Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማድረግ ስንነሣ ማድረግ ያለብን ሦስት ዋና ዋና ዝግጅቶች አሉ እነዚህም ሠ ሎፖ ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ማመስገን ልመና ማቅረብ ማለት ነው መጽሐፍ ቅዱስን ልናነብ ስንነሣ የመጻሕፍቱ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር እንድናነባቸውና እንድናጠናቸው ቅዱስ ፈቃዱ እንዲሆንልን ትክክለኛ ትርጉምና መልእክታቸውን እንድንረዳ እንዲያደርገን እያነበብን ሳለን ደግሞ ለመረዳት ከባድ የሆነ ነገር ሲያጋጥመን የተሰወረውን እንዲገልጥልን አንብበን ከጨረስን በኋላም ያነበብነውንና የተረዳነውን በልቡናችን እንዲያሳድርልንና በሕይወት እንድንኖረው እንዲረዳን እግዚአብሔርን መለመን አስፈላጊ ነው የሚመረጠው ቦታ በተቻለ መጠን ማዘጋጀት ነው። እነዚህም ትክክለኛ ትርጉም ያለው መጽሐፍ ቅዱስ።
የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርያት ቆ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሞች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መርሆዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አጠቃላይ መመሪያዎች ዝግጅት ማድረግ በመገዛት በማድነቅና በትሕትና ማንበብ ትክክለኛውን ትርጉም ለመረዳት መጣር ለሕይወት ማንበብ ሄ መቅድም መጽሐፍ ቅዱስ ለሰው ልጆች የእምነትና የሕይወት መመሪያ እንዲሆን ከእግዚአብሔር የተሰጠ መጽሐፍ ነው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሚናገርባቸው መንገዶችም አንዱ ነው። በትክክል ያነበቡትን የተረዱትንና የተመሩበትን ሰዎችም መንገዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል ረድቷቸዋል በዘመናችን መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብን በተመለከተ ሁለት ዐበይት ችግሮች ይስተዋላሉ ብዙ ምዕመናን መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የተሰጠ መጽሐፍ እንደሆነ ከማመንና መጽሐፍ ቅዱስን ከማክበር አልፈው መጽሐፍ ቅዱስን ሲያነቡ አይስተዋሉም በዚህም ምክንያት ከመጽሐፉ ሊያገኙት የሚገባቸው ብዙ ጥቅም ቀርቶባቸዋል ሌሎች ደግሞ ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስን ቢያነቡም እንዴት መነበብና መጠናት እንዳለበት ባለመረዳታቸው ለጥርጥርና ለክህደት ይደረጋሉ ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው ለእነዚህ ሁለት ችግሮች መፍትሔ እንዲሰጥ ማለትም ለሰው ልጆች የሕይወት እና የእምነት መመሪያ እንዲሆን የተሰጠውን መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ማንበብ እንዳለብን የሚናገር መመሪያ እንዲሆን ነው ምጽሐፈ ዐራት ዋና ክፍሎች አሉት በመጀመሪያው ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስን ምንነት ባሕርያት ጥቅም እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መርሖዎችን እንመለከታለን በሁለተኛው ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስን አጠቃላይ ይዘትና ክፍሎች እንዳስሳለን በሦስተኛው ክፍል መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ለመረዳት