ ነበር ከልክ በላይ ስለሚጠላው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ራሱን እንዳያጋልጥ ስጋት አደረበት ሆኖም ብስጭቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ፍርሀቱ ወዲያውኑ ተወገደለት ተዝናንቶ ወደ ፖርፊሪ ቢሮ ለመግባት በተቻለ መጠን ጥቂት ለመናገር ፖርፊሪን በጥልቀት ለመገምገምና በጥንቃቄ ለመስማት ብሎም መሸበሩን ትቶ አደብ ለመግዛት ቆረጠ በዚያን ቅፅበት ወደፖርፊሪ ቢሮ ተጠራ ፖርፊሪ ከቢሮው ብቻውን የተቀመጠ ይመስላል ቢሮው ትልቅም ትንሽም የማይባል ነው በአሜሪካ ጨርቅ ከተሸፈነ ፎቴ ፊት ለፊት ትልቅ የፅህፈት ጠረጴዛ ቆሟል ከተላገ እንጨት የተሰሩ መደርደሪያዎችና ጥቂት ወንበሮች ይታያሉ ከጀርባ በኩል ካለው ግድግዳ ጥግ የተዘጋ በር ስላለ ሌሎች ክፍሎች መኖር አለባቸው ራስኮልኒኮቭ ወደቢሮው እንደገባ ብቻቸውን እንዲሆኑ በማሰብ ፖርፊሪ የቢሮውን በር ዘጋና በጥሩ የወዳጅነት ስሜትና በትህትና ተቀበለው ወደእኛ አለም መጥተሀል መድፈር አይሁንብኝና ወዳጄ ተቀመጥ የእኔ ጌታ ከፎቴው ላይ ተቀመጥ አለው ። አለው ለጥቂት ጊዜ ፊቱ ከደስታ ብዛት አበራና የተቋጠረው ግንባሩ ተፈታ አይኖቹ አናነሱ ፊቱ አባበጠና ከመላው ሰውነቱ ጋር አብሮ እየሳቀ ራስኮልኒኮቭን በቀጥታ ተመለከተው ራስኮልኒኮቭ ራሱን አስገድዶም ቢሆን መሳቅ ጀመረ ፖርፊሪ ራስኮልኒኮቭ መሳቁን እንደተመለከተ ከአንጀቱ ተንፈቀፈቀና ፊቱ ፍም መሰለ ራስኮልኒኮቭ ግን በጣም ስለበሸቀ የፈለገው ይምጣ በማለት ሳቁን አቆመ ፖርፊሪ ሆን ብሎ በሳቅ ሲንከተከት በግልዕ በሜታይ የጥላቻ አይን ትክ ብሎ ተመለከተው ይሁንና በሁለቱም ዘንድ ግዴለሽነት ሰፈነና ፖርፊሪ ቢስቅም እንኳን በራስኮልኒኮቭ የአፀፋ እርምጃ የተነሳ ግራ የተጋባ መሰለ ራስኮልኒኮቭ ደግሞ ቀደም ሲል መርማሪው ግራ አለመጋባቱን አስታውሶ ምናልባትም እርሱ ራሱ ወጥመድ ውስጥ መግባቱን ተገነዘበ ከዚህ ሁሉ ጀርባ የማያውቀው አንድ ጉዳይ እንዳለና ሁሉም ነገር ቀደም ብሎ ስለተወጠነ ሳይታሰብ በሆነ ቀን እንደገለጥ ገመተ። ካለ በኋላ በክፍሉ ውስጥ ወዲያና ወዲህ እየተዘዋወረ ወይም ራስኮልኒኮቭ እንዲቀመጥ እየሞከረ እንዲህ ሲል ተናገረ ይሄ ሁሉ ፍሬከርስኪ ነው ገና ብዙ ጊዜ አለን። መሙመሙ ይቀጥሳል ይህን ሁኔታ ራስኮልኒኮቭ ያስተዋለው ፖርፊሪ ከክፍሉ ሊወጣ ከተንደረደረ በኋላ የሆነ ነገር የሰማ ይመስል ከበሩ አጠገብ ለአንድ ሰኮንድ በቆመበት ጊዜ ነበር የደጨሂጠብቀው ነገር ይኖር ይሆን። አንተም ትክክል ነህ ይሄ ሁሉ በተለይም የጦርነቱ ጉዳይ አልፎ አልፎ የሚያጋጥም መሆኑን እቀበላለሁ ይሁንና ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር አንድ ወንጀል ገና እንደተፈፀመ የተለየና ብዙውን ጊዜም ቀደም ሲል ከተፈፀመው ጋር የማይመሳሰል ሆኖ ስለሚገኝ በመፃሕፍት ላይ የምናነባቸው የሕግ ደንቦችና ስልቶች አግባብነት ያጣሌ የሚገርሙ ብዙ ሁኔታዎች አጋጥመውኛል አንድን ተጠርጣሪ አስሮ ከማስቀመጥ ይልቅ ስጋት አድሮበት ያለማቋረጥ እንዲሸበር ባደርገው እርሱ ራሱ ግራ ግብት ይለውና ሳይወድ በግዱ ወደእኔ ይመጣል እንደእኛ አይነቱ የተማረው ቀርቶ ያልተማረው ዝሬም ቢሆን እንኳን ይሄን ያደርጋል ወዳጄ ልቤ በሰው አእምሮ ውስጥ ያሉትን አዝማሚያዎች ማወቁ በጣም አቢይ ጉዳይ ነው የነርሾቹን ሁኔታ የዘነጋህ ትመስላለህ ምክንያቱም በዛሬ ጊዜ ሁሉም ሰው የታመመ በአጉል አስተሳሰብ የተጠመደና የሚቅበጠበጥ ሆኖ ስለሚታይ ነው ይህ አይነቱ ሰው የቱን ያህል ጥሳቻ እንዳለበት እስቲ ተገንዘበው አንድ ተጠርጣሪ እንደ ነፃ ሰው በከተማው ቢዘዋወር ምን ጨነቀኝ። እያለ ለራሱ አሰላሰለ ለሚመጣው ሁሉ ነገር ወኔው እንዳይከዳው አደረገ አንዳንዴማ ፖርፊሪን ዘለህ እነቀው የሚል ስሜት ይመጣበት ነበር ገና ወደ ፖርፊሪ ቢሮ እንደገባ የጥሳቻ ስሜቱ እንዳይቀሰቀስ ሰግቶ ነበርና ከንፈሩ እንደደረቀና የልብ ትርታው እንደጨመረ ተሰምቶታል እንዲያም ሆኖ ግን ትክክለኛው ወቅት እስኪመጣ ድረስ ሳለመናገር ወሰነ በአሁኑ ሁኔታ ዝም ማለቱ ከመሳሳት የሚያድነው ብቻ ሳይሆን ጠላቱን አበሳጭቶ መናገር የማይፈልገውን ሁሉ የሚያስቀባጥረው መሆኑን ተገነዘበ ፖርፊሪ እየተዝናና እየሳቀ በክፍሉ ውስጥ በመንጎራደድ ንግግሩን ቀጠለ እንደማታምነኝ ይገባኛል ዝምብዬ የምቀልድ ይመስልህል ሊመስልህም ይገበል እግዚአብሔር የሰጠኝ ቸርነት በሰዎች ዘንድ ሌላ ነገር ሳይሆን አስቂኝ ሀሳቦችን ብቻ ለመፈንጠቅ የሚያስችል ነው የምገርም ሰው ነኝ ወዳጄ ልቤ አንድ ነጥብ በተደጋጋሚ ላውሳልህ እንደእኔ አይነት አስገራሚ ሽማግሌ እንዳንተ አይነቱን ወጣት በግልፅ ሲያነጋግር እንደማትቀየም ተስፋ አደርጋለሁ እንደማንኛውም ወጣት ለሰብአዊ አእምሮ ከፍተኛ ግምት የምትሰጠውም በዚሀ የተነሳ ነው አግባብ ያለው ቀልድና ሎጂክ የሚያስገኙት ውጤት የሚደነቅ ነው ስለወታደራዊ ጉዳዮች እስከማውቀው ድረስ የአውስትሪያን የጦር ምክር ቤት ነ መጥቀስ ይቻላል አየህ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ናፖሊዮንን አሸንፈው እስረኛ አድርገው ወስደውታል። እያለ ፖርፊሪ በቁጣ ድምፅ ጠየቀ ወዲያውኑ መልስ ባያገኝም ከበሩ በስተጀርባ አያሌ ሰዎች መኖራቸውና ከመካከላቸው አንደኛውን ወደበሩ እንዳይጠጋ አየገፈተሩት እንደሆነ ግልዕ ነበር ምንድነው ጉዳዩ። ሲል ለሁለተኛ ጊዜ ፖርፊሪ በጉጉት ጠየቀ እስረኛውን ኒኮላይን አምጥተነዋል የሚል መልስ አገነ ፖርፊሪ ወደበሩ እየሮጠ እኔ አልፈልገውም ሂዱ ከዚሀ። የምትገርም ሰው ነህ አይደለህም እንዴ። እኔ የምልህ ደህና ሰንብት ነው ፖርፊሪ አጉል ፈገግታ እያሳየ እንገናኛለንሲል አጉረመረመ ራስኮልኒኮቭ ከቢሮው እንደወጣ ብዙ ሰዎች በትኩረት ይመለከቱት እንደነበር አስተዋለ በመግቢያው አዳራሽ ውስጥ በዚያን ምሽት ወደፖሊስ ጣቢያ እንሂድ ያላቸውን የህንፃውን ሁለት ዘበኞች ተመለከተ የሆነ ነገር እየጠበቁ ቆመዋል ከደረጃው ደርሶ የሆነ ድምፅ ሰምቶ ዞር ሲል ፖርፊሪ እያለከለከ ወደእርሱ ሲሮጥ እየ ወዳጄ ልቤ አንዲት ቃል ልንገርህ ስለዚያ ጉዳይ በደንቡ መሠረት ጥቂት ጥያቄዎች ሳላቀርብልህ አልቀርምና በድጋሚ እንገናኛለን። እያለ ራስኮልኒኮቭ ጠየቀ ፖርፊሪ ኮስተር ብሎ አዎን ለዚያ ነው ካለ በኋላ ወደልደት ግብዣው መሄድህ ነው ወይ። ጥርሱን በድጋሚ ማፋጨት እየጀመረ መጃጃሉን አመነ ሚስተር ሉዚን የማርሜላዶቭን የቀብር ስነስርአት አስታወሰና ከቀብር መልስ በሚኖረው ዝግጅት ላይ ራስኮልኒኮቭ ጭምር እንደተጋበዘ ትዝ አለው በሌላ በኩል ደግሞ ሚስተር ሌቤዚያትኒኮቭ የዚያን እለት ጥዋት ከቤቱ ሳይወጣ ቆየ ሚስተር ሉዚን ይህን ሰው ክፉኛ እየጠላው ሄጻል ወደ ፒተርስቡርግ ከመጣ በኋላ አብሮት የሚቀለበው ከገንዘብ ስስት ሌሳ ምክንያት ስላለው ነበር በክፍለ ሀገር ይኖር በነበረበት ወቅት የቀድሞ ተማሪው ሌቤዚያትኒኮቭ በየጥናት ክበቡ ሰፊ አስተዋዕኦ የሚያደርግ ተራማጅ ወጣት እንደሆነ ሰምቶ ስለነበር ፒተርስቡርግም ውስጥ ይህ ሰው እውቅና ይኖረዋልና ልጠቀምበት ብሎ ነው ይሁንና ሌቤዚያትኒኮቭ በስመ ተራማጅነት ከዚህ ግባ የማይባል ሰው እንደሆነ ለማወቅ ሉዚን ጊዜ አልፈጀበትም ተራማጆች ሁሉ ቂላቂሎች ናቸው የሚል ማረጋገጫ ቢያገኝ እንኳን ቀልቡ አያርፍም። አይደለም እንዴ። እንዲያውም ሀሳብህን እንዳውቀው ብትገኝ ጥሩ ነው እኔ የማስበው የተለየ ነገር የለም የምታነጋግራት ጉዳይ ካለህ እርሷን መጥራቱ አይከብድም እኔ እንደማላደናቅፍህ እርግጠኛ መሆን ትችሳላለህ ከአምስት ደቂቃ በኋላ ሌቤዚያትኒኮቭ ከሶንያ ጋር ተመልሶ መጣ ሶንያ እንደተለመደው ከመገረምና ከሀፍረት ስሜት ጋር ወደ ክፍሉ ገባች ከልጅነቷ ጀምሮ አዲስ መልክ ስታይ የሚሰማት የሀፍረት ስሜት እስከዛሬ ድረስ አለቀቃትም በሚስተር ሉዚን እምነት መሠረት እንደ እርሱ አይነት ኩሩ ሰውና እንደ እርሷ አይነት ወጣትና አስደሳች ሴት በሚተዋወቁበት ጊዜ መሆን እንዳለበት ሁሉ ትህትና ባልተለየው ሁኔታ ሳቅ እያለ ተቀበላትዙ ወዲያውኑ ሊያረጋጋት ሞከረና ከእርሱ ፊት ለፊት እንድትቀመጥ ጠየቃት ሶንያ ተቀመጠች ክፍሉን ቃኘች ሌቤዚያትኒኮቭንና ከጠረጴዛው ላይ ያለውን ገንዘብ አየችና ከመቅዕበት አይኖቿን ከሚስተር ሉዚን እንደገና ሳትነቅል ተመለከተችው ሌቤዚያትኒኮቭ ክፍሉን