ሊታወቁ የሚገባቸውን የመጻሕፍቱን በእግዚአብሔር መንፈስ መጻፍ እና ቀኖና የመሳሰሉ ነገሮች እናያለን በዐራተኛው ክፍል መጽሐፍ ቅዱስን አንብቦ በዚያ መጽሐፍ ያለውን የእግዚአበሔር መልእክት በትክክል ለመረዳት መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት መጠናት እንዳለበት ይህንን ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የጥናት ስልቶችን እንመለከታለን ክፍል አንድ መግቢያ መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው። ታዎጎዎፎ ያፖቋ«ም ፍጀ «መጽሐፍ ቅዱስ» የሚለው ሐረግ ግእዝ ሲሆን በአማርኛ «ቅዱስ መጽሐፍ» ማለት ነው ሐረጉ የተመሠረተባቸው ሁለት ቃላት ትርጉም እንደሚከተለው ነው መጽሐፍ በላዩ ላይ ነገር የተጻፈበት ብራና ወረቀት ነዶው በአንድነት የታሰረና የተያዘ የተሰፋ የተጠረዘ ጽሑፍ ማለት ነው ቅዱስ ክቡር ምስጉን ልዩ ምርጥ ንጹሕ ጽሩይ ማለት ነው ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ማለት በቁሙ የተከበረ የተለየ ንጹህ የሆኑ ጽሑፎች ስብስብ ጥራዝ ማለት ነው ች ፀውያዊ ፍቿ በዚህ ጽሑፍ የምንናገርለትን መጽሐፍ ለመግለጽ ጥቅም ላይ ሲውል «መጽሐፍ ቅዱስ» የሚለው ሐረግ ሁለት ተያያዥነት ያላቸው ትርጉሞች አሉት በተለያዩ ዘመናት የተነሱ ቅዱሳን ሰዎች የእግዚአብሔርን ማንነት ባሕርያት ሥራዎች ከሰው ልጆች ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲሁም የሰው ልጆችን ለማዳን በባሕርይ ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የተከናወኑትን ነገሮች የሚገልጹና ለሰው ልጆችም የሕይወት መመሪያ የሚሆኑ በርካታ መጻሕፍትን ፈዋል ከእነዚህ መጻሕፍት መካከል የተወሰኑት በቤተ ክርስቲያን ጉባኤያት እና አባቶች ተለይተው ተመርጠው እና በቁጥር ተወስነው አሥራው መጻሕፍት ተብለው ይጠራሉ እነዚህ መጻሕፍትም ኦሪት ዘፍጥረትን ኦሪት ዘጸአትን መጻሕፍተ ነገሥትን የትንቢት መጻሕፍትን አራቱን ወንጌላትን የማቴዎስ የማርቆስ የሉቃስና የዮሐንስ የተለያዩ ሐዋርያት መልእክታትንና የዮሐንስ ራእይን የመሳሰሉት መጻሕፍት ናቸው አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ ሐረግ ማለት ከሁለትና ከሁለት በላይ የሆኑ ቃላት በማጣመር የሚፈጠር ቃል ማለት ነው ስለ አሥራው መጻሕፍት እና ስለቅዱሳት መጻሕፍት ቀኖና በስፋት በክፍል ሦስት እንመለከታለን የኢኦተቤክርስቲያን የምትቀበላቸው አሥራው መጻሕፍት ዝርዝር በክፍል ሁለትና ሦስት እንመለከታለን እንግዲህ «መጽሐፍ ቅዱስ» የሚለው ሐረግ ሀ እነዚህን መጻሕፍት ሁሉም ወይም በከፊል በአንድነት የሚገኙበትን መጽሐፍ ያመጻሕፍት ጥራዝ ለ መጻሕፍቱን እያንዳንዳቸውን ይወክላል ይቃቀሥ ለጠቃፇም በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ቃላትን በሚከተለው መልኩ እንጠቀማለን መጻሕፍቱን እያንዳንዳቸውን በተናጠል ለመጥቀስ ሲፈለግ የመጻሕፍቱን ልዩ ስም እንጠቀማለን ለምሳሌ የኦሪት ዘፀአት መጽሐፍ የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ወዘተ እንላለን መጻሕፍቱን በጥቅል ለመጥቀስ ሲፈለግ «ቅዱሳት መጸሕፍት» እንላለን ለምሳሌ «ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ» ስንል መጽሐፍ ቅዱስ በሚባለው የመጻሕፍት ጥራዝ ስብስብ ውስጥ የተካተቱን የተለያዩ መጻሕፍት ማንበብ ማለት ነው ሁሉንም መጻሕፍት እንደ አንድ የተጠረዘ መጽሐፍ ለመጥቀስ ሲፈለግ ደግሞ መጻሕፍቱን የያዘውን ጥራዝ «መጽሐፍ ቅዱስ» ብለን እንጠራዋለን በመጻሕፍቱ ውስጥ ያለውን ቃል ምንባብ የመጻሕፍቱን ይዘት ደግሞ «ቃለ እግዚአብሔር እንለዋለን ለምሳሌ «ቃለ እግዚአብሔር የነፍስ ምግብ ነው» ስንል «በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈ ቃላት ምንባባት የነፍስ ምግቦች ናቸው ለነፍስ ጤናማ ሆኖ መኖር አስፈላጊ ናቸው» ማለታችን ነው ቃለ እግዚአብሔር መባላቸውም ወደፊት እንደምንመለከተው የመጻሕፍቱ አስገሺ እና ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር በመሆኑ ነው ለምን ቅዱስ ተባለ ተባሉ። የሚለውን ነው» «ቅዱሳት» የ«ቅዱስ» ብዙ ቁጥር በአንስታይ ጾታ ነው በአጭሩ መጽሐፍቱ ቅዱስ የሆኑት አስገኛቸው ቅዱስ እግዚአብሔር ስለሆነ ነው «ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፉ ናቸው ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማነጽ በጽድቅም ላለው ጥበብ ሁሉ ይጠቅማሉ» ኛ ጢሞ « ትንቢት ከቶ ከሰው ፈቃድ አልመጣምና ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተረድተው ተናገሩ» ኛ ጴጥ ጸ «አንድ የመጽሐፈ ክርታስ ውስድ ለአንተም ከተናገርኩበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእሥራኤልና በይሁዳ ላይ በአሕዛብም ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት» ኤር ስለዚህ ቅዱሳት መጻሕፍት በቅዱስ እግዚአብሔር ፈቃድ አነሣሽነት ረዳትነት ጠባቂነት ከስህተት ገላጭነት የተጻፉ ስለሆኑ ቅዱሳት ናቸው «ቅዱሳት መጻሕፍት» ይባላሉ መጻሕፍቱ በአንድ ላይ የሚገኙበት ጥራዝም መጽሐፍም «መጽሐፍ ቅዱስ» «ቅዱስ መጽሐፍ» ይባላል የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርያት የመጽሐፍ ቅዱስ ባሕርያት የምንላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መገለጫ የሆኑትና መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች መጻሕፍት ልዩ የሚያደርጉትን ነገሮች ነው የእነዚህ ባሕርያት ምንጭ የመጽሐፉ የመጻሕፍቱ አስገ እግዚአብሔር መሆኑ ነው ሠ መጋ ጸና ሪታ ዲይጃረውም ጴይተጎውጠውም ጽሕፈት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ጸሐፊዎች በተለያዩ ዘመናት የተለያዩ መጻሕፍትን ጽፈዋል እነዚህ መጻሕፍት በየዘመናቸው የብዙዎችን ቀልብ ስበዋል ተወዳጅነትንና ታዋቂነትን አትርፈዋል ሁሉንም ግን ዘመን ሽሯቸው ዛሬ በቦታቸው ሌሎች ተተክተዋል መጽሐፍ ቅዱስ ግን ከ ዓመታት በፊት ጀምሮ የተጻፉት መጻሕፍትን የያዘ ቢሆንም ቅዱሳት መጻሕፍትን ዛሬም ሕያው ነው የመጻሕፍቱ አስገፒ ሕያው የሆነው አምላክ ስለሆነ በፊተ በነበረው ዛሬም ላለው ለሚመጣውም ትውልድ የሚሆን መልዕክት አላቸው ስለዚህ ዘወትር ሕያው ናቸው ከዚህም በተጨማሪ መጻሕፍቱ መጀመሪያ የተጻፉት በ ቋንቋዎች እብራይስጥ ግሪክ እና አራማይክ ብቻ ቢሆንም ዛሬ መጽሐፍ ቅዱስ በበርካታ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በመላው ዓለም ተሰራጭቷል ለ ያልሐፈውና ዖሟመማው ዕጳረፖጠንንምዖ ይናራልጳ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱሳት መጻሕፍትን ለጻፉ ሰዎች ከሰጣቸው ጸጋዎች መካከል ኃብተ ትንቢት አንዱ ነው ኃብተ ትንቢት ማለት ያለፉትን ነገሮች ኃላፍያትን እና ወደ ፊት የሚመጡትን መጻእያትን የማወቅ ስጦታ ማለት ነው በዚህም ምክንያት ጸሐፍቱ ከነበሩበት ዘመን በፊት የተከናወኑ ነገሮችን እርግጠ ኝነት ተናግረዋል ለምሳሌ ሙሴ እርሱ ከነበረበት ዘመን ከበርካታ ሺህ ዓመታት በፊት የሆነውን የዓለም መፈጠር በዝርዝር ጽፏል በርካታ ነቢያትም በየዘመናቱ እየተነሱ ወደ ፊት ስለሚሆኑና ስለሚደረጉ ነገሮች ተናግረዋል ነቢዩ ኢሳይያስ ከጌታችን መወለድ ብዙ ዓመታት አስቀድሞ የእመቤታችንን በድንግልና መጽነስና ወንድ ልጅ ጌታችንን መውለድ እንዲህ ሲል ተንብዮ ነበር «ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች» ኢሳ ጂፀ ነቢዩ ዳዊትም ከጌታችን መወለድ ዓመታት ያህል አስቀድሞ የጌታችንን ሞትን ድል አድርጎ መነሣት እንዲሁም ወደ ሰማይ ማረግ መውጣት እንደተፈፀሙ ሆነው አይቷቸው እንዲህ ሲል ተናግሮው ነበር «እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ» መዝ «እግዚአብሔር በእልልታና በምስጋና ዐረገ» መዝ ገና ወደፊት ስለሚረጉትና ስለሚሆኑት ነገሮችም የተነገሩ በርካታ ትንቢቶች አሉ ሌሎቹ ትንቢቶች እንደተፈፀሙት እነዚህም ደግሞ ጊዜያቸውን እየጠበቁ ይፈፀማሉ ከነዚህም በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት ተለይቶ በዓይነ ሥጋ ስለሚታየው ብቻ ሳይሆን ስለማይታየውም ዓለም ማለትም ልናያቸው ስለማንችላቸው ስለ ገነት ሲኦል መንግሥተ ሰማያት መላእክት ስለ ሰማያዊቷ የእግዚአብሔር መንግሥት እና ስለመሳሰሉት ይናገራል ኋሕ ያሟቋሙቶ ወደ ቅድዕና ዉሕይወታ ይመራጳ ይፀረጎልም ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉት በእግዚአዘብሔር መንፈስ ስለሆነ በውስጣቸው ያሉ ምንባባት የሰው ልብ ለእግዚአብሔር ፈቃድ የማስገዛትና ሰዎች በእግዚአብሔር መንገድ እንዲሄዱ የማድረግ ኀይል አላቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአይሁድ ተላልፎ ተሰጥቶ በተሰቀለ ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ መካከል ሁለቱ ሉቃስና ቀለዮጳ ይባላሉ አስቀደሞ ስለ ትንሣኤው የሰጠውን ተስፋ ልብ ባለማለታቸው ተስፋ ቆርጠው ከኢየሩሳሌም ወጥተው መሄድ ሲጀምሩ ክብር ይግባውና ጌታችን በመካከላቸው ተገኝቶ አብሯቸው መጓዝ ጀመረ በመንገድ ላይ ሳሉም ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጎመላቸው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ማንነታችን እንድንረዳና መሆንና ማድረግ የሚጠ በቅብንን እንድናውቅ የሚረዳ የሕይወት መመሪያ ልንጓዝበት የሚገባንን መንገድ የሚያሳይ የሕይወት ካርታ ነው ሐ የአገልግሎት መመሪያ ነው አገልግለት የሚለው ቃል ሁለት ጉዳዮችን ሲወክል ይችላል ለፈጠረንለሚጠብቀንና ለሚመግበን በድለን ስንወድቅ የሞት ዋጋ ከፍሎ ላዳነን አምላካችን አምልኮና ምስጋና እርሱ ለመረጣቸው ቅዱሳን ደግሞ አክብሮትና ምስጋና የምናቀርብባቸው ሂደቶች አገልግሎት ይባላሉ ጸሎትቅዳሴስግደት እግዚአብሔርን እንደ እግዚአብሔርነቱ የማያመልኩትንና ልጁን ወደዚህ ምድር ልኮ የጠፋውን ዓለም ማዳኑን ያሳመኑንና ያልተቀበሉትን አስተምሮ ወደ ትክከለኛው እምነት ሃይማኖት ለማምጣትና በሃይማኖት ያሉትም እግዚአብሔርን የሚያስደስት ኑሮ እንዲኖሩ ለማድረግ የሚሠሩ ሥራዎች አገልግሎት ይባላሉ መጽሐፍ ቅዱስ ሁለቱንም