ለቆ ሊወጣ ሲል ሚስተር ሉዚን ሶንያ እንደተቀመጠች እንድትቆይ ምልክት አሳያትና ሌቤዚያትኒኮቭን ከበሩ አጠገብ አስቆመው ራስኮልኒኮቭ አለ ወይ። ችግር እንዳልፈጥርብህ ከመስኮቱ አጠገብ እቆማለሁ በቂ ምክንያት ያለህ ይመስለኛል አለ ሚስተር ሉዚን ከሶንያ ፊት ለፊት ከሚገኘው ፎቴ ላይ ተቀምጦ ትክ ብሎ አያትና በኮራ ስሜት ከሆነ መደምደሚያ ላይ ደርሰሻል ሲላት ሶንያ ግራ ተጋባች ሚስተር ሉዚን በመልካም አንደበትም ቢሆን ፈርጠም አድርጎ ሚስስ ማርሜላዶቭ እናትሽ ማለት ናቸው አይደል እንዴ። ሌላ ሀሳብ በአእምሮዬ ይመላለሳል ሲል ተናገረ ሶንያ ወዲያውኑ ተቀመጠች ግራጫና ቀስተ ደመና ቀለማት ያላቸውን የገንዘብ ኖቶች ከጠረጴዛው ሳይ እንደገና ተመለከተችና ከመቅዕበት አይኖቿን ነቅላ ሚስተር ሉዚን ላይ አነጣጠረች የሌላውን ገንዘብ መመልከት ጨዋነት የጎደለው መሆኑ ወዲያውኑ ተሰማት ሚስተር ሉዚን በግራ እጁ የያዘውን መነዕርና በዚያው እጁ ካለው የመሀል ጣት ላይ ያረፈውን ውብ የወርቅ ቀለበት ቃኘችና አይኖቿን ከእነርሱ ላይ ዞር አድርጋ ወዴት እንደምታይ ቢጨንቃት የሚስተር ሉዚንን ፊት ትክ እያለች ተመለከተች ከ ከጥቂት ዝምታ በኋላ ሉዚን እንዲህ ሲል ቀጠለ ትናንት ለምስኪኗ ማርሜላዶቭ እግረ መንገዴን ነግሬአታለሁ መቼም ቀውጢ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ግልፅ ሆኖልኛል ጌኤ። ሠጉሽዉዉመ አዎ ቀውጢ ሁኔታ ላይ ነች በማለት ሶንያ ፈጥና ተስማማች ወይም በግልፅ ለማስቀመጥ ያህል በሽተኛ ነች አዎ ጌታው በግልፅ ለመናገር በሽተኛ ነችፅ እንደዚያ እስከሆነ ድረስ የሚገጥማትን አስከፊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ከሰብአዊነት አንፃር በበኩሌ እገዛ ሳደርግላት እፈልጋለሁፊ በአሁኑ ጊዜ የዚህ ድህነት ያደቀቀው ቤተሰብ እጣ ፈንታ በአንቺ ትከቫ ላይ ነው የወደቀው ብል የተሳሳትኩ አይመስለኝም ሶንያ ሳይታሰብ ብድግ ብላ በትናንትናው እለት የጡረታ አበል ስለምታገኝበት ሁኔታ የነገሯት ነገር አለ ወይ። በእንዲህ አይነቱ ቀውጢ ሁኔታ ውስጥ የወደቁ ሰዎችን ለመርዳት ሲባል እንደሚደረገው ሁሉ የእርዳታ ገንዘብ ማሰባሰብ ወይም የሎተሪን ዕጣ የመሰለ ነገር ማዘጋጀት ይቻላል አንቺን ማወያየት የምፈልገው ስለዚህ ጉዳይ ነው ተግባራዊ ማድረግ ደግሞ ይቻል ይሆናል ሶንያ ሚስተር ሌዚንን ትክ ብላ እየተመለከተች አዎ ጌታው አመሰግንዎታለሁ እግዚአብሔር እንደሚያሳካው እርግጠኛ ነኝ ስትል በማጉተምተም ተናገረች አዎ ይቻላል በኋላ ተገናኝተን እንማከርበታለን ዛሬም ቢሆን ይጀመር ይሆናል ዛሬ ምሸት ላይ እንደገና ስንገናኝ ስለጉዳዩ መክረን መሠረቱን እንጥላለን ከምሽቱ አንድ ሰአት ወደዚህ መምጣት ትችያለሽ።