አገልግሎቶች ለምን እንደምናገለግል እንዴት ማገልግል እንዳለብን እና የአገልግሎት ዋጋችን ምን እንደሆነ ስለሚነገረን የአገልግሎት መመሪያ ነው መ ለምድራዊ ሕይወታችን መሳካት የሰው ልጅ ወደማያልፈው ዓለም ከመሸጋገሩ በፊት በዚህ ዓለም ጥቂት የዝግጅት ዘመናትን ያሳልፋል መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅ በዚህ ዓለም ሲኖር ለማያልፈው ዓለም ለሚያደርገው ዝግጅት ብቻ ሳይሆን በዚህ ዓለም የሚኖረው ኑሮ ስኬታማ እንዲሆን በርካታ ጥቅሞችን ይሰጣል ለማሳያ እንዲሆን ሁለት ነገሮችን እንጥቀስ ሁ ሰዎች ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ተከትለው ቢኖሩ ዓለማችን ፍትሕ ነጻነት እኩልነት ፍቅር የሰፈነባት ስጋት የጠፋበት ጥሩ የመኖሪያ ስፍራ ትሆን ነበር ሁ መጽሐፍ ቅዱስ የምድራዊ ጥበብ ምንጭ ነው ስለ ዓለም ታሪክ ሕግና አስተዳደር ሕክምና ግንባታና ስነ ሕንፃ ወዘተ በርካታ ቁም ነገሮችን ያስተምረናል በአጠቃላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከማንበብና ከማወቅ እነዚህና ሌሎች በርካታ ጥቅሞች ይገኛሉ መጻሕፍትን አለማወቅ ደግም «ህዝቤ ዕውቀት በማጣት ጠፋ» ሆሴ እንተባለው የጥፋት መንገድ ነው ስለዚህ በቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ልንበረታ ይገባናል ሐዋርያውም «የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ ቆላ እያለ የሚመክረን ለዚሁ ነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መርሆዎች ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና ልንረዳቸውና ሁል ጊዜም ልናስተውላቸው የሚገቡ ሁለት መሠረታዊ መርሆዎች አሉ እነዚህም ሀ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ማጥናትና መረዳት ማለት የጽሑፉን ትርጉምና እግዚአብሔር በዚያ ጽሑፍ አማካኝነት ለእኛ እያስተላለፉ ያሉትን መልእክት በትክክል መረዳት ማለት ነው ቅዱሳት መጻሕፍት ደግሞ የተጻፉት በእግዚአብሔር መሪነት በመሆኑ በመጻሕፍቱ ባለቤት ፈቃድና ዕርዳታ ካልሆነ በስተቀር ይህንን ማድረግ አይቻልም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን እንዲህ በማለት በግልጽ ተናግሮታል «ከእናንተ ጋር ስኖር ይህን ነግሬአችኋለሁ አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል»ዮሐ «የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ ነገር ግን አሁን ልትሸከሙት አትችሉም ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል» ዮሐ ቅዱስ ጳውሎስም ለቆሮንቶስ ምእመናን ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ በማለት ጽፎላቸዋል «በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃዱ ሆኗል» ኛ ቆሮ «መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው» ቆሮ በአጠቃላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብም ሆነ መረዳት የሚቻለው በመጻሕፍቱ ባለቤት በእግዚአብሔር ፈቃድና እርዳታ ነው ለ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብና ትርጉማቸውን መረዳት የክርስቲያኖች ግብ አይደለም ግባችን ያወቅነውን መፈፀምና በተረዳነው መጠን መኖር ነው የቅዱሳት መጻሕፍትን ጥናት ወደዚህ የሚያመጣ መንገድ ብቻ ነው ጌታ ቃለ እግዚአብሔርን እንዴት መማር አንዳለብን በዘር በምድር በፍሬ በመሳሰሉት መስሎ እንዲህ በማለት አስተምሯል «እነሆ ዘሪ ሊዘራ ወጣ እርሱም ሲዘራ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ ወፎችም መጥተው በሉት ሌላውም ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ላይ ወደቀ ጥልቅ መሬትም ስላልነበረው ወዲያው በቀለ ፀሐይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ እሾህም ወጣና አነቀው ሌላውም በመልካም መሬት ላይ ወደቀ አንዱም መቶ አንዱም ስድሳ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ። » ብሎ በትሕትና እንዲያስረዳው እንደለመነው ሐዋዐ እኛም በትሕትና ወደ መምህራን መቅረብና ቅዱሳት መጻሕፍትን እንዲያብራሩልንና እንዲተረጉሙልን መጠየቅ የቤተክርስቲያን አባቶችና መምህራን ያዘጋጂቸውን የትርጓሜ እና የማብራሪያ መጻሕፍት መጠቀምም ይኖርብናል እነዚህ ከላይ የተመለከትናቸው ነገሮች ሁሉ ከመንፈሳዊነት ማደግ ጋር አብረው የሚያድት ናቸው ስለዚህ ለዚህ በሚያበቁ ነገሮች ማለትም በጸሎት በጾም በተመስጦ በስግደት ልንበረታ ይገባናል የምናነበውን ነገር ትርጉምና እግዚአብሔር በዚያ ጽሑፍ አማካኝነት እያስተላለፈ ያለውን መልእክት በትክክል ለመረዳት መጣር አስቀድመን እንደተናገርነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዓላማ የምናነበውን ነገር ትክክለኛ ትርጉም እንዲሁም እግዚአብሔር በዚያ ጽሑፍ አማካኝነት እያስተላለፈ ያለውን መልእክት በትክክል መረዳት ነው ቋንቋ እና ጽሑፍ ሐሳብን የማስተላለፊያ መንገዶች ናቸው ይሁን እንጂ አንዳንድ ጊዜ አንድን ጽሑፍ በምናነብበት ጊዜ ትርጉሙን ለመረዳት ሊከብደን ወይም ለትርጉም አሻሚ የሆነ ንባብ ሊያጋጥመን ይችላል ከዚህም በተጨማሪ ጽሑፉን እግዚአብሔር ወይም ጸሐፊው እንዲኖረው ካሰበው በተለየ መንገድ ልንረዳውም እንችላለን በእርግጥ እነዚህን ችግሮች አስወግዶ መጻሕፍትን እንድንረዳ የሚያደርገው እግዚአብሔር ነው ነገር ግን ከእኛ የሚጠበቁና ልናደርጋቸው የሚሜገቡ ነገሮች አሉ ሀ የመጽሐፉንና የጸሐፊውን ዳራ መረዳት ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉት ከረጅም ጊዜ በፊት ቢያንስ ከ ዓመታት በፊት ነው ስለዚህ መጻሕፍቱ በተጻፉበት ዘመን የነበረው ሁኔታ ማለትም ባህል ቋንቋና አነጋገር መልክአ ምድር ሥልጣኔና ጥበብ ወዘተ አሁን ካለው በብዙ መልኩ የተለየ ነው መጻሕፍቱ የተጻፉበት ቦታ እኛ ዛሬ ካለንበት ቦታ የተለየ ሲሆን ደግሞ ልዩነቱ የበለጠ ይሰፋል መጻሕፍቱን ልንረዳቸው የሚገባው በዚያው በተጻፉበት ዘመን እና ቦታ ከነበረው ሁኔታ አንጻር እንጂ ዛሬ ካሉት ሁኔታዎች ቋንቋ ባህል ባለመሆኑ ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመረዳት እነዚህን ነገሮች ማጥናት አስፈላጊ ነው ከዚህም በተጨማሪ የጸሐፊውን ማንነት ጽሐፉ የተጻፈበትን ዓላማ ወዘተ ማጥናትና መረዳት ለጥናታችን ውጤታማነት በጣም አስፈላጊ ነው እነዚህን ጉዳዮች በዝርዝር በክፍል ዐራት እንመለከታቸዋለን ለ ዐውደዊ ፍቺ መጠቀም ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናነበብና ስንተረጉም እያንዳንዷን ቃል ልንፈታት የሚገባን በዚያው ባለችበት ዓረፍተ ነገር ውስጥ ካላት ድርሻ አንጻር መሆን አለበት ዓረፍተ ነገሩንም እንዲሁ ባለበት ምዕራፍ ውስጥ ካለው ድርሻ አንጻር ምዕራፉንም ከጠ ቅላላው ከመጽሐፉ ይዘትና ዓላማ አንጻር መተርጎምና ለመረዳት መሞከር አለብን ሐ ጉዳዮችን በአጠቃላይ ዕይታ መረዳት አንድን ጉዳይ እውነት በትክክልና በጥልቀት ልንረዳው የምንችለው ጉዳዩን ከተለያዩ አቅጣጫዎች አንጻር ስንመረምረው በጉዳዩ ላይ የተባሉ ነገሮችን በሙሉ ስንዳስስና ጉዳዩን በምልአት ስናውቀው ነው ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠናም ይህንኑ ማድረግ አለብን ስለዚህ አንድን ጉዳይ በተመለከተ ለምሳሌ ድኅነት ጸሉሎት እምነት ፍርድ ምልጃ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናነብ በጉዳዩ ላይ አንድ ንባብ ወይም መጽሐፍ የሚለውን ብቻ ሳይሆን ስለ ጉዳዩ በተለያዩ ቅዱሳት መጻሕፍት የተባሉትን ነገሮች ሁሉ ማየት አስፈላጊ ነው ይህ ሲደረግ በአንድ ጉዳይ ላይ የተለያዩ የሚቃረኑ የሚመስሉ ሐሳቦች ከተለያዩ ቦታዎች ሊገኙ ይችላሉ ነገር ግን እያንዳንዱ ትምህርት ከምን አንጻር እንደተሰጠ ስናጠና ቀስ በቀስ በጉዳዩ ላይ ከንፈኝነት እና ከከፊል እይታ የራቀ የተሟላ ዕውቀትና መረዳት ይኖረናል መ ተገቢውን ቅደም ተከተል ጠብቆ ማንበብ ቅዱስ ጳዉሎስ በዕብራውያን መልእክቱ መግቢያ ላይ «ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን» ዕብ እንዳለው የእግዚአብሔር ለሰው ልጆች መገለጥ ቀስ በቀስና ደረጃ በደረጃ የተደረገ ነው በእያንዳንዱ ደረጃ ላይ የተደረገው መገለጥም ከዚያ በፊት የነበረውን መገለጥ መሠረት ያደረገ ነው እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደዚህ ዓለም ልኮ ዓለሙን ያዳነበት መንገድ ከዚያ በፊት በነበሩ ዘመናት የተደረጉ ዝግጅቶችን መሠረት ያደረገ ነው ስለዚህ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና በዘፈቀደ ወይም መጽሐፍ ቅዱሱን ስንከፍት ያገኘነውን ነገር ከማንበብና ከማጥናት ይልቅ ትክክለኛውን ቅደም ተከተል ተከትሎ መጻሕፍቱን ማንበብ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረን ያደርጋል ቅዱሳት መጻሕፍቱ እንዴት ባለ ቅደም ተከተል ቢጠኑ ይሻላል የሚለውን ወደፊት እንመለከታለን ለሕይወት ማንበብ ቅዱሳት መጻሕፍትን የምናጠናበት ዓላማ የእግዚአብሔርን ማንነት ራሳችንን እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን መልካም ዕቅድ እና ለዚህ ዕቅድ መሳካት ከእኛ የሚጠ በቀውን ተረድተን የሚጠበቅብንን ለማድረግ መሆኑን ተመልክተናል ስለዚህ ቅዱሳት መጻሕፍትን ስናጠና ይህንን ልብ ማለትና ለማስተማርና ለመጻፍ ከማንበብ በፊት በመጻሕፍቱ መስተዋት ራስን እየተመለከቱ ማንበብና ማጥናት የግድ ነው ይህም ማለት የእግዚአብሔርን ለሰው ልጆች ያለውን ፍቅር ቸርነት ረዳትነት መገንዘብና ማጣጣም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለውን እቅድ ከተረዳን በኋላ ራሳችንን ከዚያ አንጻር መገምገምና የሚጎድለንን መረዳት መንገዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ካደረጉ ቅዱሳንና በጥፋታቸው ከወደቁ ሰዎች የሕይወት ተሞክሮ ትምህርት በመወሰድ መጻሕፍትን ማጥናት ማለት ነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በአግባቡ ካልተያዘና ካልተጠቀሙበት በርካታ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።